በዉጭ አገር ለምትገኙ ለተከበራችሁ የኢትዮጵያዉያን ሜዲያዎች — ከሰሜን አሜሪካ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት ግብረ ኋይል

በዉጭ አገር ለምትገኙ ለተከበራችሁ የኢትዮጵያዉያን፡ ሜዲያዎች፣ የድህረ ገጽ አዘጋጆች፣ የፓልቶክ ክፍሎች፣ የሬዲዮ ፕሮግራም አዘጋጆች፣ የቴሌቭዥን ስርጭት ጣቢያዎች ፡

ከሁሉ አስቀድመን ፣ በየመልኩ በዉጭ ለምንኖር ኢትዮጵያዉያን፣ ባህላችንን፣ ታሪካችንን ችግሮቻችንና የአገራችንን እሴቶ፣ በየወቅቱ በመከታተል፣ ግንዛቤ እንድናገኝ ለምታደርጉት ጥረት፣ ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

ዛሬ አገራችን አጣብቂኝ ሁኔታ ዉስጥ እንዳለች፣ የሁላችንም ግንዛቤ ነዉ። ከሁሉም በላይ፣ እንደ ማንኛዉም አገር ሕዝብ፣ የሃይማኖት የብሄረሰብ የቋንቋ ልዩነቶች ቢኖሩም፣ የእኛ የኢትዮጵያዉያን ልዩ እሴት፣ ልዩነቶቻችንን አቻችለን፣ በፍቅርና በሰላም መኖራችንና መቻቻላችን ቀዳሚነቱን ስፍራ የሚይዝ ነዉ። ዛሬም ፖለቲካዉ በፈለገዉ አቅጣጫ ቢሽከረከርም፣ ይህንን የሕዝባችንን አኩሩና ትልቅ እሴት ሊያጠፋው አልቻለም።

ይሁን እንጂ፣ ጊዜ በረዘመ ቁጥር፣ አጥፊ ፕሮፖጋንዳዎች ትዉልዱን እየሸረሸረ ከሄደ፣ የአንድነት እሴቶቻችን አደጋ አይገጥመዉም ማለት አይቻልም።

ለዚህም ነዉ ኢትዮጵያን የማዳን መስዋትነት እያስከፈለ ያለ ትቅል ትግል የሚደረገዉ። ፖለቲካዉን በበላይነት ተቆጣጥሮ እያሽከረከረ የሚገኘዉ ገዢዉ ፓርቲ፣ ሕወሃት/ኢሕአዴግ፣ ጎጂና ከፋፋይ የሆኑ ፖሊሶዎቹን እንዲቀይር፣ የዜጎችን መብት እንዲያከብር.፣ ለሕዝብ ጥይቄ አዋንታዊ መልስ እንዲሰጥ የሚጠይቅ ከፍተኛ የሕዝብ ጩኸት ከሁሉም ማእዘናት እየተሰማ ነዉ። ሰሞኑን፣ በአንድነት ፓርቲና ሌሎች ድርጅቶች መሪነት፣ ደፎር መብቱን ለማስከበር ሰልፍ በመዉጣት፣ ሕዝቡ ወደ ተሻለ የ እምቢተኝነት የትግል ምእራፍ መሸጋገሩን ያሳያል።

ዉድ ኢትዮጵያዉያን

ይህ ሕዝብ፣ ሰላማዊ በሆነ መንገድ በሰልፍ ወጥቶ ቅሬታዉን ለሚመለከተዉ መንግስት ማቅረቡ በምንም መመዘኛ ቢሆን ትልቅ ውጤትና ድል ነዉ። በተለይም የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻት ንቅናቄ በሚል ፣ በሰለጠነ መልኩ የሚደረገዉ፣ ትግል የፖለቲካ ባህላችንን መዳበርም ያመለክታል።

ይህ ትግል ቀላል ትግል አይደለም። የፖለቲካ ኃይልና ባላቤቱ የሆነው ህዝብ፣ የሚያደርገዉ ትግል፣ ከፍተኛ እገዛና ድጋፍ ይፈልጋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ቶሌ፤ የቦሌ መለማመጃ - መስፍን አረጋ

በመሆኑ በበኩላችሁ በምታደርጓቸው ፕሮግራሞች፣ ይህንን ትግል በማገዝ ረገድ ከሕዝብ ጎን እንድንቆሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን። በርግጥም በአንድነት ከተባበርን፣ አምባገነኑን ስርዓት አስገድደን፣ በሕዝብ መዳፍ ሥር ማዋል የምንችልበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም።

በሰሜን አሜሪካ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት ግብረ ኋይል

 

 

1 Comment

Comments are closed.

Share