ቀጣዩ ታሳሪ ወይም ፈርጣጭ የፍትህ ሚ/ሩ ብርሃን ኃይሉ?

አቶ ብርሃን ለቃሊቲ በሮች ተቃርበዋል

በአዲስ አበባ ዛሬ ታትሞ የወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ እንደዘገበው በቅርቡ ከስልጣን የተነሱት የፍትህ ሚኒስትር አቶ ብርሃነ ኃይሉና ከአስር በላይ አቃቤ ህጐች በሙስና፣ በሽብርተኝነትና በግድያ ወንጀል በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ የተመሰረተን ክስ ያለአግባብ አቋርጠዋል በሚል በፖሊስ ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ምንጮቹን ጠቅሶ ዘገበ፡ ፖሊስ በሚኒስትሩና በአቃቤ ህጐቹ ቢሮ ባካሄደው ከፍተኛ ብርበራ በርካታ መዝገቦችን ማግኘቱንና ለምርመራ መውሰዱን ምንጮች ተናግረዋል ያለው ጋዜጣው በፖሊስ ብርበራ የተገኙት መዝገቦች ያለአግባብ ተቋርጠው እንዲዘጉ የተደረጉ ክሶች ናቸው ተብሏል፡፡

ተከሳሾች ላይ በቂ ማስረጃ ማቅረብ ካልተቻለ ክሶቹን አቋርጦ መዝገቡን መዝጋት የፍትህ ሚኒስትርና የአቃቤ ህጐች ስልጣን መሆኑ ቢታወቅም ከሙስና፣ ከሽብርተኝነትና ከግድያ ጋር የተያያዙት እነዚህ በፖሊስ ብርበራ የተገኙ ከደርዘን በላይ የሆኑ መዝገቦች ግን፣ በቂ ማስረጃ እያለ፣ ያለ አግባብ የተቋረጡ ናቸው ተብሏል ያለው የጋዜጣው ዘገባ ምርመራው ተጠናቆ እንዳበቃ በሚኒስትሩና በአቃቤ ህጐቹ ላይ ክስ እንደሚመሰረትም ምንጮች ጠቁመዋል ብሏል። ለሰራተኞች አቤቱታ ምላሽ ባለመስጠትና በሥራ ድልድል በደል ፈጽመዋል በሚል ቅሬታ ይቀርብባቸው የነበሩት የፍትህ ሚኒስትሩ፤ በተለይ የጥብቅና ፈቃድ አሰጣጥ ላይ ይታያሉ የተባሉ ችግሮችን እንዲፈቱ አራት የማሳሰቢያ ደብዳቤዎች ተጽፎላቸው እንደነበር ምንጮቹን ጠቅሶ አዲስ አድማስ ጋዜጣ ዘገቧል።

በቅርቡ በተካሄደው የኢህአዴግ ዘጠነኛ ጉባኤ ላይ ከፓርቲው መሪዎችና አባላት ለሚኒስትሩ የቃል ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸው እንደነበር ጋዜጣው ጠቅሶ ፓርላማም የመ/ቤቱ በርካታ ችግሮች መፈታት እንዳለባቸው ማሳሰቡን ጠቅሷል።
በዚህ ዓመት ብቻ ሶስት ሚኒስትሮች በወንጀል ተጠርጥረው ከስልጣን የወረዱ ሲሆን፣ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ጁነዲን ሳዶ ከአገር መኮብለላቸው ይታወሳል፡፡ ቀጣዩ ባለሳምንት እንደጁነዲን ፈርጣጭ ወይም እንደ መላኩ ዘውዴ ቃሊቲ የፍትህ ሚ/ሩ ብርሃን ኃይሉ?

ተጨማሪ ያንብቡ:  Sport: የብሔራዊ ቡድናችን አማካይ አዲስ ሕንጻ ለሱዳኑ ክለብ ለመጫወት በ$100 ሺህ ዶላር ፈረመ

የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች አስተያየት ይጠበቃል።

5 Comments

  1. sinte ye weyane tigre musenchoch ministroch molteu eyalu-agobdage ministroch yitaseralu-ye fandya weyane sira endew sekefe-kefafewoch nachew!

  2. If you are really serious about fighting corruption, prepare more prison space and do not forget Azeb, Sebhat, Abay Woldu, Bereket, Seyoum etc. etc. in short all woyane ethnic fascists. If they want to join diaspora, they better flee to China where their corruption partners live.

  3. The old saying goes :”The Fish Smells(stincks) from the Head”. There is nothing particularly wrong with this or that minster. They were not meant to be a minster! Period!! They were put in that postion without education/ qualification/experience. That is true to ALL EPRDF! Period!!

    .You Can Not make an omlet ( frfir) from a Rotten EGG! Period! You Just Discard It!! Period!!

Comments are closed.

Share