ቡድናችንና ግብፃዊ ዳኛ …… (አብርሃ ደስታ ከመቀሌ)

June 16, 2013

ዛሬ እሁድ ማታ ለሚካሄደው የዋልያዎችና የባፋናዎች የእግርኳስ ግጥምያ መቐለዎች ለድጋፉ ካሁኑ ሽርጉድ ጀምረዋል። የሀገራችን ባንዲራ የያዙ ወጣቶች በብዛት ይታያሉ። የተወሰኑ ወጣቶች እንደነገሩኝ የዛሬ ጨዋታ አስጨናቂ ነው። ምክንያቱም

(1) ለዓለም ዋንጫ የምናልፍበት ወሳኝ ጨዋታ ነው። (2) የመሃል ዳኛው ግብፃዊ ነው (በግብፅና ኢትዮዽያ መካከል ያለው የፖለቲካ ውዝግብ የዳኛው ውሳኔ …. ከሚል ስጋት ነው)።

የኔ ስጋት ግን ‘ዋልያዎቹና ባፋናዎች ይመጣጠናሉ ወይ?’ የሚል ነው። የስፖርት ትንተናው ለባለሙያዎቹ ልተወውና ስለ ግብፃዊ ዳኛና የተገመተው የፖለቲካ ተፅዕኖ ትንሽ ልበል።

ግብፃዊው የመሃል ዳኛ (የፖለቲካ ሁኔታችን እየታወቀ ለምን ግብፃዊ ዳኛ እንደተመረጠ አልገባኝም) ያሰብነው ችግር ይፈጥራል ብዬ አላምንም። ምክንያቱም

(1) የስፖርትና የፖለቲካ የጨዋታ ሕጎች የተለያዩ ናቸው። የእግርኳስ ጨዋታ የራሱ የሆነ ደምብ አለው። ደምቡ ሳይንሳዊ ነው፤ አብዛኛው የእግርኳስ አፍቃሪ ሕጉ ያውቀዋል። ጨዋታው ህዝብ ያየዋል፤ አይቶም የየራሱ ፍርድ ይሰጣል። ዳኛው ጨውታውን ይዳኛል፤ ህዝቡ ደግሞ ዳኛውን ይዳኛል። በስፖርት ሕግና ዳኝነት (ከፖለቲካ ጋር ሲነፃፀር) የተሻለ ግልፅነት አለ። በፖለቲካ እውነታውን መጠምዘዝና በውሸት ‘ትክክል’ መሆኑ ለህዝብ መሸወድ ይቻላል። ይህን የሚደረገው ግልፅነት በማጥፋትና መረጃ በማሳሳት ነው። ግልፅነትና መረጃ ማሳሳት የሚቻለው ነፃ የግል ሚድያ በማፈን ነው።

ፖለቲካ ስለስነግባር አይደለም። የስፖርት ዳኝነት ግን ከስነምግባር ጋር የተያያዘ ነው። ስለዚህ ዳኛው ውሳኔ ያበላሻል ብዬ አላስብም። ደግሞ አበላሽቶ ምን ይጠቀማል? ጉዳት ብቻ ነው ያለው። ካበላሸ በስነምግባር ጉድለት ከዳኝነት ሙያው ሊታገድ ይችላል።

(2) እንበልና ዳኛው የፖለቲካ ዓላማ ይዞ ወደ ሜዳው ገብቷል። በጦርነት ወይ ግጭት ለማሸነፍ ፕሮፓጋንዳ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ከፕሮፓጋንዳዎች አንዱ የሌላውን ህዝብ ቀልብ መሳብ (public diplomacy) ነው። ስለዚህ ግብፅዊው ዳኛ ለሀገሩ ማበርከት የሚፈልገው ፖለቲካዊ ሚና ካለው ለኢትዮዽያ ብሄራዊ ቡድን በተቻለ መጠን ማገዝና (ወይም ፍትሓዊ ዳኝነት በመስጠት) ኢትዮዽያውያንን ማስደሰት ነው። ኢትዮዽያውያን ስለ ግብፃውያን ‘ጥሩ’ አመለካከት እንዲኖራቸው ጥረት ካደረገ ለሀገሩ ጥሩ ነገር ሰራ ማለት ነው።

