June 3, 2013
1 min read

በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ በገለልተኝነት ያሉ አብያተ ክርስቲያናት እንዲቀላቀሉት ጥሪውን አቀረበ (መግለጫውን ይዘናል)

(ዘ-ሐበሻ) በዳላስ ቴክሳስ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ጉባኤውን አድርጎ ያጠናቀቀው በብጹዕ ወ ቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ የሚመራው ሕጋዊው ሲኖዶስ ባወጣው ባለ 8 ነጥብ መግለጫው በገለልተኝነት ያሉ አብያተ ክርስቲያናት የቅዱስ ሲኖዶሱን ጥሪ በአንድነት ተቀበለው፤ ለትውልድ የምትተላለፍ አንዲት፣ ቅድስት፣ ሐዋርያዊትና ኩላዊት ቤተክርስቲያንን የሚጠቅም፤ እንዲሁም አገርንና ወገንን የሚጠቅምና የሚያኮራ ሥራ ለመሥራት ቅዱስ ሲኖዶሱን እንዲቀላቀሉ ጥሪውን አቀረበ።

ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

1 Comment

  1. እኛስ በእውነት የተዋሕዶን ሥረዓት እንከተላለን! አቡነ መርቆርዮስ ከመንበራቸው በርግጥ ተባረዋል ተሰደዋል። ልብ በሉ ተባረዋል ተሰደዋል። ጥያቄው ይመለሱ ከሆነ ትክከል ነው። ኢትዮጵያ ካሉት አባቶች ጋር በሆነው መንገድ እንደገና የሰላም ንግግር አድርገው የአስታራቂው ኮሚቴ ሥራ ጀምሮ ውጤት ላይ ቢደርሱ፤ምንም አይነት ስምምነት ይሁን፤ ብቻ ሁለቱ ወገኖች ከተስማሙ እሰየው ነው። እንግዲህ ሁሉ ሲሆን በየትኛውም መንገድ ቢሆን ወይ ወደመንበራቸው ይመለሳሉ፣ወይ በተስማሙበት የድርድር ውጤት መሰረት ይሆናል። ሁለቱም ቢሆን ግን ተፈጻሚነቱ መንበሩ ኢትዮጵያ ሆኖ ነው። ይመለሱም ቢባል፣እርቅም ቢወርድ መጨረሻው ያው መንበረ ፕትርክናው ኢትዮጵያ ነው የሚሆነው። ቀድሞም የነበረው ወደፊትም የሚሆነው። ስለዚህ አሁንም ቢሆን መንበሩ ኢትዮጵያ ነው ማለት ነው።ታዲያ እንዲህ ከሆነ የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን መንበር እንዴት አሜሪካ ነው ይባላል? ይህ ቁልጭ ያለ ስህተት ነው! ስለዚህ ነው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን መንበር ከኢትዮጵያ በፍጹም አይሰደድም የምንለው። ይህ ማለት ግን ከላይ እንዳልኩት አላዊ መንግት ሲመጣ የቤተክርስቲያኗ መሪ ወይም ጳጳሳት አይሰደዱም ማለት አይደለም። በተባረሩት ወይንም በተሰደዱት አባቶች ቦታና ወንወበር በአላዊው መንግስት የተቀመጡና የሚቀመጡም ትክክለኛ ናቸው ማለት አይደለም። ስለዚህ ጳጳሳት ይሰደዳሉ እንጂ መንበር ወይንም ሲኖዶስ አይሰደድም! በተባረሩና እንዲሰዱ በተደረጉ ቦታም የተቀመጡ እውነተኞች/ ትክክለኛ ሥርዓትን የተከተሉ አይደሉምና ሁለቱንም አንቀበልም። ይህ አቋም ፍጹም ክርስቲያናዊና ትክክለኛ አቋም ነው። የተሰደዱ አባቶች ልማድ ተገቢ ከሚያደርገው አገር ውጪ ስለተሰደዱ ሌላ ሲኖዶስ አላቋቋሙም። በተባረሩት ወንበር ላይም የተቀመጡትን ከርስቲያኖች አልተቀበሏቸውም። ይህ ሥርዓተ የቤተክርስቲያን ነው። ይህ ለሰው ሳይሆን ለቤተክርስቲያንና ለሥርዓቷ መቆም ነው። ሁለቱም ወገኖች ያጠፉትን አለመቀበል እውነተኛነት ነው። በሁለታችሁም በኩል የተፈጸመውን ስህትት አንቀበልም። ይህ በአባቶቻችን በነ ቅዱስ አትናቴዋስ( አምስት ጊዜ ከመንበሩ ተሰዷል) በአባታችን በቅዱስ ዶዮስቆርዮስ በአባታችን በቲቶ ዘመነ ፕትርክና በአሊክሳንድሪያ የሆነ ነው። አላውያን ነገሥታት ከስልጣናቸው ቢያወርዷቸው ልጆቻቸው ክርስቲያኖች በአላውያን የተሾሙትን አልተቀበሉም። የተባረሩት አባቶችም ሲኖዶሱ /መንበሩ ከእኛ ጋር ተሰዷል ብለው ሌላ ሲኖዶስ ሌላ መንበር አላቋቋሙም። በፈቃደ እግዚአብሔር ወደመንበራቸው ተመለሱ፣ሥርዐትን ሳያፈርሱ በኃይማኖት ጸንተው ተገኙ እንጂ። አሁን በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እየሆነ ያለው ግን ተበዳይም የቤተክርስቲያንን ሥርዐት በዳይ ሆኗል። በዳይም ከበደሉ አልተመለሰም። ስለዚህ ሁለቱንም ወገን ወይ ሥርዐት ያዙ ወይ ታረቁ ማለትና ከጥፋታቸው ጎን አለመቆም ትክክለኛ የአባቶቻችን ታሪክ ነው። ይህንም ከጥፋተኞች መገለል ከቤተክርስቲያን መገለል እንደሆነ አድርገው ለማሳየት መሞከርና ኑና አብረን እናጥፋ ማለት በበደል ላይ በደል መጨመር ነው። ይልቅስ ያጠፋችሁትን አርሙና ማኅበረ ካሕናት አቋቁሙና ሁላችንም አንድ ላይ ሆነን በትክከለኛው ወንበር ላይ የተቀመጡትን ሳይገባችሁ ነው ወንበሩን መልሱ ሰላምና አንድነት እንዲፈጠር አድርጉ እያልን እንጠይቅ። ያን ጊዜ እግዚአብሔርም እነኚህ በውነት ተገፍተዋል ሥርዓቴንም ጠብቀዋል ፍትህ ይገባቸዋል ይልና የምህረት ፊቱን ይመልስልናል። ያልተገባቸውንም ያስተካክላቸዋል። ችግሩን የፈጠሩትንም ይቀጣቸዋል። አሁን ለእግዚአብሔር የቸገረው ነብዩ ሁሉም በደሉ በአንድነትም ረከሱ እንዳለው ምህረት ለማን ላድርግ እያለ ነው። እናም የኢትፖጵያ ሲኖዶስ /መንበር የሚገኘው በኢትዮጵያ ነው። ፓትርያርኩ ግ ተሰደዋል። ሁለቱ እንዲገናኙ እንፈልጋለን ። ያ እስኪሆን ግን እንደአባት ሁላችሁንም እንቀበላለን ያጠፋችሁትን ግን ማረም አለባችሁ እንጂ ኑና አብረን እናጥፋ አይባልም። ወደፊት በሰፊው በዚህ ጉዳይ ላይ አትትበታለሁ። ከበቂ ማስረጃ ጋር። ይቆየን።

Comments are closed.

Previous Story

ሸንጎ በአ.አ የተደረገውን ሰልፍ “በሺዎች የተጀመረው እንቅስቃሴ የሚሊዮኖች ይሆናል” አለ

979885 10200726530979603 470373367 o
Next Story

የፖለቲካ ኃይል ሽግሽግ ትግል – ቁጥር 01

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop