(ዘ-ሐበሻ)የአውራምባ ታይምሱ ዳዊት ከበደ ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከአቶ ግርማ ብሩና ከሌሎች የኤምባሲው ሃላፊዎች ጋር ረጅም ሰዓት የፈጀ ውይይት ማድረጉን ከኤምባሲ አከባቢ የተገኘ መረጃ አጋለጠ።
የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች እንዳጋለጡት ዛሬ ጁላይ 8 ከቀኑ 4pm ጀምሮ ዳዊት በኤምባሲው ቅጥር ግቢ ተገኝቶ ውይይት ያደረገው ስለምን እንደነበረ ባይታወቅም በድምጻዊ ሰለሞን ተካልኝ ምትክ ወያኔ ለመክፈት ላቀደው ሬዲዮ እንዲያዘጋጅ ሊሆን እንደሚችል የኤምባሲው ምንጭ ያለውን ግምት ገልጿል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይም የገዢውን ፓርቲ የሚያስደስቱ ቪድዮችን በመልቀቅ ከትግራይ ኦንላይን እና ከአይጋ ፎረም የማይተናነስ ገዢውን ፓርቲ የሚያስደስቱ ሥራዎችን እየሰራ ነው በሚል የሚተቸው ዳዊት ከበደ በኢትዮጵያ ኢምባሲ ከአቶ ግርማ ብሩ ጋር ከመገናኘቱ አስቀድሞ በቅርብ ወደ አሜሪካ ለአባይ ግድብ ጉዳይ መጥተው ያልተሳካ የገንዘብ ማሰባሰብ ካካሄዱት የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቴዎሮስ አድሃኖም ጋርም በስልክ መገናኘቱን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል።
የአውራምባ ታይምሱ ዳዊት ከበደ በዲያስፖራው የሚገኙ የነፃው ፕሬስ ሚዲያዎችን በማጥቃት እየተወነጀለ እንደሚገኝ በተለያዩ የማህበራዊ ድረገጾች ከሚሰጡ አስተያየቶች መረዳት ተችሏል።