(ዘ-ሐበሻ) የሚያሳዝን ዜና ነው ይሄ። ኢትዮጵያዊቷ ወጣት የቤት ሠራተኛ በሳዑዲ አረቢያ ራሷን አጠፋች። ኤመሬትስ 247 የተሰኘው ድረ ገጽ እንደዘገበው ይህች ወጣት ኢትዮጵያት ራሷን ያጠፋችው በኤክትሪክ ገመድ አንገቷን በማነቅ እና ከወንበር ላይ በመዝለል ሲሆን ራሷን ለማጥፋት ምክንያት የሆናትን ጉዳይ አልዘገበም። እንደ ድረገጹ ዘገባ የአሟሟቷ መንስኤ እየተጣራ ነው።
ራሷን አንቃ ገደለች የተባለችው ይህችው ኢትዮጵያዊት ፎቶ ግራፍ በድረገጹ ከመለቀቁ ውጭ ስሟ ያልተገለጸ ሲሆን አፍላጅ በሚባል የሳዑዲ አካባቢ የሚኖረው አሰሪዋ ሰራተኛው በመኝታ ክፍሏ ውስጥ ታንቃ እንዳገኛት ለፖሊስ መናገሩን ድረገጹ ጨምሮ ዘገቧል።
ጥቂቶች ሚሊዮን ዶላር የሚቆጥሩባትን፤ ሚሊዮኖች በረሃብ የሚቆሉባትን ኢትዮጵያን በሥራ አጥነት፣ በፖለቲካ ነፃነትና ድህነትን በመሸሽ ወደ አረብ ሃገራት የሚሄዱ ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን የማጥፋት ዜና አሁን አሁን እጅግ በጣም እየተለመደ መምጣቱ “ኢትዮጵያውያን መጨረሻችን ምን ይሆን?” ያስብላል።
የዚህችን ወጣት ጉዳይ ተከታትለን እንዘግባለን። አዲስ መረጃ እንዳገኘን እንመለሳለን።