(3) ሆን ብሎ የኢትዮዽያ ብሄራዊ ቡድን ለመበደል ካሰበና ካደረገ ግን እንደ የፖለቲካ መሪዎቹ ፖለቲካ አያውቅም ማለት ነው። የኢትዮዽያ መንግስት (ከዳኛው ስሕተት) ፖለቲካዊ ጥቅም ያገኛል ማለት ነው። ባጭሩ ግን ዳኛው ፍትሓዊ ዳኝነት ከመስጠት እንጂ ከማበላሸት ምንም አይጠቀምም። ስለዚህ ‘ትክክለኛ ዳኝነት’ ይሰጣል ብዬ አስባለሁኝ።

በመጨረሻም

አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ተጫዋቾቹን በትእግስት፣ ስነምግባር በተሞላበት ጥሩ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ እንጂ አንዳንዴ ከሚፈፅሙት ጥፋት (በዳኛም በሌሎች ተጫዋቾችም) እንዲጠነቀቁ መምከር አለበት። የኢትዮዽያ እግርኳስ ፌደሬሽንም የቡድኑ ደጋፊዎች (አንዳንድ ችግሮች ቢፈጠሩ) በዳኛውና በሌሎች ተጫዋቾች ችግር እንዳይፈጥሩ (ሊጣልብን ከሚችል ቅጣት አንፃር) ጠንከር ያለ መልእክት ማስተላለፍ ይገባዋል።

ድል ለብሄራዊ ቡድናችን!!!

It is so!!!

Latest from Blog

ነገሩ እንዲህ ነው ባሳለፍነው ታህሳስ 15 በተካሄደው ብልጽግና ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ላይ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አረጋ ከበደ እጃቸውን አውጥተው ተናገሩ እኔ አቅቶኛል የአማራ ክልል ቀውስ ማስተዳደር አልቻልኩም ብለው ተናገሩ በዚህ ጊዜ

“አንተን ለማኝ አደርጋለሁ” አቢይ አሕመድ ለአማራ ክልል ፕረዚዳንት ለአረጋ ከበደ የሰጠው ማስጠንቀቂያ

January 31, 2025
ከቴዎድሮስ ሃይሌ የምናከብራቸው ጀነራል ተፈራ ማሞ ሰሞኑን አደባባይ ወጥተው አድምጠናል:: የጀነራሉ ጤንነትና ደህንነት ሲያሳስበን ለቆየነው ወገኖች ሁሉ በጥሩ ቁመና ላይ ሆነው በማግኘታችን የሕሊና እረፍት ሰጥቶናል:: አሁንም ባሉበት ሰላሞት እንዲበዛ ምኞታችን ዳር የለውም::

እስክንድር ነጋ እና ጀነራል ተፈራ ማሞ ከድል ለዲሞክራሲ እስከ ፉኖ ተሰማራ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ዛሬም እንደ ትናንቱ አያሌ ምሁራንና ታዋቂ ነን ባይዎች ስለብሔራዊ ሽምግልና እርቅ ይደሰኩራሉ፡፡ ያለምንም ሐፍረት ቅዱሱን ሽምግልናን ከምእራብ ከተሸመተው ኤፍሬም ይሳቃዊ ድርድር ጋር እያምታቱ የአያት የቅድመ አያቶቻችንን የተባረክ የሽምግልና ሐብት ያበላሻሉ፡፡ ሽምግልና በመለኮት

ፍትህ የሌለው ሽምግልናና እርቅ ሥራ እንደሌለው እምነት የሞተ ነው!

Go toTop