ዜና ፍትሕ ከትግራይ ክልል፡ የ12 ሰዎች አስከሬን በአንድ ቤተክርስትያን በጅምላ ተቀበረ… እና ሌሎችም

June 16, 2013

አብርሃ ደስታ ከመቀሌ

አንድ

በአፅቢ ወረዳ (ጣብያ ሩባ ፈለግ፣ ቁሸት ደብረሰላም) የሚኖሩ አርሶ ኣደሮች በግጦሽ መሬት ይገባኛል ምክንያት ከመንግስት ጋር ተጣሉ። መንግስት በፓኬጅ ፕሮግራም (‘ፓኬጃዊ ምትእትታው’) መሰረት በ’ፍትሓዊ ልቃሕ’ (‘ፍትሓዊ ብድር’ መሆኑ ነው) አማካኝነት ገበሬዎቹ ብድር ወስደው ከብቶች ይገዛሉ። በተመሳሳይ ግዜ በአከባቢው የሚገኝ የሳር (ግጦሽ) መሬት እንዲከበርና ገበሬዎቹ እንዳይጠቀሙት ይወሰናል።

አርሶ አደሮቹ ከብቶች ገዝተው አርብተው ዕዳቸው (የወሰዱት ብድር) ለመመለስ ሲፈልጉ ከብቶቻቸው የሚበላ አስፈለጋቸው። የሳር መሬቱ መጠቀም ፈለጉ። መንግስት አልፈቀደላቸውም፤ ከለከላቸው። ህዝቡ ዓመፀ (ወይ ዕዳው ይሰረዝ ወይ ከብቶቹ የሚበላ ይኑራቸው ብለው)። መፍትሔ አላገኙም። የተወሰኑ አርሶ አደሮች የራሳቸው የነበረ (በኋላ የተከበረ) ሳር መጠቀም ጀመሩ። የወረዳው ምልሻዎች ሰዎቹን ማስፈራራት ጀመሩ። ሁሉም የአከባቢው ገበሬዎች የየራሳቸው ግጦሽ መጠቀም ጀመሩ። የወረዳው ፖሊሶች መተው (አቶ ወልደገብርኤል ሃይሉና አምሳ አለቃ አታክልቲ የተባሉ ሁለት ሰዎች) ለማሰር ሲሞክሩ ህዝቡ ተሰብስቦ ‘ከፈለጋቹ ሁላችን እሰሩን’ ብለው ይጮሃሉ። ፖሊሶቹ በዱላ መደብደብ ጀመሩ። ህዝቡም ድንጋይ እየወረወረ ከፖሊሶቹ ይጋጫል። ተኩስ ተከፈተ፤ በድንጋይ የቆሰሉ ብዙ ሰዎች አሉ።

ያልተመጣጠነ ሃይል በመጠቀም ሰባት አርሶ አደሮች (ከነከብቶቻቸው) ታስረዋል። ከብቶቹ እንዴት እንደታሰሩ ግልፅ አይደለም። ዛሬ ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች እንዲታሰሩ ስም ዝርዝራቸው ይፋ ሆነዋል። በአከባቢው ውጥረት ነግሷል። ከነከብቶቻቸው የታሰሩ ሰባት ሰዎች የድሮ የህወሓት ታጋዮችና እስከ ቅርብ ግዜም የሕወሓት አባላት የነበሩ ናቸው። በደርግ ዘመን ‘ከህወሓት ታጋዮች ግንኙነት አላቸው’ ተብለው ከነከብቶቻቸው ታስረው እንደነበርና በዛ ምክንያት ወደ ትግሉ እንደተቀላቀሉ ለማወቅ ችያለሁ። የአከባቢው ኗሪዎች አሁንም ከነከብቶቻቸው መታሰራቸው ግርምት ፈጥሮባቸዋል። ግጭቱ የተጀመረው ግንቦት 10 ሲሆን ተኩሱና እስሩ የተፈፀመው ግን ሰኔ 6, 2005 ዓም ነው።

ሁለት

በሰሓርቲ ሳምረ ወረዳ (ጣብያ አዲሳለም፣ ቁሸት ሓንጣባት) የመንግስት ሰዎች የአከባቢው አርሶአደሮች በማስገደድ መዳበርያ እንዲወስዱ በሚያስፈራሩበት ግዜ ሁለት ሰዎች (አቶ ግርማይና መምህር ገብረህይወት የተባሉ ነዋሪዎች) ‘ህዝብ ማስፈራራት ተገቢ አይደለም’ ብለው ስብሰባ ረግጠው በመውጣታቸው እንዲታሰሩ ሲወሰን ህዝቡ (በሙሉ) ‘ሁላችንም እሰሩን’ ብሎ ፖሊስ ጣብያ ድረስ በመሄዱ ሁለቱም ሰዎች ሳይታሰሩ ቀርተዋል። መተባበር እንዲህ ነው። ህዝቡ ካበረ የካድሬዎች መጫወቻ አይሆንም።

