Hiber Radio: “የመጣሁት በእስር ቤት ያሉትን ጭምር እንዲፈቱ ለ እስራኤል መንግስት ጥሪ ለማቅረብ ነው” – ኦባንግ ሜቶ

/

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
የህብር ሬዲዮ ዕሁድ ሰኔ 16 ቀን 2005 ፕሮግራም

<<እስራኤል የመጣሁት በችግር ላይ ያሉ ወገኖቻችንን ጉዳይ በተመለከተ ከእነሱ ጋር ለመወያየት እና በእስር ቤት ያሉትን ጭምር እንዲፈቱ ለእስራኤል መንግስትና ለሚመለከታቸው ባለስልጣናት ጥሪ ለማቅረብ ነው…>>

አቶ ኦባንግ ሜቶ በእስራኤል ያደረጉትን ስብሰባ አስመልክቶ ከሰጡን ቃለ ምልልስ የተወሰደ

<<…በቬጋሱ ስፖርት ክለብ ጉዳይ ቦርዶ በአብላጫ (በሞሽን) ተጫዋቾቹ እንዲመጡ ወስኗል። ጉዳዩ ግን የመጨረሻ ውሳኔ አላገኘም።በቀጣዩ ቅዳሜ ስብሰባ ጉዳዩ የሚነሳ ይመስለኛል። ዛሬም የቬጋሱ ጉዳይ የፌዴሬሽኑ ትልቅ እንቅፋት ነው። ሰላማዊ በሆነ መንገድ ሁለቱንም ወገኖች የሚያስታርቅ ነገር ከየቦታው እየመጣ ነው።ትልቅ በዓል ለማክበር እየተዘጋጀን ነው ችግር ሆኖ የተገኘው ይሄ ነው ።የሁሉም ስጋት ነው።ጥፋት ተሰርቷል በሁሉም በኩል በእኛም ግን ጥፋትን በጥፋት ለመመለስ አለመሞከሩ ጥሩ ነበር።እስካሁን ድረስ ያ ነገር አልታየም።ቅዳሜ እለት ከፍተኛ እርብርብ ተደርጎ ሰላማዊ ነገር ይደረጋል ብዬ ሙሉ እምነት ይኖረኛል …>>

ተካበ ዘውዴ የቀድሞው የብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂና የፌዴሬሽኑ የውድድር ጉዳይ ሀላፊ

<<…አቶ ጌታቸው ኢትዮጵያውያንን እኩል በሚያየው ፌዴሬሽን እንዴት ተጫዋቾችን ባልመረጥነው ወኪል ካልመጣችሁ በሚል ቅዳሜ ሰርፕራይዝ ይኖራል ብለው ያስፈራሩናል?...>>

ከኢትዮ ስታር ክለብ አባላት አንዱ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት በአንድ ራዲዮ ላይ ለተወካዩ ወግነው የቡድኑን አባላት ያስፈራሩበትን ቃለ መጠይቅ የፈጠረበትን ቅሬታ ሲገልጽ

የብዙዎቻችንን ልብ ያንጠለጠለው የኢትዮጵያ ለብራዚሉ የአለም እግር ኳስ ውድድር የማለፍ ጉዞ እና አዲሱ እክል ሰሞነኛ ውሎ ሲቃኝ (ወቅታዊ ዘገባ)

የአባይ ፖለቲካ የሱዳን የኢትዮጵያን አቁዋም መደገፍ የሚያመጣው ፖለቲካዊ አንደምታና ግብጽ ወታደራዊ ፉከራዋን እውን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል አቅም አላት? (ወቅታዊ ትንታኔ አለን)

የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ጋዜጠኛ በኡጋንዳ በወገኖቹ ጥቃት እንደተሰነዘረበት መግለጹ(ቃለ መጠይቅ)

<<…በአላሙዲ የሚደገፈውን የወያኔ የዲሲ ፌስቲቫል ኢትዮጵያውያን እንዳይገኙ እና በተቃውሞው ዕለት ከጎናችን እንዲሰለፉ እንጠይቃለን…>> አቶ መስፍን የተለጣፊውን ፌዴሬሽን ለመቃወም የተጠራው የተቃውሞ ሰልፍ አስተባባሪ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ቃለ ምልልስ የተወሰደ

ሌሎች ቃለ መጠይቆችም አሉን

ዜናዎቻችን
የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌዴሬሽን ቦርድ በአብላጫው የቬጋስ ተጫዋቾች በዘንድሮው ውድድር እንዲሳተፉ ወሰነ

የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ የቦርዱን ውሳኔ በጽሑፍ አላሳወቀም

ፕሬዝዳንቱ ያልመረጡትን ወኪል ካልተቀበላችሁ ብለው ማስፈራራታቸውን ተጫዋቾቹ ገለጹ

የሱዳኑ ፕት አልባሽር በህዳሴው ግድብ ዙሪያ አቋማቸውን በይፋ ገለጹ; ኡጋንዳ አዲስ ግድብ ለመገንባት ከቻይና ጋር ተስማማች

ፕ/ት ኦባማ ደ/አፍሪካ ውስጥ” ታስረው ለፍርድ እንዲቀርቡ” ተጠየቀ

የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት አያያዝ በአሜሪካን ባለስልጣናት ፊት ተብጠለጠለ ዶ/ር ብርሃኑ “መፍትሄ ካልተበጀ መጨርሻው አያምርም “ይላሉ

<<ትኩረት እንሻለን!>><<በደል በዛብን!>> በግብጽ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ

ተጨማሪ ያንብቡ:  በእነ ሽመልስ ፉከራ ማግስት የ4 ኪሎና መቀሌ ሽር ጉድ ወዴት!? | Hiber Radio

ሌሎችም ዜናዎች አሉን

Share