July 23, 2013
8 mins read

Sport: ሞውሪንሆ ፕሪሚየር ሊጉን ሊያመሰቃቅሉት ይችላሉ – (የስፖርት ተንታኞች አስተያየት)

jose mourinho 1812989c

የ2012/13 የውድድር ዘመን መገባደጃ በርካታ ክስተቶችን ያስተናገደ ነበር፡፡ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ከአሰልጣኝነት ጡረታ መውጣታቸውና በዴቪድ ሞዬስ መተካታቸው፡፡ ሮቤርቶ ማንቺኒ ከማንቸስተር ሲቲ የመሰናበቱ እንዲሁም የራፋ ቤኒቴዝ ከቼልሲ የሚለቁበት ቀን መቆረጡ አበይቶቹ ነበሩ፡፡ ክስተቶቹ እንደ ትልቅ ድግስ ነበሩ፡፡
በፕሪሚየር ሊጉ አዳዲስ አሰልጣኞች መጥተዋል፡፡ አዳዲሶቹ አሰልጣኞች በክለቦች ይሳካላቸው ይሆን? ማንንም ያስፈርማሉ? ማንን ያሰናብታሉ? ምን አይነት ውጤት ይገጥማቸዋል? የሚሉት ጥያቄዎች ይከተላሉ፡፡ የውድድር ዘመኑን መጠናቀቅ ተከትሎ መጪው 2013/14 ጥሩ የውድድር ዘመን እንደሚሆን በማሰብ ወደ እረፍት አቀናሁ፡፡ ነገር ግን ፔትር ቼክ በፕራግ ከሚገኝ አካዳሚው የሰጠውን ቃል መጠይቅ አነበብኩ፡፡ ቢዘገይም የሆነ ነገር እንዳስብ አደረገኝ፡፡ በቼልሲ ጆዜ ሞውሪንሆ በመመለሳቸው ምናልባት ሁኔታዎች ወደ ቀድሞ ቦታቸው ሊመለሱ ይችላሉ፡፡
የቼልሲው ግብ ጠባቂ ስለሞውሪንሆ መመለስ የገለፁባቸው ቃላት በ2013/14 ክፍት ፉክክር ይካሄድበታል ብዬ የሰነቅኩት ተስፋ ላይ ውሃ ቸልሶበታል፡፡ ‹‹ሞውሪንሆ አቻ ከመውጣት ይልቅ መሸነፍን የሚመርጥ አሰልጣኝ ነው፡፡ አንዳንዶች ማሸነፍ ካልቻልክ እንዳትሸነፍ ይላሉ፡፡ ሞውሪንሆ ጋር ግን ይህ አይሰራም፡፡ እርሱ የሚያስበው በትክክለኛው መንገድ ስለማሸነፍ ነው፡፡ ትክክለኛ የሚለው በማራኪ አጨዋወት ላይሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜያት መጥፎ ተጫውተህ ማሸነፍ ይኖርብሃል›› የሚለው ቼክ ማብራሪያውን በመቀጠል ‹‹በአካላዊ ጥንካሬ ላይ አመዝነው የሚጫወቱ ቡድኖች ሲገጥሙህ ለመፎካከር መንገድ መፈለግ አለብህ፡፡ በፕሪሚየር ሊጉ ቡድኖች የተለያየ አጨዋወት ዘይቤ ስለሚከተሉ ማራኪ አጨዋወት ለመተግበር የማይቻል ሊባል ይችላል፡፡ በትክክለኛ አካሄድ ማለት በታክቲኩ ረገድ በመዘጋጀት ተጋጣሚህን ማሸነፍ ነው፡፡ የምትችለውን እና ሲመለከቱት ማራኪ ያልሆነ እግርኳስን ልትጫወት ትችላለህ፡፡ ነገር ግን ዋንጫ ለማንሳት የግድ ማሸነፍ ይጠበቅብሃል፡፡ ትክክለኛው መንገድም ይኸው›› ይላል፡፡

ይህ የሞውሪንሆ አካሄድ ነው፡፡ ፕሪሚየር ሊጉን ሊያመሰቃቅሉት ይችላሉ፡፡ በቼልሲ ሌላ አሰልጣኝ አስቀምጣችሁ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን እስከ አምስተኛ የጨረሱ ቡድኖች ለዋንጫ ፉክክሩ ውስጥ እንደሚኖሩ መገመት ቀላል ነው፡፡ ቀደም ብዬ ፉክክሩ ክፍት ይሆናል ያልኩት በሊጉ እስከ አምስተኛ ባጠናቀቁት ቡድኖች መካከል ያለው ልዩነት ሰፊ አለመሆኑን ተከትሎ ነው፡፡ ባለፉት አምስት የውድድር ዘመናት በአንደኛውና አምስተኛ ሆኖ በጨረሰው ቡድን መካከል አማካይ የነጥብ ልዩነቱ 21 ነው፡፡
የሞውሪንሆ ሹመት ሲረጋገጥ የውይይቱ አብዛኛው ርዕስ በሰውየው ባህሪይ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ ምክንያቱም ጆዜ በ2004 ወደ እንግሊዝ ሲመጡ በስኬታቸው ተቀባይነታቸው አግኝቶ ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን የሞውሪንሆ ተቀባይነት ወርዷል፡፡ አሁን ልንጠብቅ የምንችለው ጠብ ፈላጊነታችንን ነው፡፡ የቼልሲ ደጋፊዎች ፖርቹጋላዊው እንዲመለሱ በጥብቅ ይፈልጉ ነበር፡፡ ሌሎች ግን በሰውዬው መመለስ እርግጠኛ አይደሉም፡፡
ስለሞውሪንሆ የምናስበው ለጥቃቅን ነገሮች ትልቅ ትኩረት የሚሰጡና ቡድናቸውን በጥንቃቄ የሚገነቡ አሰልጣኝ አድርገን ነው፡፡ ‹‹ሞውሪንሆ በዝግጅት ወቅት ለጥቃቅን ነገሮች ሰፊ ትኩረት ይሰጣል፡፡ ከአንተ ብዙ ነገር ይጠበቃል፡፡ በስሩ ያሉት የበለጠ ለመስራት እንዲነሳሱ ያደርጋል›› ሲል ቼክ የሞውሪንሆን አካሄድ ያብራራል፡፡ ጆዜ ስህተት ፈላጊ መሆናቸው ወደ ቼልሲ ለመመለስ ትክክለኛው ጊዜ ስለመሆኑ እጠራጠራለሁ፡፡
በፕሪሚየር ሊጉ ትልቅ ለውጥ አለ፡፡ በተለይ ባለፉት አንድና ሁለት የውድድር ዘመናት የቡድኖች መከላከል በአንፃራዊነት መዳከሙ ሊጉን እንድደሰትበት አድርጎኛል፡፡ ማንቸስተር ዩናይትድ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን 43 ጎሎች ተቆጥረውበታል፡፡ ከአምስት የውድድር ዘመናት በፊት ግን ዩናይትድ ያስተናገደው 22 ጎሎች ብቻ ነበር፡፡ ሬዲንግና ሳውዛምፕተን በ2012/13 በስታምፎርድ ብሪጅ እያንዳንዳቸው ሁለት ጎሎች አግብተዋል፡፡ ሞውሪንሆ የመጀመሪያ የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫቸውን ሲያነሱ በሜዳቸው የተቆጠሩባቸው ጎሎች ስድስት ብቻ ነበሩ፡፡ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን አርሰናል በሁለት ግጥሚያዎች ቶተንሃምን 5-2 ማሸነፍ ችሏል፡፡ ሞውሪንሆ ዳግም ወደ እንግሊዝ በመምጣታቸው ይህ የጎል ናዳ ማብቂያ ሊያገኝ ይችላል፡፡
ሞውሪንሆ ሁልጊዜ ጠንካራ ቡድን ከመስራታቸው ባሻገር ለማሸነፍ ያላቸው ተነሳሽነት ሌሎች ፍላጎታቸውን እንዲያልፉ ያደርጋቸዋል፡፡ በ2004 ሴፕቴምበር ላይ ጆዜ የቶተንሃሙን ጥብቅ መከላከል ቢተቹም በ2007 በኤፍኤካፑ ፍፃሜ ጨዋታ በሙሉ መከላከል ካሸነፉ በኋላ ከጨዋታው ይልቅ በድሉ መደሰት የበለጠ ይሻላል የሚል አስተየየት ሰጥተው ነበር፡፡ የሞውሪንሆ የማሸነፍ ድርሻ የላቀ ነው፡፡ በማድሪድ 72%፣ በኢንተር ሚላን 62%፣ በቼልሲ 67% እንዲሁም በፖርቶ 73% ነበር፡፡ ተፎካካሪዎቻቸው በራሳቸው መንገድ እየተጓዙ ባሉበት ወቅት ያልተጠበቀውን በመከወኑ በኩል ግን ሞውሪንሆ አስገራሚ ናቸው፡፡

(በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ላይ ታትሞ የወጣ)

Previous Story

‹‹ጋዜጠኞች ከእስር ቤት እንደወጡ በአንድ የፖለቲካ ድርጅት ጥላ ስር ሲሰባሰቡ መመልከት ያሳዝናል›› ዳዊት ከበደ [ጋዜጠኛ]

ask your doctor
Next Story

Health: በወሲብ ወቅት ብልቴን ያቃጥለኛል፣ ያመኛል፣ ይቆስላል፣ ይላላጣል

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop