ክብሪት የሚጠብቀው የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮት – (በያሬድ አይቼህ)

በያሬድ አይቼህ ፥ ጁላይ 5፥2013

በቱኒዚያው ህዝባዊ ንቅናቄ የተጀመረው የአረቡ ህዝብ ቁጣ ፡ እንደገና ሌላ የግብጽ ፕሬዘደንት ከስልጣን ገፍትሮ ጣለ። በቲኑዚያ የተጫረው ፡ የሊቢያውን ጋዳፊ አቃጥሎ ፡ የየመኑን ፕሬዘዳነት አባሮ ፤ አሁንም በሶርያ እየነደደ ነው። ይሄንን ሁሉ የህዝብ ቁጣ የጫረው አንድ ጥፊ ነበር። አዎ! ጥፊ።

በአገራችንም የሚጭረው ክብሪት የሚጠብቅ ህዝባዊ የነጻነት የፍትህና የዴሞክራሲ አብዮት እያጉረመረመ ነው።

ጉዳዩ እንዲህ ነው። በ2011 ቱኒዚያዊው የኮሌጅ ምሩቅ ወጣት መሃመድ ቦአዚዚ 8 የሚሆኑ ቤተሰቦቹን እና ዘመዶቹን የሚያስተዳድርበት ገቢ ሚያገኝበትን የፍራፍሬ ጋሪ ፓሊስ ያግትበታል። መሃመድ መክፈል የነበረበትን ክፍያ ከፍሎ የፍራፍሬ መሸጫ ጋሪውን ሊያስለቅቅ ሲሞክር ፓሊሱ ፡ የመሃመድን ሟች አባቱን ሰድቦ ፡ በጥፊ ጭው ያረገዋል።

መሃመድ ከተሰማው ጥልቅ ውርደትና ሰሚ ማጣት የተነሳ ሰውነቱ ላይ ነዳጅ አርከፍክፎ ራሱን ያቃጥላል። የመሃመድን አበሳ የሰሙ ቱኒዝያውያን የኑሮ ውድነት ፡ ከፍተኛ ስራአጥነት ፡ የምግብ ዋጋ መናር ፡ የመናገር ነጻነት መነፈግና ሌሎች የፓለቲካ ጭቆናዎች የተነሳ ቁጣቸው ገነፈለ። ቁጣቸው ቤን አሊን ከ23 ዓመት ስልጣን ላይ ነቅሎ ከአገር አባረረው። ይህ ሁሉ የጫረችው ያች ጥፊ ናት።

ያች ጥፊ ናት ቤን አሊን ጭው ፡ ሙባረክን ጭው ፡ ጋዳፊን ጭው ፡ አሁን ደሞ ሙርሲንም ጭው ያደረገቻቸው። ጥፊዋ ለሁለት አመታት የሶርያውን ባሻርን ጭው ፡ ጭው እያደረገችው ትገኛለች። አብዮታዊ ጥፊዋ ወደ አገራችን ለመግባት እያንዣበበች ይመስለኛል።

ህዝባችን በኑሮ ውድነት ታይቶ በማይታወቅ መንገድ እየተንገላታ ፡ በሙስና የተዘፈቀ አመባገነናዊ ፋሽስት መንግስት እያሰቃየው ፡ የፈለገውን እያሰረ ፡ የፈለገውን እየገደለ ፡ የፈለገውን ከመሬት እያፈናቀለ ፤ የሙስሊሙ የሃይማኖት ነጻነት ተደፍሮ ፡ የክርስትያኑን ሱኖዶስ ከፋፍሎ ፤ የፓለቲካ ምህዳሩን ዘግቶ በምንገኝበት በዚህ ወቅት ክብሪት ከየት ይመጣ ይሆን?

ክብሪት የሚጠብቀው ህዝባዊ የነጻነት ፡ የፍትህ እና የዴሞክራሲ አብዮት በኢትዮጵያ ሚፈነዳበት ጊዜው እየተቃረበ ነው።

ማን ይሆን የኢትዮጵያን ህዝባዊ የነጻነት አብዮት የሚጭረው? ታሪክና ትውልድ በጉጉት እየጠበቀ ነው።

– – – –

ጸሃፊውን ለማግኘት፦ yared_to_the_point@yahoo.com

10 Comments

 1. Because they are in a very shock condition following the diversion of political land scape over flooded egypt which is wiping out Islamic brotherhood and its companies. The political dynamics has no mercy at all. Face the inevitably.

  • Hi, yared Ayecheh, are you mad? you are fly yogerte.I do not under stand your stand . one time you supportband you insulted Ethiopian peopel.To day also you seems to be an Ethiopian. you are double face .I told you we lived the same city. I know you very well. you are TPLF spy. and cadere.. Please do not insultede people . one day we will get freedom and democracy. we Ethiopian srtugle to faildown the Aprtide dictatorial authority. i am sure you will see and I plan to speak about you in the media. I will call you that day.

 2. Lij Tesfaye G/Ab,

  Your style of writing is too unique to be confused with others. It is likable, concise and to the point as you also proclaimed it in your mail address. But now, why are you using this pseudo-name of Yared Ayicheh given the fact that you are not operating from Ethiopia? As a fugitive journalist living abroad, you could have revealed your true name without fear. By doing so, you would primarily be honest to your profession and secondly to your readers.

  From what I could tell of your short articles, they are more of propaganda pieces than informative journalistic works. Let us, for example, consider your article recently written about Jawar Mohammed. Through that article, you portrayed yourself as an Amhara, who is eloquent in Amharic and who strongly support the self determination of Oromiya up to cessation with the objective of confusing Amharas and agitating pro-Ethiopia Oromos and other tribes to join the defunct old-styled politics of OLF. You show your inexplicable disdain to Amharas, whose language you speak and use excellently, perhaps much better than the natives themselves. By doing these things, you are helping the woyanes, whom you appear to despise since your run away and whose main job is to drive wedges through hair cracks, in order to foment suspicion and hatred among the ethnically diversified Ethiopians along ethnic and religious lines.

  My question to you: what do you really gain by assisting the evil notions of Woyane/Shabia to throw the people of this big East African region into chaos and turmoil?

  As a journalist, there are a lot of noble causes you could have supported instead of working day and night to foment hatred among people regardless of their ethnicity and faith. My brotherly advice to you is to stop such activities for a while and think twice without prejudice. It is not too late for for redemption and a change of stance. You have the capacity to do much nobler works than what you are doing now. Please do not let even a single soul suffer from distorted outlooks.

  My brother, if you, as a remote possibility, did not understand what you are doing, I would like to tell you that you are playing with fire that has the capacity to ravage the entire region.

  While acknowledging the relevance and timeliness of this particular short article of yours about the ever likely upcoming revolution in Ethiopia, I want you also to understand how a huge fire can easily be kindled. Compare yourself to Mohammed Bouazizi: his fire is consuming dictators possibly not to come again in the form we have known them while liberating hundreds of millions from their tyrannical grips, and yours is a fire that has the potential to consume millions of innocent citizens paving the way to long-lasting chaos and anarchy.

  I pray to God to give you the wisdom to repent and do good in place of bad.

 3. Who are you after all to say so? Why don’t you be M.Boaziz of Ethiopia?mere instigation? Our life by itself is instigating us! Don’t wish(and it is impossible) to put youths in to fire!

  In addition I have read your previous article(which advocates that Ethiopia is ins very good situation)!

  Better to get into hell with your wish for revolution(in Ethiopia)! After all you have no clear position!!

