የእናት ጡት ነካሾቹ ህወሃት ና ጀሌወቹ

ከብርሃኔ አሰበ አለሁድረስ

ከዛሬ 21 ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ህዝቦች ሁለንተናዊ ተሳትፎ ስልጣን የተቆናጠጠው ህወሃት/ወያኔ ገና ከጅምሩ የሃገርና የህዝብ ሃብትና ንብረት መዝረፍና ማውደም መለያ ባህሪው የሆነው የእናት ጡት ነካሹ ህወሃት በሆድ አደር ጀሌዎቹ ተባባሪነት እንሆ ለ21 ዓመታት የሃገራችንን ቁሳዊይና አካላዊ ሃብቶች እያራቆታት ይገኛል
ህወሃት/ወያኔ በ 17 አመታት የጫካ የሽፍትነት ዘመኑ በቀመረው ፀረ-ኢትዮጵያ የጫካ ሕጉ በትግል ጎራ ሳይቀር አብረወት ሲቆስሉና ሲዋደቁ ከነበሩት እውነተኛ ታጋዮች መካከል፣ በሃገራቸው አንድነትና ልኡላዊነት ላይ ጽኑ እምነት የነበራቸውን፣የኢትዮጵያ ህዝብ የስልጣን ባለቤት የሚሆንበትንና ዴሞክራሲ ስርአት በኢትዮጵያ መገንባት አለበት የሚል አቋም ያላቸውን እና የህዝብ ወገናዊነት የነበራቸን በየጊዜው በማሶገድ ፀረ-ኢትዮጵያ አቋም ያላቸው ሃይሎች ተሰባስበው ና ተማምለው እንሆ ዛሬ በአዝማቹ ህወሃት እና ከየብሄር ድርጅቱ ተወክለናል ባዮቹ ጀሌዎች በዚህ ትውልድ ላይም ለዜጎች መብትና ነጻነት የሚታገሉትን፣ በጹሁፍ ላይ የሰፈረው ሕገ መንግስት በተግባር ሊተገበር ይገባል የሚል ጥያቄ የሚያነሱ አካላትን፣ የህዝብ ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ምላሽ ሊያገኝ ይገባል በማለትጥያቄ የሚያነሱ የህብረተሰብ ክፍልን፣በሃይማኖታችን ጣልቃ አይገባብን፣በሃገራችን ሁላችንም እኩል ልንስተናገድ ይገባናል፣የሠብአዊ መብት ሊከበር ይገባል፣ የመሰብሰብና የመደራጀት መብታችን ሊገደብ አይገባውም ወዘተ በማለት ጥያቄ የሚያነሱ የህብረተሰብ ክፍሎችን አሸባሪ ፣ነውጠኛ፣ ሙሰኛ፣ የአመለካከት ችግር ያለበት ወዘተ በሚሉት ተለጣፊ ቃላቶቹ በመጠቀም ትውልዱን በመግደል፣ በማሰር፣ ከሃገር በማባረር እያመከነው ይገ ኛል
የዛሬ የእናት ጡት ነካሾቹ ህወሃት ማ! ያ- ን- ዬ በታጋይ ስም < ዴሞክራሲ ልናመጣልህ ነው የምንታገለው> በሚሉበት በዚያን ዘመን ደጉ ያገሬ ሰው የውስጥ የልባቸውን መርዝ ሳይረዳ የተባለለት ዴሞክራሲ ከፊቱ እየታየው ለተራበው በማጉረስ ፣ለተጠማው በማጠጣት፣መንገድ ለጠፋው መንገድ በማሳየት፣የተመታን ሸሽጎ ሂዎት በማትረፍ፣ገደል ፈንቅሎ መንገድ በመስራት፣ጅረት ጫካውን በማሻገር ፣ስንቅ ቋጥራ/ሮ/ ይቅናችሁ ብላ /ሎ/ ለመረቀ እናት/አባት፣እህት/ወንድም ህወሃት/ወያኔ በሃብት ላይ ሃብት አካብተው በዘረፉት ሃብት ደንዝዘው የህዝብን ጥያቄ ወደጎን ትተው ያ ሂዎታቸውን የታደጋቸውና ለድል ያበቃቸውን ህዝብ በፀረ-ዴሞክራሲ ህጋቸው መፈናፈኛ አሳጥተውታል ፥ ህዝቡይህንን ብሶቱን በንጉርጉሮ እንዲህ ሲገልጸው ይደመጣል
እሾህ ብቻ ሆኗል እግሬን ብዳብሰው
እንዴት መራመጃ መሄጃ ያጣል ሰው
ወ–ገ–ን በዚያን ዘመንታጋይ አይራብም ብላ ፈትፍታ ያጎረሰች እናት በኖረችበት ቀዬ /ቦታ/ ያረገዘችውን ልጅ እንኳን ሳትወልድ ቤንሻንጉል ጉምዝ አገርሽ አይደለም በሚል ከቤቷ ተፈናቅላ /ተገፍትራ /ጫካ ስትወልድ ዝምእንበል?
– የሃገር አለኝታ የሆነው አርሶ አደሩ ያ ትልቅ ሰው በግዳጅ ከ ቤንችማጅዞን ውጣ ሲባል ቤንችማጅዞን ሃገሬ ካልሆነማ ! ቀን ይሰጠኝ ሃብትና ንብረቴን ሰብስቤ እወጣለሁ ብሎ እጁን ዘርግቶ ሲማፀን እጣ ፋንታው ዱላ ሲሆን ምን እንፍጠር ? ምንእንበል ?
በሃገራችንና በህዝባችን ላይከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሰ የመጣውን የሰብአዊ መብትጥሰት፣ እየደረሰ ያለውን የሃገር ውድመትእና የሕዝባችንን ሰቆቃ ለመታደግ ይህንን እኩይ ስርዓት ማሶገድ አማራጭ የሌለው ተግባር ነው
በመሆኑም በየትኛውም ቦታ የምንገኝ የህዝባችን ሰቆቃና ስቃይ የሚቆረቁረን ኢትዮጵያዊ ሁሉ ልብ ለልብ ተገናኝተን ይህን ፀረ-ዴሞክራሲና ፀረ-ህዝባዊነት የተንሰራፋበትን ስርአት ሁለገብ ትግል ለማድረግ እንነሳ
ሁላችንም ለሃገራችን የድርሻችንን እናበርክት!
አዘጋጅ ብርሃኔ አሰበ አለሁድረስ
21/07/2013

