ወያኔ እና ግንቦት 7

ወያኔ ማን ነው?

  • ዎያኔ ጫካ በነበረበት ዘመን ብሄሬ ተጨቁኗል በማለት ኢትዮጵያን ለማዳከም በሚፈልጉት በግብጽ በሶርያ እና በሻብያ  እየተረዳ  17 ሰባት አመት ሙሉ ኢትዮጵያን በእርስ በርስ ጦርነት እንድትፈራርስ : ልማት እንዳይሰራ (አባይ እንዳይገደብ)  እና 100,000 በላይ ህዝብ እንዲሞት ካደረገ በኋላ ስልጣን ያዘ::
  • ዎያኔ  ስልጣን ከያዘ በኋላ : የኢትዮጵያ ህዝብ ስልጣን ሳይሰጠው ከሻብያ ጋር ባለው ጓደኝነት ብቻ ኤርትራ እንድትገነጠል አደረገ:: ዎያኔ ሆን ብሎ የኢትዮጵያን የባህር ሃይል እና አየር ሃይል እንዲፈራርስ ዓደረገው:: ከዛም ሁሉንም መርከቦች እና አውሮፕላኖች ያለድርድር  ሻብያ  በነጻ እንዲወስዳቸው አደረገ::
  • ዎያኔ ቀጥሎም ኢትዮጵያ የባህር በር አልባ (land locked) መሆን አለባት አለና አሰብን ለሻብያ ሰጠ:: በዚህ ወቅት የአሜሪካ  መንግስት (USA): የአውሮፓ ህብረት (EU) እና የአፍሪካ  ህብረት (OAU) ኢትዮጵያ  ወደብ ያስፈልጋታል ቢሉም መለስ ዜናዊ አያገባችሁም  በማለት አሰብ የሻብያ  ነው ብሎ ኢትዮጵያን ወደብ አልባ አደረጋት:: በወቅቱ የነበሩት የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ ፑትሮስ  ፑትሮስ  ጋሊ ስለነበሩ መለስ ዜነዊ ከኝህ ግብጻዊ ጋር በመተባበር ኢትዮጵያ  ወደብ አልባ  መሆን የለባትም ያሉትን የአሜሪካን  መንግስት (USA): የአውሮፓን ህብረት (EU) እና የአፍሪካን  ህብረት (OAU)  ዝም እንዲሉ በማድረግ ኢትዮጵያን  ወደብ አልባ  አደረጋት:: በዚህም ዎያኔዎች ጓደኛቸውን  ሻብያን አስደሰቱ::
  • ዎያኔ ከዚህ በኋላም ኢትዮጵያን በቋንቋ  እና  በዘር መከፋፈሉን ቀጠለ:: በዚህን ወቅት የዎያኔ  ሸሪክ ሻብያ በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ከፈተ : ትግራይን በቦንብ ደበደበ:: በዚህም ጦርነት ዎያኔ ከ70,000 በላይ ህዝብ እንዲያልቅ ዓደረገ:: በዚህም አላበቃም አልጀርስ ላይ በመሄድ ከሻብያ ጋር በባድመ ጉዳይ ተፈራረመ:: በዚህ በአልጀርስ ስምምነት ወቅት የቦርደር አደራዳሪ ኮሚሽኑ ኢትዮጵያ  የባህር በርን (የአሰብን) ጉዳይን በተመለከተ  በድርድሩ አብሮ  እንዲታይላት ትፈልግ እንደሆን ሲጠይቅ ባንዳው መለስ ዜናዊ ለሁለተኛ  ግዜ አንፈልግም አሰብ የኛ አይደለም አለ:: መለስ ዜናዊ ቀጥሎም ለቦርደር ኮሚሽኑ ዲፕሎማቶች በሚስጥር ባድመን ለኤርትራ እንደሚሰጥ ቃል ገባላቸው ነገር ግን ይሄን የሚያደርገው  የኢትዮጵያ ህዝብ በባድመ ጦርነት ምክንያት የደረሰበትን ሃዘን ከረሳ በኋላ  ማለትም ከተወሰነ  አመታት በኋላ መሆኑን አረጋገጠላቸው::
  • ዎያኔ  ቀጥሎም ከዚህ በኋላ ሻብያን ሳይሆን ሻብያ  ያዘጋጀልንን ጦርነት ማለትም ኦጋዴን ውስጥ እና ሶማሊያ ውስጥ ነው መዋጋት ያለብን በማለት ሌላ ብዙ የኢትዮጵያ  ህዝብ አስጨረሰ:: አሁንም  ድረሰ  ሶማሊያ ውስጥ ተዘፍቆ  ስለሚገኝ ሻብያ እና  በቅርቡ ደግሞ ግብጽ ያዘጋጁለትን ጦርነት ይዋጋል::
  • መሬትን እንዲሸጥ እንዲለወጥ የማላደርገው አማራው ገዝቶ እንዳይጨርሰው ነው እያለ ለፈረንጆቹ ሲለፍፍ የነበረው መለስ ዜናዊ  ከምርጫ 97 በሁላ የደቡብን የጋምቤላን የአማራን እና የኦሮሞን ሰፋፊ መሬት ለአረብ(ለግብጽ እና ሳውዳረብያ) ለቻይ ለህንድ ለፓኪስታን ወዘተ ሃገሮች በነጻ ያድለው ጀመረ:: በዚህም ምክንያት ከመቶ ሽህ በላይ ጋምቤላዎች አማራዎች መሬታቸው ተነጥቆ ከነበሩበት ቦታ ተባረሩ:: የነጻነት ተዋጊ እና ልማታዊ ነኝ የሚለው ዎያኔ በ22 አመት ውስጥ ትራክተር ገዝቶ ሰፋፊ መሬት ማረስ ብርቅ ሆኖበት ዎይም አቅቶት መሬቱን በጥድፊያ ለባእድ ሃገራት ይቸረችረው ጀመር::
  • ዎያኔ የሰራው ልማት :- መንገዶች እና  ዩኒቨርስቲዎች  በ10 ቢሊዮን ዶላር + መካከለኛ ግድቦች 5 ቢሊየን ዶላር + አባይ ግድብ 5 ቢሊየን ዶላር = ድምር 20 ቢሊየን ዶላር
  • ባለፉት 22 አመታት ዎያኔ  ባጠቃላይ ያባከነው እና  የሰረቀው :-  12 ቢሊየንዶ ዶ ላር ተዘርፎ  የወጣ + 40 ቢሊየን ዶላር ለወደብ ክፍያ ማለትም ለጂቡቲ  ወደብ : ለኬንያ ወደብ : ለሱዳን እና ለሶማሊያ ወደብ + 5 ቢሊየን ዶላር ባድመን ለሚጠብቅ የኢትዮጵያ  ወታደር= ድምር 57 ቢሊየን ዶላር
  • ስለዚህ ኢትዮጵያ በዎያኔ ምክንያት ላለፉት 22 አመታት ባጥቃላይ 37 ቢሊየን ዶላር አጥታለች:: ህዝቧ  በዘር እና በጎሳ ተተብትቦ  እየተናቆረ ይገኛል:: ፍትሃዊ የስልጣንና የሃብት ክፍፍል  እንዲሁም ዴሞክራሲዊ ምርጫ የሚባል ነገር በኢትዮጵያ የለም:: ወደብ የላትም :: መሬቷ ለሱዳን ተሰጥቷል::
ተጨማሪ ያንብቡ:  እውን ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ ጥቁር አይደለንም ይላሉ? | ይህን ቪዲዮ ይመልከቱ