 4. እኔ፡እንደገባኝ፡ክብሪቶቹ፡ትንንሽ፡ሆኑእንጅ፡በሁሉም፡ሰዉ፡እጅና፡ኪስ፡ዉስጥ፡አለ፡በቤተእምነቶች፡ዉስጥ፡አለ፡በየቀኑ፡በተናጠል፡ይለኮሳሉ፡የሚያቃጥሉት፡ግን፡ግፋቢል፡ራሳቸዉን፡ነዉ፡፡ምናለ፡ሰብሰብ፡ቢያደርጉት፡መሰብሰብ፡እንዳለበት፡ሁሉም፡ይስማማል፡ግን፡እኮ፡ሰብሳቢ፡ያስፈልገዋል፡እንዴት፡መሰብሰብናየትና፡መቼ፡ከየት፡ጀምሮ፡መቃጠልም፡እንዳለበት፡ስለወደፊቱ፡ራእይም፡መነጋገርም፡መግባባትም፡መተማመንም፡እንዲሁ፡ያስፈልጋል።

 5. You are a piece of shit I read the crap you wrote supporting JAWAR the supporter of the criminal and genocidal party OLF and anybody who support JAWAR is stupid And sick racist dude please your writings are shallow and stupid please read read a good writer has to be a good reader and it seems that u need a lot of reading

 6. ፩) ያሬድ ሰው ሆነህ አይቼህ! ‘ቤቲ አዋረደችን!’ የኢትዮጵያን ህዝብ ለመሆኑ ክብር አለው ?ከየት ወዴት ነው የወረደው? ይህ ችጋራም፣ ድሃ፣ ህዝብ! ስትል የኢትዮጵያን ሕዝብ ኋላቀር፣ደንቆሮ፣ መንጋ አስተሳሰብ ያለው፣ “ብቻውን የበላ ብቻውን ይሞታል” የሚል የድሃ አስተሳሰብ ያለው እያልክ አጋጣሚውን ተጠቅምህ ግብረሰዶማይነትን ስትሰብክ ባህልን፣ ሕዝብን፣ በዘሁ ድረገፅ ስታዋርድ ነበር።( ህዘብ አንብቦ ይፍረድ!)

  ፪) ” የአማራ ሊሂቃን እና ጃዋር መሃመድ” ስትል እራስህን አማራ ለመሆን ዕድሜህን ሙሉ የምትመኝ ግን ያልተሳካልህ መሃይም የብሔር ብሄረሰብ የመለስ ኮብል እስቶን መሆንህን ነገርከን።የአማራ ደንቆሮ ለመሆን ይሆን? የመንገድ ላይ ማደጎ ሁሉ አማራ ነኝ ካለ አማራ ቤት ያደገ ውሻ ምን ይበል? ተስፋዬ ገብረእባብ ከነጋሱ ጊዳዳ፣ ከቡልቻ ደመቅሳ፣ከመራራ ጉዲና በለጠ ጆሌ ቢሸፍቱ ሲቲዚኒ ኦሮሞያ ነኝ ብሎ የለምን? … “ጋኖች አለቁና ምንቸቶች ጋን ሆኑ” አለ ይህ አንድ የጥርብ ድንጋይ መሆናችሁን ለማሳየት ተወሰደ ነው። ለምሳሌ ያሬድ ግለሰብ ነፃነት ይልና ‘እኛ አማራዎች’ ይላል እንዲህ ያለ አማራ በዘር ሳይሆን የአማራ እንጨት ፈላጭ፣እረኛ ወይም ዘበኛ የተሻለ አማርኛ ይናገራል። እዚህ ላይ የትግሬ ተወላጅ (እግዝሐብሔር ጨርሶ ይማረውና ) አስመላሽ የተባለ ቀልደኛ ትዝ አለኝ ” አንተ አማራ አደለህም የምትናገረው የአማርኛ ዘይቤ የመንዝ ‘ነው ቢሉት…ተወልጄ ያደኩት በአዲስ አባባ ሰሜኑ ክፍል በእንጦጦ አካባቢ ነው መንዜዎች በዚህ ተራራ ላይ በግ ሊሸጡ ሲመጡ ሌላው ገንዘብና በግ ሲሠርቃቸው እኔ ግን አማርኛ እሰርቃቸው “ነበር አለ። ለመሆኑ አማርኛ ቋንቋና ኢትዮጵያዊነት በትግሬው ላይ በግድ ተጭኖበት ነበር። እንዴት በጅዋር መሀመድ ላይ ብቻ ተጫነበትና ያሬድ ቂጡን ቆላ? ለመሆኑ የመማር እድል በኢትዮጵያ የተነፈገ ኦሮሞ አልጀዚራ ላይ ለመሞላፈጥ ቻለ?ለምሳሌ በዛን ዘመን አማርኛ ሳይናገሩ ከትምህርት ቤት የተባረሩት አቶ ሽፈራሁ ሽጉጤ አሁን አቶ ኅይለማርያም ደስአለኝ ቂጥ ከወነወጅል ለማምለጥ ሊሸጎጡና በትምህርት ሚ/ር ሚኒስትር ማዕረግ ሊሾሙ አማርኛ የተማሩትና ለዚህ የበቁት በኢህዴግ ዘመን ተወልደው አድገው እንግሊዘኛ ተመርቀው ነው ወይንስ በክልላቸው ቋንቋ ውጭ ሀገር ተምረው ነው ማለት ይሆን? ። በለው መቀሳፈት!

