የመቀሌው ሰላማዊ ሰልፍ እንዲተላለፍ ተወሰነ

August 3, 2013

መንግስት አንድነት ፓርቲ በመቀሌ የተጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ በኃይል አደናቀፈ፡፡ የመቀሌ ከተማ አስተዳደር በቅስቀሳ ላይ የነበሩ የአንድነት አመራሮችን በህገወጥ ሁኔታ በማሰር፣ከመቀሌ ለቅቀው እንዲወጡ በማስጠንቀቅ እንዲሁም ቅስቀሳ ሲደረግባቸው የነበሩ ቁሳቁሶችን በአደባባይ በመንጠቅ በመቀሌ በቂ ቅስቀሳ እንዳይደረግ በማድረግ ሰላማዊ ሰልፉን በኃይል አደናቅፏል፡፡

የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ግብረኃይል ኮማንድ ፖስት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ መንግስት በመቀሌ የወሰደውን ህገወጥ እርምጃ በመገምገም በነገው እለት የተጠራውን ሳላማዊ ሰልፍ እንዲተላለፍ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ በቅርቡም በመቀሌ ከተማ በተጠናከረ ሁኔታ ዳግም ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚጠራ በመወሰን ሰልፉ የሚያደርግበትን ቀን በሚቀጥሉት ቀናት ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡ አንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ግብረኃይል ጀግናው የመቀሌ አዋሪ የመንግስትን ህገወጥ እርምጃ በማውገዝ ለአንድነት ፓርቲ አመራሮች ያሳየውን አጋርነት በማድነቅ በመቀሌ ከተማ በቅርቡ የሚጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ በንቃት እንዲጠባበቅ ጥሪን አስተላልፏል፡፡
‪#‎millionsofvoicesforfreedom‬ ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎UDJ‬

Latest from Blog

ነገሩ እንዲህ ነው ባሳለፍነው ታህሳስ 15 በተካሄደው ብልጽግና ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ላይ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አረጋ ከበደ እጃቸውን አውጥተው ተናገሩ እኔ አቅቶኛል የአማራ ክልል ቀውስ ማስተዳደር አልቻልኩም ብለው ተናገሩ በዚህ ጊዜ

“አንተን ለማኝ አደርጋለሁ” አቢይ አሕመድ ለአማራ ክልል ፕረዚዳንት ለአረጋ ከበደ የሰጠው ማስጠንቀቂያ

January 31, 2025
ከቴዎድሮስ ሃይሌ የምናከብራቸው ጀነራል ተፈራ ማሞ ሰሞኑን አደባባይ ወጥተው አድምጠናል:: የጀነራሉ ጤንነትና ደህንነት ሲያሳስበን ለቆየነው ወገኖች ሁሉ በጥሩ ቁመና ላይ ሆነው በማግኘታችን የሕሊና እረፍት ሰጥቶናል:: አሁንም ባሉበት ሰላሞት እንዲበዛ ምኞታችን ዳር የለውም::

እስክንድር ነጋ እና ጀነራል ተፈራ ማሞ ከድል ለዲሞክራሲ እስከ ፉኖ ተሰማራ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ዛሬም እንደ ትናንቱ አያሌ ምሁራንና ታዋቂ ነን ባይዎች ስለብሔራዊ ሽምግልና እርቅ ይደሰኩራሉ፡፡ ያለምንም ሐፍረት ቅዱሱን ሽምግልናን ከምእራብ ከተሸመተው ኤፍሬም ይሳቃዊ ድርድር ጋር እያምታቱ የአያት የቅድመ አያቶቻችንን የተባረክ የሽምግልና ሐብት ያበላሻሉ፡፡ ሽምግልና በመለኮት

ፍትህ የሌለው ሽምግልናና እርቅ ሥራ እንደሌለው እምነት የሞተ ነው!

Go toTop