የነመላኩ ፈንታን የሙስና ጉዳይ ከማጣራት ቢላደንን ማግኘት ይቀል ነበር ማለት ነው?

(ከአዘጋጁ፡ ይህ ጽሁፍ በኢሜይል የደረሰን ነው፤ ጽሁፉ ጸሐፊውን አይገልጽም። ለሀገር ቤት ኢሜይል ያደረገልልንን ሰው የጸሀፊውን ስም እንዲነግረን ብንመይልለትም ከዛ በኋላ ምላሽ አልሰጠንም። ለማንኛውም ያንብቡት።)

የኢትዮጵያ ታሪክ መቼም አያልቅም፡፡ ታዲያ በዚህ በማያልቀው ታሪክ ውስጥ በጣም ብዙ የሰማሁች ታሪክ ቢኖር በኢህአዴግ ዘመን ነው ብል ማጋነን አይሆንም፡፡ ኢህአዴግ ስልጣን ከጨበጠ 22 አመት ሞልቶታል፡፡ ታዲያ በዚህ ወቅት ላይ “ትልቅ ሙስና” ብሎ ታላላቅ ባለስልጣናትን ወደ ማረሚያ ቤት አወረደ፡፡ መቼም ይህንን በማድረጉ ኢህአዴግ “ዴሞክራት ነው” የዚህ አይነት እርምጃ የሚወስድ መንግስት የለም ሊባል ይቻላል፡፡ ግን የኢህአዴግ የሙስና ጉዳይ ልክ እንደ ቼዝ እየዘገየ የሚደረግ ነገር ነው፡፡ በአለማችን ረጅም ጊዜያት የሚቆይ ጨዋታ ቢኖር ቼዝ ነው፡፡ የአለማችን የቼዝ ሻምፒዮን ሩሲያዊው ሰው ለሰባት አመት በቆየ የቼዝ ጨዋታ አሸናፊ ሆኗል፡፡ ታዲያ ከዚህ ቀደም በ1987 ዓ.ም. የቀድሞ ታምራት ላይኔ ከሙስና ጋር በተያያዘ ወደ ዘብጥያ ወረዱ፡፡ ከሰባት አመት በኋላ ደግሞ በ1994 ዓ.ም. ላይ የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትሮችና ስዬ አብርሃ ከቤተሰባቸው ጋርና ከሌሎች ባለስልጣናት ጋር ወህኒ ወረዱ፡፡ ይህ ሲሆን መቼም ያልተገረመና ያልተደነቀ ሰው የለም፡፡ ይሁንና ታዲያ ከአስር አመት በኋላ ግን ዳግም የሙስናን ጉዳይ ሰማን ወይም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ከሙስና ጋር መታሰራቸው ነበር፡፡
በርካቶች የኢህአዴግ ጠንካራ እርምጃ በሙስና ላይ ወሰደ ሊሉ ይችላሉ፡፡ከሙስና ጋር በተያያዘ ግን የታሰረው ወገን ስንናገር “ይሄ ቼዝ አውራዎቹንና ዋናዎቹን” ብለን እንድናስብ ያደርገናል፡፡ ከሁሉ ከሁሉ ግን የገረመኝና ያስደነቀኝ ነገር ቢኖር እነዚህ ሰዎች ከሙስና ጋር በተያያዘ ወደ ወህኒ ከወረዱ በኋላ የፀረ ሙስና ኮሚሽነሩ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ቀርበው ያሉት ነገር ነው፡፡ “ይህ ጉዳይ ጠ/ሚ መለስ በሕይወት በነበሩበት ወቅት ከአንድ አመት ከስምንት ወር በፊት የተጀመረ ነገር መሆኑን” ገለፁ፡፡ በዚህን ያህል ጊዜ ውስጥ ደግሞ እርምጃዎች ያልተወሰዱት ጠ/ሚ መለስ ተረጋግታችሁ በስህተት ሰውን እንዳታገላቱ ብለው በማለታቸው እንደሆነ ተናገሩ፡፡
ይህ የእሣቸው አነጋገር ግን አንድ ነገር በአእምሮዬ ውስጥ እንዳስብ አደርገኝ፡፡ ሙስኛን ወይስ አሸባሪን መያዝ ይከብዳል የሚል፡፡ መቼም ሙስናን የሚፈፅምን ሰው በርግጠኝነት በሕብረተሰቡ ዘንድ መረጃ ከተገኘበት ቀላል ነገር ነው፡፡ የሽብር ተግባር የሚፈፅምን ሰው መያዝ ግን በአሁን ሰአት እንኳን ለኛ ለአሜሪካ የከበደና አሜሪካንን ሆድ ያስባሰው ቢላደን እንኳን ከስንት አመት በኋላ እንደተገኘና እንደሞተ የምናውቀው ነገር ነው፡፡ ታዲያ አሁን ምን ታዘብን ብትሉ ከሽብርተኛ ሙስና በለጠ የሚለውን ነገር ነው፡፡ ይህንን ነገር ደግሞ በምንም ሣይሆን ከባለፈው የፀረ ሙስና ኮሚሽን ሊቀመንበር የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መግለጫ ማወቅ የምንችለው ነገር ሆኗል፡፡ ታዲያ ምናልባትም እሣቸው አንድ የገለፁት ነገር አለ፡፡ ይህ ነገር ወይም ክትትሉ የተጀመረው ጠ/ሚ መለስ በሕይወት በነበሩበት ወቅት መሆኑንና በፍጥነት ሄዳችሁ ሰው ማጉላላት የላባችሁም ማለታቸውን ገለፀ፡፡ ስለጠ/ሚ መለስ ራእይ ምናልባትም ተራው ለመናገር የፀረ ሙስና ኮሚሽን ሊሆን ይችላል፡፡ ግን ከሽብርተኛና ከሙስኛ የትኛውን ወገን መያዝ ወይም በፍጥነት ማወቅ ይቻላል የሚለውን እናስብ ይህንን ነገር ስናስብ ደግሞ ጉዳዩን የምንመለከተው ከሰብአዊ ወይም ከምርመራና ከውሣኔ አንፃር ሊሆን ይችላል፡፡ መቼም ኢትዮጵያ እንግዳ ተቀባይ ሀገር ናትና ከአሜሪካ ጀምረን ወደኛ እንመለስ፡፡
ባራክ ኦባማና ኦሳማ ቢላደን
በ2000 ወይም በፈረንጆቹ ሚሊኒየም በአሜሪካ የደረሰው ነገር መቼም ለመላው አለም ይዞት የመጣው ነገር ጥሩ አይደለም፡፡ በአሜሪካን የሽብር ጥቃት ደረሰ በርካታ ሰዎችም ሕይወታቸው አለፈ፡፡ አሜሪካ የምትታወቅበት የኒውዮርክ መንታ ህንፃዎች ሣይቀር የዚህ ጥቃት ሰለባ ሆኑ፡፡ አለም ሽብርተኝነት የሚለውን ትርጉም ወይም “አሸባሪ” የሚለውን ነገር ያወቀው በዚህ ጊዜ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ይሁንና ግን ታዲያ ይህንን የሽብር ተግባር ማን ፈፀመው የሚለው ነገር ሲነሣ “ኦሣማ ቢላደን” መሆኑ ተረጋገጠ፡፡ ከሽብርተኝነትም በላይ የድፍረትም ያህል የቆጠረችው አሜሪካ ከሁልጊዜ ሸሪኳ እንግሊዝ ጋር በመሆን አልቃይዳ ይገኘበታል ያላቸውን አፍጋኒስታን ላይ ጥቃት ለማሰንዘር “በተባበሩት መንግስታት ድርጅት” ተ.መ.ድ አማካይነት ዘመቻ ጀመረች፡፡ ይህ ሁኔታ ሁሉም ዜጋ የሞተበትና የተፈፀመው የሽብር ጥቃት ከዚህ ቀደም የማይታወቅ በመሆኑ ድምፀ ተአቅቦ ማድረግ ሽብርተኝነትን ማበረታታት በመምሰሉ ውሣኔው ፀደቀ፡፡ ይሁንና የአሜሪካና እንግሊዝ ጦር ወደ አፍጋኒስታን ዘልቆ ገባ፡፡
የታሊባን ኃይሎች ወይም ለአልቃይዳ ቦታ ሰጡ የተባሉት ኃይሎች እየተሸነፉ ጭምር የተባበሩት ኃይሎች ድል እያገኙ መጡ፡፡ ግን ይህ ድል ለአሜሪካ አንጀት የሚያርስ አይደለም፡፡ ለአሜሪካዊያንም ሆነ ለሌሎች ወገኖች ደስታው ይህን የሽብር ጥቃት በመንደፍ የአሜሪካ መለያ የነበሩትን መንታ ፎቆች ሣይቀር ያወደመውን አሸባሪው ኦሳማ ቢላደንን መያዝ ነበር፡፡ ይህ ግን አልሆነም፡፡ በአፍጋኒስታን ታሊባን ወርዶ የሽግግር መንግስት ቢቋቋምም ቢላደን አለመገኘቱ የኪሳራ ያህል ነበር፡፡ የሪፖብሊካኑ የጆርጅ ቡሽ አስተዳደር በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ጥሮ ምንም ሣይሣካ ወረደ፡፡ ከዛ በመቀጠል የኦባማ አስተዳደር ተተካ፡፡ ይሁንና ኦባማ ሙሉ ትኩረታቸውን በዚህ ጉዳይ ሣያደርጉ ስራ ጀመሩ፡፡ ይሁንና ግን በ2010-11 ላይ አንድ ያልተጠበቀ ዜና ተሰማ፡፡ ይህ ዜና ደግሞ አሜሪካ ትፈልገው የነበረው አሸባሪው ኦሳማ ቢላደን መገደሉንና ይህንን ያደረገው የአሜሪካ ጦር መሆኑን ተናገሩ፡፡ የኦባማ ቃል ለአለም አስገራሚ ነበር፡፡ ምክንያቱም ኦባማ ሲገልፁ ኦሣማ ቢላደን ያለበትን ቦታ አውቆ በእሱ ላይ እርምጃ ለመውሰድ የአንድ አመት ጊዜ መውሰዱን ጭምር ገልፀው ነበር፡፡ ኦሣማ የሚኖርበት ቦታ ላይ ማስረጃ /መረጃ/ ካገኘን በኋላ የዚህን ያህል አንድ አመት የቆየው እሱና ቤተሰቡ ለመሆናቸው ማረጋገጫ ማግኘት ስለነበረብን ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡ አንድ አመት መቆየቱን ግን ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ ሊያውም አቅም ያለው አሸባሪን በሚመለከት፡፡ ታዲያ በኛ ሀገር ባለፈው ሰሞን የፀረ ሙስና ኮሚሽነር የሆኑት አሊ ሱሌይማን ሲገልፁ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የሆኑት አቶ መላኩ ፈንታና ምክትላቸው የሆኑት ሰዎችን ለመያዝ አንድ አመት ከስምንት ወር መፍጀቱን ገልፀዋል፡፡ ይህ ስራ የተጀመረው ጠ/ሚመለስ በሕይወት በነበሩበት ወቅት መሆኑንና መለስም ዝም ብላችሁ የራሣችሁን ነገር አታድርጉ በጥንቃቄ ማድረግ አለባችሁ ማለታቸውን ገልፀዋል፡፡
ምናልባትም የእሣቸው ጉዳይን ከመለስ ጋር ማያያዝ ምናልባት ከውለታ ጋር እናገናኝ፡፡እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የሙስና ተግባራት ይከናወናል ተብሎ ከሚጠበቅባቸው ተቋማት መካከል የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ነው፡፡ በየአመቱ የየሀገራችን የሙስና ጉዳይ የሚመረምረው ተቋም የአለም ባንክ በኢትዮጵያ ባለፉት አስር አመታት ውስጥ ሙስና የተፈፀመበትና ከባድ ምዝበራ የሚከናወነው የገቢዎችና ጉምሩክ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ይህ ነገር ደግሞ መቼም በስልጣን ላይ ለሚገኘው መንግስት የማንቂያ ደውል ሊሆን ይችላል፡፡ በዛው መጠን መለስ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን መ/ቤት ላይ ትኩረት አደረጉ፡፡ ታዲያ የአለም ባንክ ሪፖርት ግን አስር አመት ነው፡፡ አሁን በቁጥጥር ስር የዋሉት መላኩ ፈንታና “ግብረ አበሮቻቸው” ሣይሆን የስራ ባለደረቦቻቸው ከተሾሙ ደግሞ ገና ሦስት አመታቸው ነው፡፡
ይህ ጉዳይ በፍርድ ላይ የተያዘ ነው፡፡ ምናልባት የፍርድ ሂደቱን ተከትሎ ብዙ ነገር ማለት ቢቻልም ስናየውና ስንገነዘበው ገና ውሣኔያቸው አልታወቀም፡፡ በኢትዮጵያ ወይም በኢህአዴግ አሠራር ከሆነ ግን አሜሪካ ወይም ኦባማ መኖሪያውን አረጋግጠው ከያዙት ቢላደን ይልቅ ጠ/ሚ መለስ ጀምረው የእሣቸው ሕይወት ካለፈ ወይም በሕይወት ጀምረውት አንድ አመት ከስምንት ወር የፈጁት መላኩ ፈንታ በለጡ ማለት ነው፡፡ ይህ ነገር መቼም በጣም የሚገምር ይሆናል፡፡ ምክንያቱም አሜሪካ በየአመቱ ከምታወጣውና ለሌሎች ሀገሮች የምትረዳው የሽብር ጉዳይን ለመከላከል ይህ ሆኖ እንኳን በቅርቡ በቦስተን ማራቶን የሽብር ጥቃት ደርሷል፡፡ሙስና ደግሞ ቀላል ነገር ነው፡፡ ሙሰኛው ሰው ላይ ለቀናት የሚደረግ ትኩረት ግለሰቡን ያጋልጣል፡፡ ሌለው ቢቀር አካውንቱን በማስመርመር ብዙ መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡ ታዲያ አሁን የገቢዎችና ጉምሩክ ሰዎች መታሰርን ከዛም ይህን እርምጃ ለመውሰድ የፈጀውን አንድ አመት ከስምንት ወር ስናስብና አንድ አመት የፈጀውን የቢላደን መኖሪያን ስንጨምርበት የትኛው በለጠ ብለን እንድስብ ያደርገናል፡፡ ገና ያደረጉት ነገር ያልተረጋገጠው ክስ የተመሠረተባቸው እነ መላኩ ፈንታን ጉዳይ ለማወቅና ለማግኘት ኦባማ ካደረጉት የቢላደን ዘመቻ በለጠ ማለት ነው፡፡