  ፫) ያሬድ አይቼህ ኦሮሞውን አባመላንና ትግሬውን ዳዊት ከበደን ተቸ!? በለው! “አመድ በዱቄት ይስቃል” አሉ።

  ፬) “ክብሪት የሚጠብቀው የኢትዮጵያ አብዮት? የት ሀገር? ለምን? በማን? የሆድ አደርና የአድርባይ አብዮት ሌባ አቁፋዳ ይዞ በተቦካበት መቅፈፍ ! አለዚያም መዝረፍ! ከዳር ቆማችሁ እንድንበጣበጥ የድሃን ልጅ የሥልጣን መወጣጫ ለማድረግ ለምትሹ ዘረኞች፣ ገንጣይና ከፋፋይ፣የሚሲዮኖች የፋፋና የወተት ዱቄት በአፋችሁ የሚቦንባችሁ ሁሉ፤ እንኳን ክብሪት አንስተን ሀገርና ህዝብ አንጎዳም ቢቻል እናንተን የእሳት እራት እንድትሆኑ እየኮረኮርን ዓላማችሁን ማስተፋት …ግን አንተንና በሐሳብ የደገፍካቸው ወሮበሎች(ልሂቃን) መቃጠል ከፈለጋችሁ እኔ በሙሉ ፈቃደኝነት(ያለወጪ) እረዳችኋለሁ። ኖራችሁም ቦታ ከማጣበብ፣ ከርሳችሁን ከመሙላት፣ ሕዝብን ከማባላት፣ የነጭ አክታ ልሳችሁ እንደገና ትውልድ ላይ ከመትፋት በቀር ለምንም አትጠቅሙም! አጭበርባሪ ይውደም !ይቃጠል! የህዝብን መቃጠል የሚጠብቁ ፀብ አጫሪዎችና አጋጣሚውን ለመጠቀም ያሰፈሰፉ ሸቃዮች ናቸው በለው!ከሀገረ ካናዳ በቸር ይግጠመን

 7. Dear Workamaw,
  I agree with your comment please dont jump in to conclusion by saying Tesafaye.how do you know him.if some body say on the comment this is tesfaye don’t conclude like that.

Comments are closed.

DSC02262
Previous Story

ESFNA 2013: የኢትዮጵያ ቀን በሜሪላንድ በደመቀ ስነ ሥርዓት ተከበረ

UDJ Images
Next Story

አንድነት በመንግስት ጥያቄ መሰረት የጎንደርን ሰላማዊ ሰልፍ ለሐምሌ ሰባት አዘዋውረናል አለ

Latest from Blog

ህገ መንግስታዊ ዲዛይን ምርጫዎቻችን የትኞቹ ናቸው?

