July 9, 2015
2 mins read

የህዝበ ሙስሊሙ ኮሚቴ ጠበቃ ተማም አባቡልጉ የጥብቅና ሙያቸው ኮሚቴዎቹ የጥፋተኝነት ብይን በተላለፈበት ቀን መሰረዙ ታወቀ

Temam Ababulgu
ጠበቃ ተማም አባቡልጉ

ጠበቃ ተማም አባቡልጉ
የህዝበ ሙስሊሙ ኮሚቴ ጠበቃ ተማም አባቡልጉ የጥብቅና ሙያቸው ኮሚቴዎቹ የጥፋተኝነት ብይን በተላለፈበት ቀን መሰረዙ ታወቀ 1

ሰበር ዜና ቢቢኤን
ቢቢኤን ሃምሌ 2/2007

የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ጠበቃ የሆነው ጠበቃ ተማም አባቡልጉ በፍርድ ቤት ላይ በሚያደርጋቸው ክርክሮች በተለይም መንግስት ከጅሃዳዊ ሀረካት ጀምሮ የሰራቸውን ሸፍጦችና ኢትዪጲያዊ ውስጥ የፍትህ ስርአቱን ዝቅጠት በመረጃና በህግ በማጣቀስ በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ በማጋለጣቸው ምክኒያት ከዚህ ክስ ተመስርቶባቸው እንደነበር ይታወቃል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ማስፈራሪያና ዛቻዎች ከመፈጸማቸውን ሌላ እብድ በሚመስል ሰው በመላክ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ይታወቃል፡፡

ይህ ሁሉ ግፍ ተፈጽሞባቸው በጀግንነት ከስራቸው ያልቆሙት እንዲሁም የህግ ክፍተቶችን ጭምር በማጋለጥ፤ ከኮሚቴዎቹ በተጨማሪ መንግስት የከሰሳቸው የነ አብራ ደስታ ጠበቃ የነበሩትን ተማም አባቡልጉን መንግስት በኮሚቴው ላይ የጥፋተኝነት ብይን ባስተላለፈበት እለት የጥብቅና ሙያቸውን ፍቃድ ፍትህ ሚኒስትር መሰዘረዙ ታውቋል፡፡
አቶ ተማም አባቡልጉ ያለ ምንም ፍርሃት እውነታውን በሚዲያዎች ላይ በማጋለጥ ታላቅ አስተዋጾ ያበረከቱ፤ በብዙዎች ዘንድ በጀግንነት የሚጠሩ ፤ ፤ለሙያቸው ያደሩ ጠበቃ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ቢቢኤን ጠበቃ ተማም አባቡልጉን በማነጋገር ተጨማሪ መረጃ ይዞ የሚቀርብ ይሆናል::

1 Comment

  1. (፩) የአመልካች ምስክሮች በሰጡት ምስክርነት ጠበቃ ተማም በሽምግልናው ወቅት መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡
    (፪) የጠበቃ ተማም ምስክሮች ሽምግልና መደረጉን የገለጹ ቢሆንም፣

    *** ጠበቃው ስለመገኘታቸው ግን ምንም ያሉት ነገር እንደሌለም ጠቁሟል፡፡
    (ሀ)ጉባዔው ማስረጃው ሲመዘን የአመልካች ምስክሮች አመሰካከር ዕምነት የሚጣልበት ሆኖ መገኘቱን ጠቁሞ፣
    (ለ)ጠበቃው በሽምግልና ያዩትን ጉዳይ በጥብቅና ይዘዋል ማለት የሚችልበት ድምዳሜ ላይ መድረሱን ገልጿል፡፡
    _ ጠበቃው ለእርቅ (ለምክር)ሁለቱን ለማቀራረብና ከፍርድ ቤት ውጭ ለመደራደር አስበው ነበር?
    _ conciliation …ሽምግልና ሳይሆን በግራና ቀኝ ጠበቆች ወይንም ጉዳዩ በሚመለከታቸው አካላት(ተወካዮች) ጉዳዩን በስምምነት ለመፍታት፣ የፍርድ ቤቱን የሥራ ጫና ለማቅለል፣ የተካራካሪዎችን ግዜና ገንዘብም የሚቆጥብ ድርድር ነው። ያም ሆኖ ድርድሩ ከፈረሰ በኋላ የተስማሙበት ፈርሶ አቶ ተማም አባቡልጉ ጉዳዩን ከረቱ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል..ለምን? ማሸናፊያውን ቀድመው አውቀውት ነበር ዳኛውን ሊያሳስቱት ይችላሉ ፍርድ አጋደለ ሊያስብል ይችላል….የጠበቆች የዲሲፕሊን ጉባኤ ሕመ/አንቀፅ ፳፭ “ሁሉም ሰዎች በሕግ ፊት እኩል ናቸው፡ ሕመ/አንቀፅ ፸፱ (፩)በፌደራልም ሆነ በክልል የዳኝነት ሥልጣን የፍርድ ቤቶች ብቻ ነው (፪) በየትኛውም ደረጃ የሚገኝ የዳኝነት አካል፡ ከማንኛውም የመንግስት አካል፡ ከማንኛውም ባለሥልጣን ሆነ ከማንኛውም ሌላ ተፅዕኖ ነፃ ነው” (ሌሎች ንዑስ አንቀጾች የዳኝነት ሥልጣን ገላጭ እንጂ ከዚህ ጉዳይ ጋር ምንም አያገናኝም!!
    ስለዚህም “የአመልካች ምስክሮች አመሰካከር ዕምነት የሚጣልበት ሆኖ መገኘቱን ጠቁሞ በሽምግልና ያዩትን ጉዳይ በጥብቅና ይዘዋል የሚል ድምዳሜ ላይ ተደረሰ!?” ግን ጠበቃው ይህንን ሁለት አንቀፅ ማንበብና መረዳት ሳይችል እንዴት የጥብቅና ፈተናውን አልፎ ተመረቀ!?
    “ሊበሏት ያሰቧትን ቂጣ ፒዛ ናት ይሏታል አለ….

Comments are closed.

afar man
Previous Story

በአፋር ክልል ወጣቶች ለውትድርና በግዴታ እየታፈሱ ነው

Next Story

በሰሜን የአገሪቱ ክፍል የሚታየውን ውጥረት ተከትሎ አየር ሃይል በጠንቀቅ እንዲቆም ታዘዘ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop