ሰበር ዜና – በወላይታ የኢህአዴግ አባላት፣ፖሊስና ደህንነቶች በአንድነት አባላት ላይ ድብደባና ዝርፊያ እየፈፀሙ ነው

በወላይታ የኢህአዴግ አባላት፣ፖሊስና ደህንነቶች በአንድነት አባላት ላይ ድብደባና ዝርፊያ እየፈፀሙ ነው

አንድነት ፓርቲ በመጪው እሁድ በሶዶ ከተማ ለሚያደርገው ህዝባዊ ስብሰባ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ የበሩ የአንድነት አባላትን ፖሊሶችና ደህንነቶች በመደብደብና ያሰባሰቡትን የህዝብ ፊርማ በመንጠቅ ላይ መሆናቸውን የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡ የአንድነት የወላይታ ዞን አመራሮችም እንዳረጋገጡት ታርጋ ያልለጠፉ ባጃጆችንና ሞተር ሳይክሎችን የያዙ ፖሊሶችና ደህንነቶች በተደራጀ ሁኔታ የሚበተኑ በራሪ ወረቀቶችንና የፀረ ሽብር ህጉ እንዲሻር እየተሰባሰበ የሚገኘውን ፊርማ በመቀማት ላይ ናቸው፡፡ አንድ ስሙ እንዲገለፅ ያልፈለገ የወላይታ ዞን ፖስ አባል ለፍኖተ ነፃነት እንደገለፀው የዞኑ አስተዳደሮች “የአንድነት አባላትን በእጃቸው ያለውን በራሪ ወረቀትና የፊርማ ማሰባሰቢያ ቅፅ ቀሙዋቸው እነሱን ማሰር አንዳች አይፈይድም” ተብለዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን ሰብሳቢ አቶ ወኖ መንአሳ ለፍኖተ ነፃነት “ኢህአዴግ ያሰማራቸው ግለሰቦች ከአንድነት አባላት ላይ በራሪ ወረቀት ከመቀማት አልፈው ቦርሳ ፣ጫማ ፣በፌስታል የተያዘ ፍራፍሬ ሳይቀር በመቀማት ላይ ናቸው” ብለዋል፡፡ አያይዘውም ለስብሰባ ስራ የተዘጋጁ ቁሳቁሶችም እንደተዘረፉ አስረድተዋል፡፡‪#‎millionsofvoicesforfreedom‬ ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎UDJ‬ – 

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  በጦርነትና ግጭት ውስጥ ሆነው የተፈተኑና የማለፊያ ነጥብ ያላመጡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከ2014 ዓ.ም መደበኛ ተፈታኞች ጋር እንዲፈተኑ ውሳኔ ተላለፈ

5 Comments

  1. The woyane fascist thugs are known for their violence , kidnap, murder and harrassment of the population. Violence is second nature to the fascist thugs.

Comments are closed.

Share