July 20, 2013
14 mins read

ስለ ኮሎኔል ታደሰ ጥቂት ልበል፡ ከፍል1 በይታያል የሩቅሰው

ከፍል1
ይታያል የሩቅሰው

መነሻዬ ሰመረ ዓለሙ የተባሉ ሰው፡ ካቀረቡት ጽሁፍ መካከል፡ አንዱን በማንበቤ ስለተጠቃሹ ከማውቀው እውነት ጥቂት ቆንጥሪ
በሚከተሉት አርእዕስቶች በመክፈል፡ የነጠረውን ሀቅ እያነሳሁ አንድ ሁለት ለማለት ነው።

ስለዚህ

1/ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ፡ ምን ሰርቶ ነበር?

2/የመሰወሩ ምክናያቶችስ ምንና እነማን ናቸው?

3/እኛስ ስለ እሱ ምን ብለናል?

4/ወደፊትስ ምን ማለት አለብን?

የሚሉ ሃሳብና ጥያቄዎችን እያነሳሁ ባጭሩ ለመዳስ ልሞክር።

 ለዛሪ

1.1.ኮሎኔል ታደሰ ምን ሰርቶ ነበር፡

Colonel Tadesse Muluneh
ስለ ኮሎኔል ታደሰ ጥቂት ልበል፡ ከፍል1 በይታያል የሩቅሰው 1

ገና በለጋ እድሜው ዝነኛውን፡ የኢትዮጵያ አየር ሃይል የተቀላቀለው፡ ታደሰ ሙሉነህ በኮሌጁ የሚሰጠውን ትምህርት አጠናቅቆ፡ በምክትል፡ መቶ አለቅነት ማህረግ እንደተመረቀ ነበር፡ በሲያድባሪ የሚመራው የሶማሌ ተስፋፊ ጦር ኢትዮጵያን የወረረው፡ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ እንደሚያስታውሰው፡ ወቅቱ የሃይለስላሴ መንግስት፡ ወድቆ ደርግ ስልጣን የያዘበት ስለነበር ሀገራችን ለመከላከል የምታደርገውን እንቅስቃሴ፡ የሚደግፍላት ባልነበረበት ሁኔታላይ ስትሆን፡ ባንጻሩ ሶማልያ የረጅም ጊዜ የወረራ ዝግጅት ከማድረጓም በላይ ሶቬት እስካፍንጫዋ ያስታጠቀቻት በመሆኑ፡ በሁሉም ዘርፍ የእኛና የጠላት ሐይል አሰላልፍ፡ የሰማይና የመሪት ያክል፡ የተራራቀ ነበር ማለት ያስደፈራል።

ደርግ በአንድ በኩል ከምዕራባውያን መንግስታት መሳሪያ ለማግኘት፡ በሌላበኩል ወታደር መልምሎ በማሰልጠን ለውጊ ዝግጁ ለማድረግ፡ በሚሯሯጥበት ወቅት፡ የሶማሌ ታንክና ልዩ ልዩ ከባድ መሳሪያዎችን፡ የጫኑ በሺ የሚቆጠሩ፡ተሽከርካሪዎች ባይድዋ መድረሳቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ይደርሰዋል፡ ይህ ሃይል ወንዙን ከተሻገረ፡ ከአንድ ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ አዲስ አበባ ከመግባት የሚያግደው፡ ነገር እንደማይኖር ሰለሚገመት፡ ምንም እነኳን በተጠናከረ የአየር መቃወሚያና፡ እጅግ ዘመናዊ ተዋጊ አውሮፕላኖች የሚጠበቅ ቢሆንም፡ የተከፈለው ዋጋ ተከፍሎ ያ እንደጉንዳን የሚርመሰመስ ታንክና ከባድ መሳሪያ የጫነ መኪና ሳይሻገር፡ ድልድዩ መፍረስና ተመልሶ እስኪሰራ፡ ጥቂትም ቢሆን የዝግጅት ጊዜ መገኘት እንዳለበት፡ በባለስልጣናቱ ስለታመነ ለአየር ሃይላችን የውጊያ ትህዛዝ በመሰጠቱ፡ ግዳጁ ለም/ መቶ አለቃ ታደሰ ሙሉነህና ለበዛብህ ጴጥሮስ፡ በመሰጠቱ ወደ ቦታው ይከንፋሉ፡ በተጠንቀቅ ይጠባበቅ የነበረው የሶማሌ ወራሪም ገና በርቀት አየር መቃዎሚያውን ቢያስወነጭፍም፡ 2ቱ ጀግኖችና እውነተኛ የ ኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች፡በድፍረት ገስግሰው ተፈላጊውን ኢላማ መትተው ድልደዩን በማፍረስ፡ ፊታቸውን ወደሃገራቸው ሲያዞሩ ታደሰ ያበረው የነበረው ተዋጊ አውሮፕላን፡ በሶማሌ አየር መቃወሚያ በመመታቱ መንደድ ሲጀምር ወጣቱ ፓይለት በፓራሱት በመውረድ፡ በጉዞ ላየም ብዙ አስደናቂ ታሪኮችን እያከናወነ በጣም አስቸጋሪ ጉዞ በማድረግ፡ ኦጋዴን የሚገኜውን የወገን ጦር በመቀላቀሉ፡ የኢትዮጵያ ጀግና መዳሊያ የተሸለመ ከመሆኑም በላይ፡ከም/ መቶ አለቅነት አንድ ደረጃ በመዝለል የሻበልነት ማህረግ የተሰጠው፡ ጀግና ነው።

ኮሌኔል ታደሰ ሙሉነህ፡ ከዚያም በሗላ  በርካታ ሃገራዊ ግዳጆችን የተወጣና ጠቃሚ ቁም ነገሮችን ያከናወነ፣ በትምህርት ዝግጅቱም የ2ኛ ዲግሪውን በማዕረግ ያጠናቀቀ፡ ፍጹም ሐገር ወዳድ፣ቅንና እሩህ ሩህ፣ አርቆ አስተዋይ፡ ባጠቃላይ እንከን የለሽ ስብናን የተጎናጸፈ፡ ሲሆን ወያኔ ኢትዮጵያን ሲቆጣጠር፡ የጠላትን ፊት ላለማየት፡ ከድሪድዋ አውሮፕላን አስነስተው፡ ኬንያ ከገቡት የአየር ሃይል አብራሪዎቻችን አንዱ ነበር።

ከዚያም የሀገሩ ውድቀት የእግር እሳት የሆነበት፡ ኮሎኔል ታደሰ ኬንያ እየኖረ የፖለቲካ እንቅስቃሴ፡ ለማካሄድ ሲጀምር ሁኔታዎች ለህይወቱ አድገኛ ሆነው ስላገኛቸው፡ የተሻለ ከለላ ለማግኘት ባደረገው ጥረት የዑጋንዳ ባለስልጣናትን አነጋግሮ ባገኜው ይሁንታ መሰረት ወደዚያው ሄዶ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንዳለ፡ የወያኔና የሻብያ ግንኙነት፡ በመበላሽት ላይ እንደሆነና፡ ሻብያ ወያኔን በጦር ሃይል ለማበርከክ፡ ሚስጥራዊ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ፡ በአንድ የድሮ የኢትዮጵያ አየር ሃይል ባልደረባና ኤርትራ ከተገነጠለች በሗላ የኤርትራ ባለስልጣን በሆነ ግለሰብ፡ ይነግረውና፡ ኢትዮጵያን ከወያኔ ነጻ የማውጣት እቅዱን በኤርትራ በኩል ቢያደርግ እንደሚሻል ያግባባዋል፡፡

ኮሎኔል ታደሰም፡ የጠላቴ ጠላት የእኔ ወዳጄ ነው ወይንም ጅብን ለመውጋት አህያን መጠጋት እንዲሉ፡ ከስልት አንጻር ከዚህ የተሻለ ቦታ የለም በማለት፡ ጥያቄውን ተቀብሎ ወደኤርትራ በማምራት የሃገሪቱን መሪ በአካል አግኝቶ ሲያነጋግር፡ ሁኔታወች እስኪመቻቹልህ ድረስ፡ የኤርትራ ተዋጊጀት አብራሪዎችን ሲያሰለጥን እንዲቆይ፡ ትብብር ስለተጠየቀ እሽ ብሎ እያሰለጠነ  ለሁለት አመት ያህል እንደቆዬ፡ ወያኔ ሳያስበው፣ ሻብያ ግን ከ3አመት ባለነሰ ዝግጅት ጦርነቱ በሻብያ ተንኳሽነት ይፈነዳል።

ይህነን ተከትሎ ደግሞ በኬንያም፣ በሱዳንም፣ በሃገር ቤትም፡ ይንቀሳቀሱ የነበሩ፡ የወያኔ ተቃዋሚዎች ኤርትራ ገብተው፡ ከእዚያ እየተንደረደሩ ወያኔን መውጋት ይችሉ ዘንድ፡ ለኤርትራ መንግስት ጠያቄ አቅርበው ስለተፈቀደላቸው፡ ጠቅልለው እንደገቡ   ከኦነግና ከኦቭነግ በቀር፡ ሌሎቹ ግንባር ፈጥረው በአንድ ድርጅት ጥላ ስር በመሰባሰብ ለውጊያ እንዲዘጋጁ፡ በሻብያ መመሪያ ስለተሰጣቸው፣

