በዋልድባ ገዳም የሚገኘው የስኳር ፕሮጀክት ነዳጅ ማራገፊያ የመሬት መንሸራተት አጋጠመው

July 16, 2013

የዋልድባ ገዳም አባቶች የድረሱልኝ ጥሪያቸውን ያሰማሉ
በዋልድባ ገዳም የሚገኘው የስኳር ፕሮጀክት ነዳጅ ማራገፊያ የመሬት መንሸራተት አጋጠመው 1
“በዋልድባ ገዳም የሚገኘው የስኳር ፕሮጀክት ነዳጅ ማራገፊያ የመሬት መንሸራተት አጋጠመው” አንድአድርገን የተሰኘው ሃይማኖታዊ ድረ-ገጽ ዘገበ።
ድረ ገጹ ዛሬ ባሰራጨው ዜና “መንግስት እገነባቸዋለሁ ካላቸው የስኳር ፋብሪካዎች ውስጥ ብዙ ውዝግብ ያስነሳው ፤ ብዙ ዋጋ ያስከፈለው አሁንም እያስከፈለ ካለው የሥኳር ፋብሪካ ውስጥ በዋልድባ ገዳም የሚገነባው አንዱ ነው፡፡ እነዚህን ፕሮጀክቶች በበላይነት የሚመራው መቀመጫው መሀል ካሳንቺስ ያደረገው በአቶ አባይ ጸሀዬ የሚመራው የስኳር ኮርፖሬሽን መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከፕሮጀክቶቹ አንዱ እና ዋንኛው የሆነውን የዋልድባን የስኳር ፋብሪካ ግንባታን በመቃወም ብዙ መነኮሳት ከበአታቸው በመሰደድ በያሉበት ሆነው ስራውን እየተቃወሙ ይገኛሉ ፤ ፕሮጀክቱን ለመስራት በየጊዜው የሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የመጡ ኮንትራክተሮች ውል በመቋጠር እንደገና በመፍታት አሁን ላይ ሶስተኛው ስራ ተቋራጭ ስራው እያካሄደ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡” ብሏል።

አንድ አድርገን ዘገባውን በመቀጠል መንግሥት በትላልቅ ፕሮጀክቶች ስራቸው እንዳይተጓጎል ለማድረግ ከየትኛውም ፕሮጀክቶች በተለየ መልኩ ከብሔራዊ ነዳጅ ማከማቻ ጋር የተለየ ውል መያዙን የውስጥ ሰዎች ይገልጻሉ ፤ ለአንድም ቀን ይሁን እነዚህ ፕሮጀክቶች ላይ የሚሰሩ መኪናዎችና የተለያዩ በነዳጅ የሚሰሩ መሳሪያዎች ስራቸው እንዳይስተጓጎል በመጀመሪያ ደረጃ በተለየ ምልከታ የነዳጅ ፍላጎታቸው በየጊዜው እንደሚቀርብላቸው ምንጮች ያስረዳሉ፡፡ ብሏል።

“ከሳምንታት በፊት በዋልድባ ገዳም እየተሰራ ለሚገኝው የሥኳር ልማት ፕሮጀክት አንድ ከነተሳቢው ነዳጅ የጫነ መኪና ከአዲስ አበባ ወደ ዋልድባ የጫነውን ነዳጅ ለማራገፍ ወደ ቦታው ያመራል ፤ ቦታው ላይም ነዳጅ የጫነው መኪና በጊዜው መድረስ ችሎ ነበር ፤ ነገር ግን ነዳጅ የጫነው መኪና በጊዜው ቢደርስም ነዳጁን ለማራገፍ በሚሞክርበት ጊዜ ከመሬት ስር የተቀበረው ነዳጅ ማራገፊያ በመሬት መንሸራተት ምክንያት ከዋናው ቦታ መሸሹን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚህ ምክንያትም ነዳጁን የያዘው መኪና በመሬት መንሸራተት ምክንያት ቦታውን ያጣውን ነዳጅ ማከማቻ ወደ ቦታው የመመለስ ስራ እስኪሰራ እና ለመገልበጥ ሁኔታዎች እስኪመቻቹ ድረስ ለ21 ቀናት በቦታው ላይ መቆሙን ለማወቅ ተችሏል፡፡” ያለው ድረገጹ እግዚአብሔር በአንድም በሌላም መንገድ ይናገራል ፤ በዋልድባ ከፕሮጀክቶቹ ጋር ተያይዙ ብዙ ምልክቶች እየታዩ ይገኛሉ ፤ ላስተዋለ አንድም ምልክት በቂ ነበር ላላስተዋለ እንደ ፈርኦን አስራ አንድ ምልክት ቢከታተል ልቡ ደንድኗልና የመጨረሻውን ምልክት እስከሚያይ ድረስ ፤ ባሕረ ኤርትራ ተከፍቶ እስኪውጠው ድረስ ከጥፋት ስራው ሊመለስ አይችልም ፤ መጽሀፉ ‹‹ ማንም የቆመ ቢመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ›› ይላል” ሲል ምክሩን አጠናቋል።

Latest from Blog

ነገሩ እንዲህ ነው ባሳለፍነው ታህሳስ 15 በተካሄደው ብልጽግና ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ላይ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አረጋ ከበደ እጃቸውን አውጥተው ተናገሩ እኔ አቅቶኛል የአማራ ክልል ቀውስ ማስተዳደር አልቻልኩም ብለው ተናገሩ በዚህ ጊዜ

“አንተን ለማኝ አደርጋለሁ” አቢይ አሕመድ ለአማራ ክልል ፕረዚዳንት ለአረጋ ከበደ የሰጠው ማስጠንቀቂያ

January 31, 2025
ከቴዎድሮስ ሃይሌ የምናከብራቸው ጀነራል ተፈራ ማሞ ሰሞኑን አደባባይ ወጥተው አድምጠናል:: የጀነራሉ ጤንነትና ደህንነት ሲያሳስበን ለቆየነው ወገኖች ሁሉ በጥሩ ቁመና ላይ ሆነው በማግኘታችን የሕሊና እረፍት ሰጥቶናል:: አሁንም ባሉበት ሰላሞት እንዲበዛ ምኞታችን ዳር የለውም::

እስክንድር ነጋ እና ጀነራል ተፈራ ማሞ ከድል ለዲሞክራሲ እስከ ፉኖ ተሰማራ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ዛሬም እንደ ትናንቱ አያሌ ምሁራንና ታዋቂ ነን ባይዎች ስለብሔራዊ ሽምግልና እርቅ ይደሰኩራሉ፡፡ ያለምንም ሐፍረት ቅዱሱን ሽምግልናን ከምእራብ ከተሸመተው ኤፍሬም ይሳቃዊ ድርድር ጋር እያምታቱ የአያት የቅድመ አያቶቻችንን የተባረክ የሽምግልና ሐብት ያበላሻሉ፡፡ ሽምግልና በመለኮት

ፍትህ የሌለው ሽምግልናና እርቅ ሥራ እንደሌለው እምነት የሞተ ነው!

Go toTop