ግንቦት 7 ማን ነው?

  • ታዋቂ የኢኮኖሚክስ ምሁር በሆኑት በዶ ክተር ብርሃኑ ነጋ የሚመራ  ግንቦት ሰባት ማለት ባጭሩ ከላይ የተጠቀሱት የዎያኔ  የባንዳ እና የሃገር ሻጭነት ድርጊቶች  እንዲሁም የፍትህ : የመልካም አስተዳደር እና የዲሞክራሲ እጦት አንገፍግፎት ለትግል የተነሳ  ድርጂት ነው:: ስለዚህም ዎያኔዎች ግንቦት ሰባት ማን እንደሆነ ዎያኔ ማን እንደሆነ ጠንቅቀን ለምናውቀው ለማስረዳት ባትሞክሩ ጥሩ ነው::  አይ ዎያኔዎች! ኦባንግ ሜቶን አሸባሪ ያላችሁ ሰዎች ሌላውን ምን እንደምትሉ ስለምናውቅ ቀልዱን ትታችሁ ዘረኘነት እንዲጠፋ: ፍትህ እና ዴሞክራሲአዊ ምርጫ እንዲስፋፋ በቀራችሁ የንስሃ ግዜ ለመስራት ሞክሩ::

BY: Asress M.

6 Comments

  1. That is the different between WOYANE and DEMOCRATIC G7,do you understand hodam caderes.

  2. This writer is tring to inspire people by using Shabieya 100 times dude read history first how country’s created on modern day all the result of colonization ok so your grand dad mad a mistake why you try blam weyina on the issue of Eritrea plus Eritrea is not a gift of Weyia for Eritrean we paid expansive pric to get our freedom wow thanks God and we are ready anytime to difend our country and we will work even with devel to distroi weyina and hodam Amharas like you.

    • @Abebe you are crazy shabia ..for the last 22 years Eritreans are living a miserable life. Shabia and woyane were fooled by Arabs (Egypt and Siria) many times. Both people are suffering.

Comments are closed.

Share