ኢትዮጵያ በግብፅ ላይ ተመጣጣኝ የኃይል እርምጃ ለመውሰድ 1ሺ 500 ኪሎ ሜትር የሚወነጨፍ ሚሳኤል መታጠቅ ብቻ ይበቃታል

June 12, 2013
በፋኑኤል ክንፉ
 
 የግብፅ ፕሬዝዳንት መሐመድ ሙርሲ የሕዳሴውን ሃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታን በተመለከተ ሁሉም አማራጮች በጠረጴዛ ላይ ናቸው ማለታቸውን ተከትሎ፣ አንድ የቀድሞ መንግስት ከፍተኛ ወታደራዊ ኤክስፐርት የግብፅ መንግስት ላይ ተመጣጣኝ እርምጃ ለመውሰድ 1ሺ 500 ኪሎ ሜትር የሚወነጨፍ ሚሳኤል መታጠቅ ብቻ በቂ ነው ሲሉ በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ ገለፁ።
ኤክስፐርቱ እንደገለፁት “ግብፅ የሕዳሴውን ኃይል ማመንጫ ግንባታ ግድብ በጦር መሣሪያ ለመምታት ካስቀመጠቻቸው አማራጮች አንዱ መሆኑን በመጠቆም ግብፅ የሕዳሴውን ኃይል ማመንጫ ግድብ ስትመታ ለኢትዮጵያ መንግስት ደግሞ በአፀፋው የአስዋን ግድብን እንዲመታ ሕጋዊ ፍቃድ መስጠቷን ልታውቅ ይገባል” ብለዋል።
አያይዘውም፤ “ግብፅ በወታደራዊ እቅዷ ከገፋችበት በኢትዮጵያ በኩል አማራጭ መንገዶችን መመልከት ተገቢ ነው። ለምሳሌ፤ ከሰሜን ኢትዮጵያ መነሻ አድርገህ ላቲቲውዱን በ14.3000 ዲግሪ እና ሎንግቲውዱን በ36.6167 ዲግሪ ብትወስደው እንዲሁም አስዋን የሚገኝበት ላቲቲውድ 23.9706 ዲግሪ እና ሎንግቲውዱን 32.8779 ዲግሪን አቀናጅተህ ብታሰላው በአየር ላይ ያለው ርቀት ከ1100 እስከ 1500 ኪሎ ሜትር የአየር ርቀት ነው ያለው። በዚህ ውጤት መነሻ የኢትዮጵያ መንግስት ከ1500 ኪሎ ሜትር የሚወነጨፍ የስከድ ሚሳኤሎችን መታጠቅ ብቻ በግብፅ አሰዋን ግድብ ላይ ተመጣጣኝ ሃይል ሊፈጥር ይችላል።”  ብለዋል።
ወታደራዊ የአየር ርቀቱን ለመለካት የተሄደበትን አሰራር ቢያብራሩት ተብለው ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፤ “ይህ ሮኬት ሳይንስ አይደለም። http://www.movable-type.co.uk/scripts/latlong-gridref.html በሚለው ድረ ገጽ ዲግሪውን በመጠቀም ማስላት ይቻላል። ቁም ነገሩ ግን ወታደራዊ አማራጭ ሁለቱንም ወገኖች ተጠቃሚ አያደርግም። ብቸኛው አማራጭ በዲፕሎማሲ ደረጃ ለመፍታት መሞከር ነው” ሲሉ ኤክስፐርቱ አሳስበዋል።
በአሁን ሰዓት በዓለማችን ላይ ከ1ሺ 500 ኪሎ ሜትር እስከ 15ሺ ኪሎ ሜትር የሚወነጨፍ ሚሳኤል የታጠቁ ሀገሮች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ ፈረንሳይ፣ ሕንድ፣ ኢራን፣ እስራኤል፣ ሰሜን ኮሪያ፣ ቻይና፣ ፓኪስታን፣ ሩሲያ፣ ሳዑዲአረቢያ እና አሜሪካ ይገኙበታል።n
ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም
ግብፆች የያዙት የተሳሳተ መንገድ እንደማያዋጣቸው ገለፁ
በጋዜጣው ሪፖርተር
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ግብፃዊያን ከሰሞኑ በቴሌቭዥን ቀጥታ ስርጭት ላይ ኢትዮጵያንና የሕዳሴውን ግድብ በተመለከተ የሚናገሩት ነገር ትክክል አለመሆኑን እና እርሳቸውንም ጉዳዩ እንዳሳዘናቸው ተናገሩ። ግብፃዊያን እየተከተሉ ያሉት መንገድ እንደማያዋጣቸው ገልፀዋል።
ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ከትናንት በስትያ በራዲሰን ብሉ ሆቴል የአፍሪካ ሕብረት 50ኛ ዓመት ክብረ-በዓልን በሚዘክረው “JUBILEE” በተሰኘው መፅሔት የምረቃ ስነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ነው። እንደ እርሳቸው ንግግር ከሆነ ግብፆች አሁን እያደረጉ ያሉት ነገር ትክክል አይደለም። በኢትዮጵያ ላይ የተለያዩ ነገሮችን ማወጅ እንደማያዋጣቸውና እንደማይጠቅማቸው ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
ዶ/ር ቴዎድሮስ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስተር አቶ መለስ ዜናዊን ጠቅሰው እንዳወሱት፣ ኢትዮጵያ እና ግብፅ በአባይ ወንዝ ላይ ተጠቃሚዎች እንጂ አንዱ የበላይ ሌላው የበታች ሆኖ የሚኖርበት ዘመን ማብቃቱን ጠቁመዋል። ይልቅስ የተፋሰሱ ሀገሮች በጋራ የሚጠቀሙበትን አግባብ መኖር ነው ያለበት እንጂ ሁልጊዜ ግብፆች የበላይ ሌላው የበታች ሆኖ መቀጠል እንደማይቻል ከንግግራቸው መረዳት ይቻላል።
ከሰሞኑ በቀጥታ የቴሌቪዥን ሥርጭት ከግብፅ ሀገር የተላለፈው ዘገባ እንደሚያሳየው፣ ፕሬዚዳንት ሙርሲ ካቢኔዎቻቸውን ሰብስበው በማወያየት ኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ለመፈፀም ታጥቀው መነሳታቸውን ያስረዳል። ከፕሬዝዳንት ሙርሲ ጋር የተሰባሰቡት የግብፅ ባለስልጣን እንደሚናገሩት ከሆነ ኢትዮጵያን በልዩ ልዩ ሁኔታዎች ማጥቃት እንደሚገባ አብዛኛዎቹ በሙሉ ስሜታቸው ሲናገሩ ታይተዋል። ኢትዮጵያን ማጥቃት መንገድ ብለው ከያዟቸው አቅጣጫዎች መካከል በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሱትን ኦነግን፣ የኦጋዴን ነፃ አውጭ ግንባርን መደገፍ፣ የኤርትራን መንግስትን መርዳት፣ ሱማሊያ ውስጥ ያለውን አልሸባብን ማስታጠቅ እና ሌሎም ተጠቅሰዋል።
ይህ የግብጻዊያን እብሪትና ትዕቢት ያናደዳቸው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ይህ የግብፃዊያን እስትራቴጂ ፈፅሞ ልክ ያልሆነ፣ የአንዲትን ሉአላዊ ሀገር መረጋጋት ለመረበሽ መጣር ለክፍለ አህጉሩ አለመረጋጋት የሚያጋልጥ አካሔድ መሆኑን ጠቁመዋል። ከዚህ ሌላም የእነዚህ የግብፃዊያን አካሔድ ወደ ተሳሳተ መንገድ የሚመራቸው በመሆኑ ሊመከሩ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በአዳራሹ ውስጥ ለታደሙት የኢትዮጵያ ምሁራን እና ለአፍሪካዊያንም መልዕክት አስተላልፈዋል። ምሁራኑም በዚህ በፀረ ኢትዮጵያዊ በሆነ መንገድ የሚጓዙን ግብጻዊያን የሚመክርና እውነታውን የሚያስረዱ ጥናቶችና የምርምር ስራዎችን እንዲሁም ፅሁፎችን እንዲያቀርቡ መክረዋል።n
ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ የዛሬ ጁን 12፣ 2013 ዕትም