1ኛ/በአቶ ዮሴፍ ያዘው፡ ይመራ የነበረው፡ የኢትዮጵያ ህዝቦች ዲሞክራ ግንባር፡

2ኛ/በአቶ ተስፋዬ ጌታቸው ይመራ የነበረው፡ የኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ንቅናቄ፡

3ኛ/በአቶ ቱሗት ፖል ይመራ የነበረው፡ የኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ግንባር፡

4ኛ/በአቶ ጁማ እሩፋኤል ይመራ የነበረው፡ የቤንሻንጉል ንቅናቄ፡ በጋራ ባደረጉት የውህደት ጉባኤ ላይ ኮሉኔል ታደሰ ሙሉነህም ተካፋይ እንዲሆን ትደርጎ ስለነበር፡ ተዋህደው አዲሱን ድርጅት የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር የሚል ስያሜ በመስጠት የመጀመሪያ ጉባያቸውን ሲያጠናቅቁ፡

1ኛ/ ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህን፡ የግንባሩ ሊቀመንበር፡

2ኛ/ አቶ ቱሗት ፖልን፡ የግንባሩ ም/ሊቀመንበረ፡

3ኛ/አቶ ጁማ እሩፋኤልን የግንባሩ ጽሃፊ፡

4ኛ/አቶ ዮሴፍ ያዘውን የግንባሩ ድርጅት ጉዳይ፡

5ኛ/አቶ ተሰፋዬ ጌታቸውን የግንባሩ የእርዕዮታለም ጉዳይና ሌሎች 2 ሰወችን በማከል፡ 7 ያመራር አካላትን መርጠው ነበር። ኮሎኔል ታደሰ ያካበተውን የጠለቀ እውቀትና ሰፊ የስራ ልም፡ ሳይሰስት ተግባር ላይ ስላዋለው፡ አርበኛ ግንባር ባጭር ጊዜ በብዛትም ሆነ በጥራት ጠላቱን ወያኔን ብቻ ሳይሆን፡ አስተናጋጇን  የኤርትራን መንግስትም፡ ከማስፈራት ደረጃ ላይ ከመድረሱም በላይ፡ በዲፕሎማሲውም ዘርፍ ኮሎነል ታደሰ ወደ አውሮፓና አሜሪካን በመጓዝ፡ ኢትዮጵያውያንንና የውጭ ሀገር መንግስታትን፡ አነጋግሮ በማሳመን ሰፊ ድጋፍን ያስገኘ ሰው ነው።

ኮሎኔል ታደሰ ወደ አሜሪካን ባቀናበት ወቅት፡ሻብያን በጥርጣሪ አይን የሚያዩ፡ ኢትዮጵያውያን፡ ተሰባስበው መኝታ ክፍሉ ድረስ በመሄድ፡ በሻብያ ድጋፍ ኢትዮጵያ ነጻ ትወጣለች ብለህ አትድከም ይልቅ፡ ሻብያ እንደበግ አስብቶ ሳያርድህ፡ አሁን እንደወጣህ በእዚሁ ቅርና ልጆችህን አሳድግ፣ ሚስትህም፡ ኢትዮጵያም ያንተ ብቻ አይደለችም፡ ወ.ዘ.ተ. በማለት ቢለምኑት፡ የሰጣቸው መልስ፡ ሁሉም ኢዮትጵያ ለእኔብቻ አይደለችም፡ እያለ ጥሏት ከሸሸ የጎርቤት ሀገር ዜጋ መጥቶ ሊታደጋት ነውን? ባለቤቴም ሆኑ ልጆቸ አሜሪካን ገብተዋል፡ የተሻለ ኑሮ እየኖሩ ነው ወደፊትም ቢሆን እኔ ኖረሁም አልኖርሁም ይኖራሉ፡ ሌላው ኢትዮጵያዊ ግን ይህንን እድል ማግኘት አይደለም በሀገሩ ላይ በሰላም የመኖር መብቱ ተገፍፎ 2ኛ ዜጋ ሆኖ በመማቀቅ ላይ ከመሆኑም በቀር፡ ወያኔ ውሎ ካደረ ኢትዮጵያ የምትባል ሃአገር አትኖርም፡ እናም ቢሆን ከጥፋት አድናታለሁ፡ ካልሆነም ጥፋቷን ሳላይ ማንም ያጥፋኝ ማን ስከላከልላት እኔ ቀድሜያት፡ እጠፋለሁ፡ ሞት እንደሁ ፈራንም ደፈርን የማይቀር የተፈጥሮ እዳችን ነው። የሚል እንደነበር ካነጋገሩት ሰዎች መካከል አንዱ ሰሞኑን በቁጭት አጫውተውኛል።

ለዛሪ በዚህ ላብቃ ቀሪውን በክፍል ሁለት ሳምንት እመለስበታለሁ፡ የሳምንት ሰው ይበለን፡

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይታደጋት አሜን!!!!

                                                          

 

Latest from Blog

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop