የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ ከጳጉሜ 3 ጀምሮ በየሶስት ወሩ ሰልፍ እንደሚጠራ አስታወቀ

July 31, 2013

በመስከረም አያሌው

(ሰማያዊ ፓርቲ በቅርቡ ጠርቶት የነበረው ሰልፍ ሁሉንም ፓርቲዎች እያነቃቃ ነው። – ፎቶ ፋይል)
የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ ከጳጉሜ 3 ጀምሮ በየሶስት ወሩ ሰልፍ እንደሚጠራ አስታወቀ 1
ከጳጉሜ 3 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በየሶስት ወሩ በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚጠራ የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ) ገለፀ።
ባለፈው ሐሙስ “ያለ ብሔራዊ መግባባት እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትም ሆነ አስተማማኝ እድገት ሊመጣ አይችልም” በሚል መሪ ቃል በዋና ጽህፈት ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተገለፀው ፓርቲው በመጪው ጳጉሜ 3 ቀን 2005 ዓ.ም የመጀመሪያውን ሰላማዊ ሰልፍ በብሔራዊ መግባባት ላይ የሚያካሂድ ሲሆን በ2006 ዓ.ም ደግሞ በየሶስት ወሩ ተከታታይ እና በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ ሰላማዊ ሰልፎችን ለመጥራት አስቧል።
“ሰላማዊ ሰልፍ የምናካሂደው መንግስት የሰልፍ መብትን ሰለሰጠ ለመሽቀዳደም” አይደለም” ያሉት የፓርቲው ፕሬዝዳንት አቶ ተሻለ ሰብሮ፣ ይልቁንም ፕሮግራማቸው ከሁለት ዓመት በላይ የታሰበበት እድሜ ጠገብ አጀንዳ እንደሆነ ገልጸዋል። የሚካሄዱት ሰላማዊ ሰልፎች መንግስት የህዝቡን ጥያቄ አድምጦ እንዲመልስ እና ችግሮቹን እንዲፈታ ቅን እና ገንቢ በሆነ መንገድ ለማስጠንቀቅ መሆኑን የገለፁት አቶ ተሻለ፤ በሁለተኛነትም ሰልፉ ህዝቡ ችግር ከመድረሱ በፊት እንዲጠነቀቅ የማንቂያ ደወል ነው ብለዋል። ሰላማዊ ሰልፉም ሆነ ሌሎች ስብሰባዎችን የሚያደርጉት ህገ መንግስቱን በጠበቀ መልኩ እንደሆነ የገለፁት አቶ ተሻለ፤ መንግስትን ጨምሮ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በሰልፉ ላይ እንደሚሳተፉ ገልጸዋል። በጳጉሜው ሰላማዊ ሰልፍ ላይም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል።
በብሔራዊ መግባባት ላይ ጳጉሜ ላይ የሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ዋና ዓላማው ኢትዮጵያውያንን ወደ ተስማማ አንድነት ማምጣት መሆኑን የገለፁት የፓርቲው የማስታወቂያ እና ህዝብ ግንኙነት ባለሞያው አቶ ጌታቸው አበበ በበኩላቸው፤ ከባንዲራችን ጀምሮ ባለው ጥልቅ ልዩነት ምክንያት የሌሎች ሀገራት ዜጎች በቀላሉ የሚያገኟቸውን መብቶች እኛ ግን እንድናጣ እያደረገን ነው ብለዋል። በተለይ ብሔራዊ መግባባቱ ከመንግስት (ገዢው ፓርቲ) ጋር ብቻ ሳይሆን ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋርም ጭምር እንደሚሆን ገልጸዋል።
የፓርቲው ም/ፕሬዝዳንት እና የህግና ፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊው አቶ ተሾመ ወልደ ሀዋሪያት በበኩላቸው እድገትም ሆነ የኑሮ መሻሻሉ ሁለንተናዊ መግባባትን ያነገበ፣ ህዝቡን በእኩልነት ያካተተ መሆን እንዳለበት ገልጸው፤ ከመጪው 2007 ዓ.ም ምርጫም በፊትም እነዚህን ነገሮች መስመር ለማስያዝ ማቀዳቸውን ገልጸዋል። ፓርቲው የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ሁሉ የሀገሪቱን ህግና ደንብ ተከትለው የሚከናወኑ መሆናቸውን የገለፁት አቶ ተሾመ፤ ፓርቲው በቀጣዩ ዓመት ሊሰራቸው ከያዛቸው እቅዶች መካከል በየ3 ወሩ ሰላማዊ ሰልፍ እና የቤት ውስጥ ስብሰባዎች መካሄድ ዋናው መሆኑን ገልጸዋል። ሰላማዊ ሰልፉም ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በክፍለ ሀገርም ለማካሄድ መታቀዱን ጨምረው ገልጸዋል።¾

(ምንጭ፡-ሰንደቅ ጋዜጣ 8ኛ ዓመት ቁጥር 412 ረቡዕ ሐምሌ 24/2005)

Latest from Blog

ነገሩ እንዲህ ነው ባሳለፍነው ታህሳስ 15 በተካሄደው ብልጽግና ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ላይ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አረጋ ከበደ እጃቸውን አውጥተው ተናገሩ እኔ አቅቶኛል የአማራ ክልል ቀውስ ማስተዳደር አልቻልኩም ብለው ተናገሩ በዚህ ጊዜ

“አንተን ለማኝ አደርጋለሁ” አቢይ አሕመድ ለአማራ ክልል ፕረዚዳንት ለአረጋ ከበደ የሰጠው ማስጠንቀቂያ

January 31, 2025
ከቴዎድሮስ ሃይሌ የምናከብራቸው ጀነራል ተፈራ ማሞ ሰሞኑን አደባባይ ወጥተው አድምጠናል:: የጀነራሉ ጤንነትና ደህንነት ሲያሳስበን ለቆየነው ወገኖች ሁሉ በጥሩ ቁመና ላይ ሆነው በማግኘታችን የሕሊና እረፍት ሰጥቶናል:: አሁንም ባሉበት ሰላሞት እንዲበዛ ምኞታችን ዳር የለውም::

እስክንድር ነጋ እና ጀነራል ተፈራ ማሞ ከድል ለዲሞክራሲ እስከ ፉኖ ተሰማራ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ዛሬም እንደ ትናንቱ አያሌ ምሁራንና ታዋቂ ነን ባይዎች ስለብሔራዊ ሽምግልና እርቅ ይደሰኩራሉ፡፡ ያለምንም ሐፍረት ቅዱሱን ሽምግልናን ከምእራብ ከተሸመተው ኤፍሬም ይሳቃዊ ድርድር ጋር እያምታቱ የአያት የቅድመ አያቶቻችንን የተባረክ የሽምግልና ሐብት ያበላሻሉ፡፡ ሽምግልና በመለኮት

ፍትህ የሌለው ሽምግልናና እርቅ ሥራ እንደሌለው እምነት የሞተ ነው!

Go toTop