ኤፍሬም ማዴቦ (emadebo@gmail.com ) እኛ ኢትዮጵያዊያን እራሳችንን ስንገለጽ የረጂም ግዜ ሥልጣኔና ታሪክ ያለን፣በነጭ ያልተገዛን፣ከ2000 አመት በላይ ተከታታይ የመንግስት ሥርዓት ያለን፣የሦስቱ ዘመን ያስቆጠሩ አብርሃማዊ ሃይማኖቶች አገር ነን እያልን ነው። ነገር ግን ባለፉት ሃምሳ አመታት

የኢካን ዓላማ በኔዘርላንድ የሚኖረውን ትውልደ ኢትዮጵያውያንን እና ኢትዮጵያውያንን ኮምዩኒቲይ የማሰባሰብ ሳይሆን የመከፋፋልና የማዳከም ተልኮን ያነገበ ነው።

አገር ! ለየአንድ ሠው ቋንቋው፣ ልማዱ፣ ባሕሉ፣ እምነቱ፣ አስተሳሰቡ፣ ወጉና በአጠቃላይ እሱነቱና ማንነቱ የሚከበርበት ብቸኛ ሥፍራ ነው። ኢትዮጵያውያንም በስደት በሚኖሩባቸው አገራት ሁሉ እነኝህን በስደት ያጧቸውን የግልና የጋራ ማንነቶቻቸውን በአንድ ላይ ሆነው ለመዘከር

ፋኖ ምሽጉን ደረመሰው ድል ተሰማ | ” ስልጣን እለቃለሁ ” ፕረዚዳንቷ | ህዴድ ድብቅ ስብሰባ በአዲስ አበባ | “ተመስገንን በመዳፌ ስር አስገብቼዋለሁ” አብይ

-966+9-የኦህዴድ ድብቅ ስብሰባ በአዲስ አበባ “ተመስገንን በመዳፌ ስር አስገብቼዋለሁ” አብይ – ስልኩ ተጠለፈ “እኛ የምን’ዘጋጀው ለፋኖ ሳይሆን ለኤር-ትራ ነው” አበባው|”በጊዜ ቦታ አዘጋጁልኝ” አረጋ

አንድ በኢኮኖሚና በሌሎች ነገሮች ወደ ኋላ የቀረች አገር አንድን ኃያል መንግስት በመተማመንና ጥገኛ በመሆን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ማምጣትና የተሟላ ነፃነትን መቀዳጀት ትችላለች ወይ?

ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ሰኔ 4፣ 2016 (ሰኔ 11፣ 2024)   በዚህ አርዕስት ላይ እንድጽፍ የገፋፋኝ ዋናው ምክንያት ሰሞኑኑ ዶ/ር ዮናስ ብሩ የቻይንንም ሆነ የቬትናምን በኢኮኖሚ ማደግ አስመልክቶ ሁለቱ አገሮች እዚህ ዐይነቱ የዕድገት ደረጃ ላይ ሊደርሱ የቻሉት ከአሜሪካ ጋር

ፋኖ አንድ ሌሊት አያሳድረንም” የአማራ ብልፅግናየኢሳያስ ግዙፍ ጦር ወደ ወልቃይት

ፋኖ አንድ ሌሊት አያሳድረንም” የአማራ ብልፅግናየኢሳያስ ግዙፍ ጦር ወደ ወልቃይት አብይና ዳንኤል ክብረት ጉድ አሰሙ-|ጀነራሉ በቁ*ጣ ተናገሩ-‘ህዝቡ ጉድ ሰራን’-|“ብልፅግናን ራ*ቁቱን አስቀርተነዋል”-|ታዳሚው ባለስልጣናቱን አፋጠጠ
Go toTop