የሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በከፋፋዮች ሴራ አትናወጥም!!! ለአንድነት ከቆሙ ምእመናን

በስመ ሥላሴ አንድ አምላክ አሜን!
የሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በከፋፋዮች ሴራ አትናወጥም!!!  ለአንድነት ከቆሙ ምእመናን  የኢትዮጵያን ሕዝብ በዘርና በኃይማኖት በመከፋፈል እኩይ አላማውን በተለያየ መንገድ እያራመደ ያለው የወያኔ ‘መንግስት’ የተለመደውን የዘረኝነትና የከፋፋይነት ተግባሩን በተለይ በውጪ አገራት በሚገኙ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በሚገለገልባቸው አብያተ ክርስቲያናትና ኮሚኒቲዎች በማተኮር በውጪው ዓለም የአልሞት ባይ ተጋዳይነት መፍጨርጨር እያደረገ ይገኛል። ይህ በውጪው አለም እየደረሰበት ያለውን ኪሳራ ለማስቆም ሲል ተቃዋሚ በመምሰል ሰርጎ በመግባት፣አንዳንዶችን በጥቅም፣ አንዳንዶችን በመደለል፣ የዋሃንንም በማጭበርበር ሰላምና አንድነትን ለመበጠበጥ የማቆፍረው ጉድጓድ የለም።  ..ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ተጨማሪ ያንብቡ:  አማራ ሆይ አሁንም ጉድህን ስማና ላልሰማው አሰማ! - ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

5 Comments

  1. This is a rubbish propaganda!! First the writer does not identify himself/herself. We all know that there are two fathers for the ethiopian church. that is a bitter reality the orthodox christians live with. however, the writer methodically tries to convince as if he is in a majority and has a moral obligation of saving a failing church administration. What i can see so far from chruch followers in the diaspora is that everyone wants to involve in the daily business of the church. Be advised, you are just a member of the congregation and you can voice your concerns to the right authority, not here on the cyber space.

  2. እውነት ነው። ብዙ አወናባጆች አሉ። መጠንቀቅ ይገባል። የእግዚአብሔርን ሃይል ክዶ ከከሃዲያን ጋር እንተባበር ማለት በጣም ያሳዝናል። ምን ለውጥ መጣና ነው አሁን? አሁንም እንደተከፋፈሉ ናቸው። ታዲያ ፕሮፌሰሩ እንዳሉት ለምን መከፋፈሉ ውስጥ ገብተን እንወግናለን? ሲሆን ሲሆን እዲግባቡ አንድነት እንዲፈጥሩ መጸለይ ነው እንጂ እንዴት ከወያኔ ደጋፊዎች ጋር እንተባበር ይባላል ባከችሁ? እነዚህ መዘምራን ድሮም ያልበሰሉ ሲነዷቸው የሚነዱ የሃይማኖታቸውን ታሪክ የማያውቁናቸው። ህዝበ አዳም ሆይ ንቃ። ሜኔሶታ የወያኔ መቀበሪያ እንጂ የወያኔ ደጋፊዎች መፈንጫ አትሆንም። ይህንነ ሁኔታ በዝምታ ብቻ የምናልፈው አይደለም። ቤተክርስቲያናችን አገራችን ኮሞኒታችን ጭምር ናት። ከዛ አሳደውን መጣን እዚህ ደግሞ አላስኖር ሊሉን ነው እንዴ ጎበዝ? ምናለ ቢተውን። ዋልድባን ሲያርሱት ገዳማቱን ሲያቃጥሉት የት ነበሩ ደርሶ አሁን ለቤተክርስቲያን ተጨናቂ የሆኑት። የወያኔ ቅጥረኞችና ሆዳሞችን ማጋጥ አለብን። ማግለል አለብን። ደግሞ እናውቃቸዋለን ፎቷውንም ጭምር እናወጣዋለን ሁሉም እንዲያውቃቸው። ይሄ የቤተክርስቲያን ጉዳይ አይደለም የፓለቲካ ነው።

  3. ስልቻ ቀልቀሎ ሆነብኝ ነገራችሁ። ቤተክርስቲያኗን የከፈላት ወያኔ/ኢሓዴግ እንጅ ተገፍተው የተሰደዱት አባቶች አይደሉም። ወያኔንና የፖለቲካ ውሳኔውን መቃወምና ከእውነተኛና ከተገፉት ጎን እንቆማለን ማለት አንድ ነገር ሆኖ ሳለ። አሁንም ያው ዶክተር ጌታቸው የሚሉትን ሦስተኛ እረድፍ (ገለልተኝነት) ማለት ትክክል አይመስለኝም። ከሆነላችሁ እውነትን በግልጽ ደግፏትና ከተገፉ መነኩሳት ጎን ቁሙ። አለበለዚያ ሲኖዶሳችን አዲስ አበባ ነው የምትሉትን አቁሙ።፡ከሆነም ከመረቁ ብቻ ሳይሆን ከስጋውም ጨምሩት። የትግራይ ገንጣዮች ከሜዳ ጀምረው ያደራጁትን ጉባኤ ጳጳሳትን አትደግፉ። ሦስተኛውን መንገድ ተውት። ለእውነት ቁሙ። ተበዳይንና በዳይን በእኩል አትኮንኑ

