በሰሜን የአገሪቱ ክፍል የሚታየውን ውጥረት ተከትሎ አየር ሃይል በጠንቀቅ እንዲቆም ታዘዘ

ሐምሌ ፫ (ሶስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሳምንት የአርበኞች ግንቦት7 በወሰደው ፈጣን ጥቃት በርካታ የኢህአዴግ ወታደሮች መገደላቸውን ፣ ይህንን ተከትሎ የወልቃይትና አካባቢው ህዝብ ያሳያው ድጋፍ እና ሽምቅ ተዋጊዎችን ለመቀላቀል የሚጠይቀው ወጣት መበራከት ያሰጋው ገዢው ፓርቲ፣ የአየር ሃይል አባላት በጠጠንቀቅ እንዲቆሙ ማዘዙን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
Photo File
የአየር ሃይል አባላቱ ካለፉት ሁለት ወራት ጀምሮ ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በሌሊት ፈረቃ እንዲሰሩ ሲደረግ ቢቆይም፣ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ስልጠናው ተጠናክሮ መቀጠሉን እንዲሁም አየር ሃይል አባላቱ ማንኛውም ግላዊ እንቅስቃሴያቸው እንዲገታ ተደርጓል።

የአየር ሃይል አባላቱ ” አንደኛ ደረጃ ተጠንቀቅ” የሚተላለፈው ፓርላማው የጦር አዋጅ ሲያውጅ ብቻ መሆኑን ለኢሳት ቢገልጽም፣ ጠ/ሚኒስትሩ ” ህዝብ አስፈቅደን በኤርትራ ላይ እርምጃ እንወስዳለን ከማለት ውጭ” የጦርነት አዋጅ እንዲታወጅ አላደረጉም።

አዲስ የጦር አውሮፕላኖች ተገዝተው መምጣታቸውንም የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በደፈጣ ውጊያ ፈጣን ጥቃት በመፈጸም ከፍተኛ ድል ያገኘው የአርበኞች ግንቦት7 ጦር ፣ በተለያዩ አካባቢዎች እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑንም የሚደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

የኢህአዴግ መንግስት ከአንድ ሳምንት ዝምታ በሁዋላ ሰሞኑን ጦርነት እንደነበር ለማመን ተገዷል። በምእራብ ትግራይና ሰሜን አማራ ድንበር ሰርገው ለመግባት የሞከሩ 30 የሻእቢያ ተላላኪዎች ተደምስሰዋል ሲል የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄ/ል አሰፋ ተናግረዋል። ጄኔራሉ ጦርነቱ ከማን ጋር እንደተካሄደ ለመግለጽ ድፍረቱን አላገኙም። በደፈናው የሻእቢያ ተላላኪዎች ከማለት ውጪ አርበኞች ግንቦት7 ለማለት አለመድፈራቸው እንዲሁም “አንድም ያፈገፈገ ተንኳሽ የለም” ካሉ በሁዋላ፣ ተመልሰው “አብዛኞቹን ደምስሰናቸዋል ፣ ጥቂቶችም ይዘናቸዋል” ማለታቸው እርስ በርሱ የሚጋጭ እና የመገለጫውን ተአማኒነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ መሆኑን ዘጋቢያችን ገልጿል።
አሰማርቷል። ይሁን እንጅ ለጥበቃ ከተሰማሩት መካካል የተወሰኑ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ጠፍተው ኤርትራ ገብተዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሙስጠፌ ነጭ ነጯን ፊት ለፊት ተናገሩ-|"ፖለቲካው ታሟል ... ብልጽግና ፈርሷል

3 Comments

  1. መልካም ዜና ነው ….. የኔ ፍራቻ ግን ምን ያህል የተጠናከረ ሀይል ዕላቸው ነው? ለምሳሌ በቀን ውጊያ ላይ ዕዲሱን ( like Drone camera )ቴክኖሎጂ በመጠቀም የውጊያውን ሚዛን የሚደፋው ወደ ወያኔ ሃይል ነው ….. ለዐርበኞች ሀይል ሊያዋጣ የሚችለው በለሊት ውጊያ ቢሆን የመረጣል ….. ዐርበኞች ሀይል ደግሞ የዛን ያሀል ችሎታ ያላቸው ግን ዐይመስለኘም …… ሌላው ከዐርበኞች ሀይል ዐዛቾቹ እንደስማነው ከሆን የወያኔ ሀይል በእጅጉ የፈራው ይመስላል ….. በቴክኖሎጂ የተበለጠ ይመስላል እና ነው….. ከሰው ሃይል በላይ የቴክኖሎጂ መሳሪያ ተገቢ እና ወሳኝነት ዐለው …… ያ ሲሆን ብቻ ነው በውጊያው የበላይነት የሚኖረው…. ያ ካልሆነ ግን የስው ሀይል ማስፈጀት ብቻ ነው….

    • ሃ ሃ ሃ ሃ !!! የእግር ኳስ ትንተና አመሰልከው እኮ !
      ጦርነት እኮ ነው! ስትራቴጂ የምታውቅ ከሆነ ለምን እዚያ ሄደህ አትዋጋም?

Comments are closed.

Share