ሦስት

በእንደርታ ወረዳ (ጣብያ ማይፀዶ፣ ቁሸት እግሪሓሪባ) በመሬት ጉዳይ በህዝቡና ካድሬዎች መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ ለሁለት ዓመት ያህል የመንግስት አገልግሎት (የመንግስት አስተዳደር) ተቋርጧል። በዛ አከባቢ የመንግስት አካል የለም። ክሊንኮች አይሰሩም። የአከባቢው አስተዳደር የለም። ለምሳሌ በአከባቢው የሚገኘው ‘ተከስተ ሃይሉ ትምህርትቤት’ በሚል ስም የሚታወቅ ትምህርትቤት ከተዘጋ ዓመት ሁኖታል። ከዛ አከባቢ የሚመጡ ተማሪዎች የትምህርት ዕድል ተነፍገዋል (‘ወላጆቻቹ ለመንግስት አልታዘዙም’ በሚል ሰበብ)። ለመንስግት አለመታዘዝ አገልግሎት ያሳጣል።

አራት

በዚህ ሳምንት በመቀለ ከተማ የአስራ ሁለት ሰዎች አስካሬን በአንድ ቤተክርስትያን በጅምላ እንዲቀበሩ የተሞከረ ሲሆን የቤተክርስትያኑ ሓላፊዎች ከመቀበራቸው በፊት የአስካሬኖቹ ማንነት እንዲታወቅ ጠይቀው የመንግስት አካላት መልስ መስጠት ስላልፈለጉ ቤተክርስትያኒቱ እንደማትቀበል አሳውቃ ነበር። ትናንት ባገኘሁት መረጃ ግን አስካሬኖቹ በእንዳጋብር ቤተክርስትያን በጅምላ (በምስጢር) መቀበራቸው ነው። ሰዎቹ በፖለቲካ ምክንያት የተረሸኑ ሳይሆኑ አይቀሩም (ተጨማሪ መረጃ ግን ያስፈልጋል)።

ህዝብ ግን ፍትሕ ያስፈልገዋል።

8 Comments

  1. It is really surprise and unbelievable, atrocity in Tigray Region where TPLF is getting full cover and backbone. I read dozens of Afar people killed woyane junta. so, who is safe???????

  2. አብርሃ፣ ይህ የምዘግበው እውነት ከሆነ በእንግሊዝኛ ጽፈህ ለሂዩመን ራይስትስና ለተባበሩት መንግሥታት እንዲሁም ለአምነስቲና ቪኦኤ ለዶችቨለ ላክ። በአማርኛ ብቻ መጻፍህ ዋጋ የለውም። የአስገደ ልጆች ቶርቸር ተደረጉ ያልከውን እስከ ዛሬ በእንግሊዝኛ ብቻ ስለጻፍክ ማመን አልቻልኩም።

  3. አብርሃ፣ ይህ የምትዘግበው እውነት ከሆነ በእንግሊዝኛ ጽፈህ ለሂዩመን ራይስትስና ለተባበሩት መንግሥታት እንዲሁም ለአምነስቲና ቪኦኤ ለዶችቨለ ላክ። በአማርኛ ብቻ መጻፍህ ዋጋ የለውም። የአስገደ ልጆች ቶርቸር ተደረጉ ያልከውን እስከ ዛሬ በእንግሊዝኛ ስላልጻፍክ ማመን አልቻልኩም።

  4. Ye Ethiopia hizbe Egypt beytegnaw menged endmtimata ye Egypt parlama negrawetal en eygamera new ye Ethiopia hizbe tezegagi. Ke ahunu 1belu.

  5. I had no a slight doubt such injustice will happen in Tigrai and upon Tigraway. I had a very misconception that in Tigray there exists arelatively better democracy unlike other regions. Is it the reward that the Tigray people should receive from TPLF after paying all that sacrfiication for the struggle?

  6. Thank you, Abraha Desta,

    TPLF leadership has been abusing Tigreans for over 39 years. Our non-Tigrean brothers think that Tigreans are safe from the mafia group. We shouldn’t fool ourselves this mafia group were/are against all of us, ETHIOPIANS since their inception. The only way out is fighting the devils in unison.

Comments are closed.

ethiopia football
Previous Story

ቡድናችንና ግብፃዊ ዳኛ …… (አብርሃ ደስታ ከመቀሌ)

Child abuse
Next Story

በአ.አ 6 መምህራን በህፃናት ላይ ግብረሰዶም ፈጽመዋል በሚል ተጠርጥረው ታሰሩ

Latest from Blog

አዲስአበባ ተኩስ ተከፈተ “ለመደራደር ዝግጁ ነን” አረጋ ከበደ | አብይ አደገኛውን ካርድ መዘዙ | አዲሱ አዋጅና የቀረበበት ተቃውሞ “የሞተም ሰው ንብረት ይጣራል | ጌታቸው ያጋለጠው ጸብ

አዲስአበባ ተኩስ ተከፈተ “ለመደራደር ዝግጁ ነን” አረጋ ከበደ\  አዲሱ አዋጅና የቀረበበት ተቃውሞ “የሞተም ሰው ንብረት ይጣራል አብይ አደገኛውን ካርድ መዘዙ ጌታቸው ያጋለጠው ጸብ

ከመጠምጠም መማርን እናስቀድም!

;በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) አብዛኛው አንባቢ ተገንዝቧል ብዬ እንደምገምተው ሕዝብ ለቡና ቲራቲም፣ ለግብዣ፣ ለበዓል፣ ለሰረግ፣ ለሐዘን፣ ለእድር፣ ለእቁብ ለውይይትና ለሌሎችም ማህበረሰባዊ ጉዳዮች ሲገናኝ የሚበዛው አድማጭ ሳይሆን ተናጋሪ  ወይም ደግሞ ለመናገር  መቀመጫውን ከወንበር ወይም
Go toTop