1 Comment

  1. tsufihin anbibe alchereskum gin rubbish aynet messelegn!!!…yemiategib enjera…!!!!Ethiopia wust yale ashebari terrorist woyane naw!!!…..musegna zerafi tsere Ethiopia woyane naw!!!

Comments are closed.

David Moyes Wayne rooney 008 1
Previous Story

Sport: ሞዬስ እና ሩኒ ይስማሙ ይሆን? – የማንችስተር ዩናይትድ ውስጣዊ ጉዳይ

kenenisa bekele wins
Next Story

Sport: ቀነኒሳ በቀለ ያሸነፈበትን ሙሉውን የሩጫ ቪድዮ ይመልከቱ

Latest from Blog

አዲስአበባ ተኩስ ተከፈተ “ለመደራደር ዝግጁ ነን” አረጋ ከበደ | አብይ አደገኛውን ካርድ መዘዙ | አዲሱ አዋጅና የቀረበበት ተቃውሞ “የሞተም ሰው ንብረት ይጣራል | ጌታቸው ያጋለጠው ጸብ

አዲስአበባ ተኩስ ተከፈተ “ለመደራደር ዝግጁ ነን” አረጋ ከበደ\  አዲሱ አዋጅና የቀረበበት ተቃውሞ “የሞተም ሰው ንብረት ይጣራል አብይ አደገኛውን ካርድ መዘዙ ጌታቸው ያጋለጠው ጸብ

ከመጠምጠም መማርን እናስቀድም!

;በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) አብዛኛው አንባቢ ተገንዝቧል ብዬ እንደምገምተው ሕዝብ ለቡና ቲራቲም፣ ለግብዣ፣ ለበዓል፣ ለሰረግ፣ ለሐዘን፣ ለእድር፣ ለእቁብ ለውይይትና ለሌሎችም ማህበረሰባዊ ጉዳዮች ሲገናኝ የሚበዛው አድማጭ ሳይሆን ተናጋሪ  ወይም ደግሞ ለመናገር  መቀመጫውን ከወንበር ወይም
Go toTop