18 Comments

 1. If woyane choose military option, they can send AGAZI , the poor Ethiopians already sacrified for the zero value Ethio-Eritria war. we know them very well, they are addicted of war, addicted of blood sheds. If war begins tomorrow , the victims are the poor, Ethiopians.
  we need peace, we need justice, we need democracy

  • dedeb koshasha ye banda banda diftete astelita nehe! ye honk kurbetam hode yizek lehachehn tazirekerikalek-dedeb gala!

   • @sayint
    Do not be emotional, try to put your counter argument than cursing and using un acceptable words

   • @sayint
    የራስህን ክብር የማታውቅ ባለጌ ነህ/ሽ፡፡ ይህን ዓይነት ክብረ ነክ ስድብ የሚታገስ ኢትዮጵያዊነት በዚህ ዘመን የለም፡፡ ከሞራል አኳያስ በእውነቱ ይህን ስድብ ማስቀመጥ ነበረብህ/ሽ? ከዚህ ጭንቅላት ማር ይፈልቃል ብሎ መጠበቅስ ይቻላል? አሳፋሪ

 2. በለው! እንዲህ ነው እንጂ ጦርነት መናፈቅ! አቦ እርቀቷን ሁሉ ቁልጭ አርገው አስነበቡን እኮ! ግን አንድ ጥያቄ አለኝ፤ ያው አየር ሃይላችን የከተመው መቀሌ ላይ ነው፤ ታዲያ እኒህ እርቀት ለኪያችን፤ በዳበሳው ከሰሜኑ ብለው ለምን አለፉት? ለምንስ ከሁመራ እንዲነሳ ቢነሳ ብለው አሰሉት? የዚች አይነት ጨዋታ፤ በደምብ ቢታሰብባት መልካም ነው!

  • @Teddy, Ediya! some don’t know what to write…one of them is you. Why are you worried since the distance is estimated and solution is proposed. In the worest scenario bilo mezegajet min yikefal bileh new!! hulunim neger anshewareh endet tizelkewaleh..

 3. That is 100% correct. We need to look into all options, military assault and diplomacy. I suspect we had something similar from North Korea. If not, we shall get it ASAP. Although we may not use it, it helps a lot in the diplomacy.

  Tefsaye, yehen ye naive wore, forget it. Nothing comes before our sovereignty & national interest.

 4. ጦርነት መፍትሄ አይደለም፡፡ ፕሬዝዳነት ሙርሲ በሚቃዎመቸው ሕዝብ ዘንድ ለመወደድ ብለው ዕነጂ ይህን የሃይ ቃል የተጠቀሙት ፡ እውነቱን ያውቁታል አማራጮች ሁሉ ክፍት እናዳልሆኑ፡፡ ይህን ቃል ለመጠቀም ያስገደዳቸው በሚስጥር አርገነዋል ብለው ያሰቡት ስብሰባ ተንኮል ሥለሆነ አላህ አጋለጦ በግልጽ ለዓለም ሕዝብ አሳያቸው፡ ይሕን ውርደት ለመሸፈን ነው አሁን በገሀድ አፋቸውን ሙልተው ጦርነትን እንደ መፍትሄ ወስደው የሚፎክሩት፡፡ ወይ ባሌ ፡ ከባልሽ ይበልጣል ሽሮ ስጭኝ፡ ማለት ይህ ነው፡፡ ለመሆኑ ግብጾች ውሀውን ብቻ ነው የሚፈልጉት ወይስ ለም አፈሩን?….

 5. Bemejemeriya Ene ye’gesziw party teqawami negn,yihun enji hulgize yemigermegn neger egna ethiopiawyan qegn silun gira,gira silun qegn yeminiregtew lemin yihon ?and gize ye ethiopia mengist be’egypt lay yalew aquam “telemamachinet new”eyalin enichohalen,wetaderawi aqim alegn sil degmo “torinet nafaqi”enilalen .be ewnet lerasachin aquam enkuan tamagninet yelenim.ene yebizowochachihun astesaseb say memar min yiteqmal eyalku asibalehu.adame calculation shemidideh siletemereqk mihur yehonk endayimesilih.yetemare dedeb beztobinal.

 6. ጦርነት መፍትሄ ባይሆንም መጠንቀቅ ከቁጭት ያድናል::

 7. የአባይ የፖለቲካ ጉዳይ ግቡን እየመታ ነው ህዝባዊ ትኩረት በብሄራዊ ስሜት እንዲዋጥና የፍትህና የዲሞክራሲ ጥያቄዎች እንዲቀጭጩ ማድረግ ህወሃት /ኢህአዴ በግብጽ ምክንያት የአደጋ ጊዜ መንግስት በመሆን በግልጽ በወታደራዊ ጄኔራሎች መመራት ይጀምራል ወታደራዊ ባጀት በእጥፍ ያድጋል የአባይ ግንባታ ባይቋረጥ እንኩዋን አያልቅም።

  • Now it is not a time to analyze the future and give blind guess with out no knowledge about the current reality ,but rather to deal with aggressive and arrogant approach of Egyptian.

 8. Former millirary experts are still better than weyane generals. We want our men back. They were Ethiopia militaries not derg. It is just a profession that any government can use. They are military proffesionals not poleticians.

  • @Gudu
   They are in late 60’s and 70’s some of them in nursing home. What do you want to do with them.

 9. Do u think Egypt will open war? Never and ever but will continue its evil work by supporting those separatist groups to jeopardize z peace in Ethiopia. I have seen some OLF members start bowing to Egypt that they are not Ethiopian and do not want the building of the dam over the Nile. Shame on them

 10. እኛ ኢትዮጵያዊያን ከጎናችሁ እንሰለፋለን በዚህ ቀልድ የለም ጥሪ ብቻ ይበቃል

Comments are closed.

4278
Previous Story

EHSNA 3rd Annual Festival 2013

Next Story

በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በምርጫ እንዲሳተፉ ሊደረግ ነው

Latest from Blog

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ የውጪ ግንኙነት የቤተክርስቲያኒቱን የሺሕ ዘመናት ታሪክ እና እሤቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርባታል!!

በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) (ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደጻፈው) እንደመንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው ጽሑፌ መነሻ የሆነኝ- ባሳለፍነው ሳምንት በአፍሪካ ኅብረት ኔልሰን ማንዴላ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለአንድ ቀን የተካሄደው፤ ‹‹የአፍሪካ  መንፈሳዊ ቀን/The African Spiritual

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ | ስለአማራ ክልል ከነዋሪዎች የተሰማው | አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል” | “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል”| “እጅ ከመስጠት ውጭ አማራጭ አይኖረንም” ፊ/ማ “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |
Go toTop