ተጨማሪ ያንብቡ:  የዳዊት ጠጠር! (መብራቱ ከስቶክሆልም)

3 Comments

  1. you simply blame or you did not appricate the good work of woyanie`s, because today EPRDF is one of the democratic party but this is alergic for you like some bastard party of g7,olf , and others.may be you are one of this group because you comment nothing

  2. For Mr. Author..Birhane Assebe,

    I know you for long time when you were one of the useless EPRDF cadre. You were the one who was making your native people to suffer by making them not to get justice and more governmental services. YOU were the one who involved in stealing of the development of woredas(Menz keya).

    Mr.Birhane Assebe, do you remember that you were the one of Puppet of TPLF when largely populated Menz keya and Menz Gera were combined and made menz Keya be go backward for long time???? The most shamefull act you did was also…..when u were asked why the woreda was taken from menz keya…..you said it was the question of the people…….what a shameful answer i heard from you……how the people request to be taken the woreda to be some where far from it???……..

    Ye enat tut nekash ante tibeltaleh…….yanin ye tplf cadre honeh yebedelkewun hizb satikisew……….zare……feretetikina……”Wusha be belabet yichohal”………Ahun man gobez endilih new ende dehna sew(tiru endesera sew)….ye enat hager tiri akirabi……betam asafari sew neh…….

    It was because of you most outstanding students are living in the rural area beceuse you were making the conspiracy by taking the schools not to be opened and making the schools far from his/her area……..
    you were the one during that time when preparatory in North shoa to be only 3 ……made the number of outstanding students to break their education from grade 10……if u are really patriot, why didn’t you fight at that time??………..what ever the time it take, you are one of TPLF puppet who were making the development of your native woreda as well as N.shoa zone to be go behind for long time and the people will never forget including me………

    yante jerbah yetegetatebe silehone………opposition side honeh lemesadeb ayimechihim……arifeh tedebikeh nur……..yeserahew bizu gif alebih…….lemayawukuh nigerachew……

Comments are closed.

Share