በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በምርጫ እንዲሳተፉ ሊደረግ ነው

በዘሪሁን ሙሉጌታ
በተለያዩ የውጪ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ዜጎች በሀገሪቱ በሚካሄዱ የምርጫ ስርዓት በመሳተፍ ድምፅ እንዲሰጡ ሊደረግ ነው።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ህግና ደንብ መሰረት በአረብ አገራት ፣ በሰሜን አሜሪካ እና በአውሮፓ እንዲሁም ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ በሌሎች አገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ምርጫ መምረጥ የሚችሉበት ዕድል እየተመቻቸ ነው።
በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የዲያስፖራ ተሳትፎ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል የሆኑት አቶ ሙሉጌታ ተሊል ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት ምርጫው የሚከናወነው የሀገሪቱን አቅም ባገናዘበ ሁኔታ በርካታ ኢትዮጵያውያን በሚገኙባቸው ማዕከላት ውስጥ የምርጫ ጣቢያዎችን በማደራጀት ዜጎቹ ህገ-መንግስታዊ መብታቸውን እንዲወጡ ይደረጋል ብለዋል።
አዲስ የተዘጋጀው የዲያስፖራ ፖሊሲ ካካተታቸው ዋና ዋና ጉዳዮች አንዱ በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በምርጫ እንዲሳተፉ ማድረግ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ቅዳሜ ሰኔ 8 ቀን 2005 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ የዲያስፖራ ፖሊሲ ላይ በውጪ ሀገር ከሚኖሩ፣ ቁጥራቸው ከአንድ ሺ እስከ ሁለት ሺ ከሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ጋር በፖሊሲው ላይ ምክክር እንደሚካሄድ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስታወቁ አይዘነጋም።n

 

ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ የዛሬ ጁን 12 ቀን 2013 ዕትም

ተጨማሪ ያንብቡ:  ፋኖ ሾኖ ደረሰ 4ኪሎ ባዶሆነ | ጀነራል አበባው በአየር አመለጠ

5 Comments

  1. when they couldn’t get any vote in the country they try to get vote from diaspora it won’t happen it is going to be worse you don’t get a single vote from out side the country for the matter of fact you don’t get any vote from either side. inside or out .

  2. ዲያስፖራው አነሰም በዛም ዲሞክራሲያዊ ግንዛቤ አለው ጥቂት አይን የጨፈኑደጋፊዎች ካልሆኑ በስተቀር ትክክለኛ ምርጫ ለማድረግ በአሁኑ ሁኔታ እንደማይቻል ሁሉም ያውቃል ።ደግሞም ኢህአዴግ በምርጫ የተሸነፈ ፓርቲ ነው እንደገና ለመወዳደር የሞራል ብቃት የለውም።

  3. Believe me the woyane ethno-fascist thugs are not doing this because they have any belief in democracy or the ballot box. This is another systematic way of the fascists to control and spy on the activities of the diaspora. The woyane thugs know that Ethiopians are fleeing the country to escape woyane fascism. Many of our compatriots dying in the desert, eaten by wild animals, drowning in the sea in trying to escape from the horrors of the woyane. The woyane know that no body is going to vote for them except their spies and cadres they have placed among the diaspora comunity.

    It is a con. woyane , we know who you are!

Comments are closed.

Share