  4. በመጀመሪያ አቶ ዳመምጠው ነገሩን ሁሉ ዳመጥከው። እውነት ማለት ምንድን ነው? ሲኖዶስ የምትለው፣መንበር የሚባለው እዚህ ከሆነ ፓትርያርኩ ይመለሱ የሚባለው የት ነው? ከዚሁ ሆኖ መምራት ከተቻለ ምን ያጨቃጭቃል? ሲኖዶስ የጳጳሳት ስብሰባ ብቻ ከሆነ የትም ሊኖር ይችላል። ሲኖዶስ ማለት ግን ከዚህም በላይ የቤተክርስቲያን አመራር ሰጪና የተለየ መንበር/ማዕከል/መቀመጫ ያለው የቤተክርስቲያን የበላይ አካል ነው። ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የሲኖዶስ መቀመጫው ኢትዮጵያ አዲስ አበባ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስት ማርያም አምስት ኪሎ ነው። በወያኔ የተባረሩት ትክክለኛው ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ መንበራቸው መመለስ አለባቸው። እውነቱ ይሔ ነው።እዚህ የተሰደዱ ፓትርያርክ እንዳሉ እዛ ፓተርያርክ የሌለው ሲኖዶስ እንዳለ እናምናለን። ፓትርያክ ይሰደዳል።ሲኖዶስም ያለፓትርያርክ ሊኖር ይችላል። ችግር በሆነ ጊዜ እንደዚህ ዘመን። ከዚህ ውጪ ያለው አካሔድ ሐሰት ነው። ክርስቲያኖችም በታሪካቸው ያደረጉት ይህንኑ ነው። አላውያን መንግሥታት በየዘመኑ ተነስተው ተመሳሳይ ድርጊት ፈጽመዋል፡፡ እውነተኛ ክርስቲያኖች ግን የወሰዱት ርምጃ አሁን ገለልተኞች እየተባሉ የተፈረጁትን አይነት ነው። የተሰደዱት ፓፓሳት ሲኖዶስ ሳይሆን ማኅበረ ካህናት አቋቁመው ቢሆን ኖሮ በአለም ላይ ያለው ኦርቶዶክሳዊ በአብዛኛው ድጋፍና ህብረት የሚኖረው ለእነርሱ ነበር። ምን ያደርጋል አቡነ መልከ ጼዲቅ ሁሉንም አበላሹት። አሁንም ማረም ይቻላል። እውነቱ ይሔ ነው። አቶ እዝራ ግን ፈስ ያለበት እንደሚባለው ስለሆንክ ልረዳህ አልችልም። ሁለት ፓትርያርክ እንዲኖር ያደረገው ወያኔ ስለሆነ እውነቱን በግድ ዋጠው ቢመርም። እውነት ደግሞ በአደባባይ በሳይበር ስፔስ ላይ ነው መነገር ያለባት። የምትፈልገው ሃሳቡን እንጂ የጸሐፊው ስም ምን ያደርግልሃል? አየህ የወያኔውያን ጠባይ? በጡንቻ እንጂ በሃሳብ መቼ ይሆንላቸዋ! ለማንኛውም መኔሶታዎች ነቅተናል አንከፋፈልም! ከስህተታቸው የማይመለሱ ለወያኔ ያደሩ ሰዎችም በአደባባይ ይጋለጣሉ። ከማህረሰባችንም ይገለላሉ። ጸሐፊው ስሙን ስላለመግለጹ ከሰሃል እስኪ አንተ ትክክለኛ ስምህንና ፎቶህን ግለጽ?

  5. የወያኔ ቅጥረኞቹ እነ አሃዱ መሆናቸውን ደርሰንበታል። በየቦታው ዲስኩሩን ሲነፋ ተሰምቷል። ይህን ቅዳሴ እንኳን የማይችል ሰው ቀጥራችሁ ይህን ያህል ገንዘብ እየከፈላችሁ ሞርጌጁን ሳይቀር የምትከፍሉለት ምን ያድርግ ጥጋብ ነው። ይህነ ሰው ባስቸኳይ አባሮ ሌላ ችሎታ ያለው ካህን መቅጠር አይቻልም ወይ? ፔቲሺን ለመፈረምና ይህን ተላላኪ ልኩን ለማሳየት የመጀመሪያው ሰው ነኝ እሺ። እንዲህ አይነት የቤተክርስቲያን ትምህርት የሌለው ዳቆን እንኳን መሆን የማይችል ሰው ምንም አስተያየት መደረግ የለበትም።

Comments are closed.

Share