ዳግማዊ ጉዱ ካሣ
ምንድነው ይሄ በየሄድኩበት የማየው ሀገራዊ ጉድ? የዚህ ሁሉ አፍዝ አደንግዝ መንስኤ ምን ይሆን? በእውነት ኢትዮጵያ የማን ወይም የነማን ናት? እንታይ ኢዩ ጉዱ! እንታይ ኢዩ’ሞ ብላዕሊ ሕዝቢ ኢትዮጵያ ዝወረደ? መአዝ ኢዩ እዙይ ኩሉ ህማምን ፃዕርን ዝክላዕ ወይን ድማ ዝውገድ? ብሃፋሽኡ ኩሉ አብዚ ዘመን እዚ ዝርዐይ ዘሎ ኩነት የጭ’ንቅን የስምብድን!ጎይታና ኢየሱስ ክርስቶስ እንተዘይመፀን እንተዘይተራድኣን ብዙኃት ነገራትና ናብ አዲ ሦርያ እንዳወፈሩ ኢዮም …
እውነትም የእናት ሆድ ዥንጉርጉር ነው፡፡ ዶክተር ኃይሉ አርአያን ያፈራች ትግራይ፣ ገ/መድኅን አርአያን የፈጠረች ትግራይ፣ አስገደ ገ/ሥላሤን የወለደች ትግራይ፣ ወጣት አብርሃ ደስታን ያፈራች ትግራይ፣ በኢትዮጵያ ሲመጡበትና የመጡበት ሲመስለው አራስ ነብር የሚሆነውንና የደመ ቁጡነቱ የብዕር ወላፈን ከጠላት አልፎ ለየዋሃን ወዳጆቹ የሚተርፈውን የኢትዮሰማይ ብሎግ አዘጋጅ ጌታቸው ረዳን ያፈራች ትግራይ(የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ጌታቸው ረዳም ስላለ ነው)፣ አብርሃ በላይን የወለደች ትግራይ፣ … ስንቶቹን ዘርዝሬ እጨርሳለሁ … እነዚህን ውድና ብርቅዬ ልጆች ያፈራች ኢትዮጵያዊት ትግራይ ከዚህ በታች የምዘረዝረውን አጸያፊ ተግባር የሚፈጽሙ ምግባረ ብልሹ ልጆችን ትወልዳለች ብሎ መገመት ይከብዳል፡፡ ነገር ግን በአንድ ሀገር ጉድ ሲወለድ የጉዱን መጠን መተንበይ አይቻልምና የማንም ምድራዊ ፍጡር አእምሮ ሊሸከመው ከሚችለው በላይ ግፍና በደል የሚሠሩ የትግራይ ልጆች መላዋን ኢትዮጵያን ወርረው በመቆጣጠር አሁን የምነግራችሁንና እናንተም ከዚህ ቀደም የምታውቁትን ግፍ እየሠሩ ናቸው፡፡
[አንድ ጓደኛየ ሁለት ዶሮዎች አሉት – አንዲት ሴት አንድ ወንድ፡፡ ጥሬ ሲበትንላቸው ሴቲቱ ወንዱን አታስበላውም፡፡ እርሷ ብቻ ስትበላ እርሱ አጠገቧ ሣር ቢጤ ይነጫል፡፡ እውነቴን ነው የምላችሁ፡፡ አዘናግቶ ሊለቅም ሲጀምር አርቃ ታባርረዋለች – በመንቆሯ እየነከሰች፡፡ ሌሎች ወፎችና እርግቦች አብረዋት ሲለቅሙ ግን እነሱን ምንም አታደርጋቸውም፡፡ ከራስዋ ጋር በአንድ ቆጥ የሚያድረውን ወገኗን ግን ታሳድደዋለች፡፡ ይህ ነገር ብዙ ካሳሰበኝ በኋላ የዚህን ምግብ ላይ ያለመስማማት ጉዳይ ምክንያቱ ምን ሊሆን እንደሚችል ጓደኛየን ጠየቅሁት፤ ከኔው ጋር ተመሳሳይ እሳቤ እንዳለው ተረዳሁ፡፡ የዚህች ዶሮ ችግር የምግብ መኖር አለመኖር አይደለም፤ ችግሯ ማሸነፏን ለማሳወቅ የምታደርገው ጥረት ነው፤ በባዶ ሜዳና ባላስፈላጊ ሁኔታ እንዲህ የምትደክመው ሥነ ልቦናዊ የበላይነቷን ለሚመለከተው ሁሉ በተለይም በ‹ሰብኮንሸሷ› ውስጠኛ ክፍል ተሰንቅሮ ፍዳዋን ለሚያስቆጥራት ‹ኢድ/ኢጎ› ለማሳየት ነው፡፡ እርሷ ጠግባ ብዙ ጥሬ ሜዳው ላይ ፈስሶ እያለ እርሷ እዚያ አካባቢ እያለች ያ ምሥኪን ዶሮ ወደዚያች ምግብ ትውር አይልም – ሌሎች አእዋፋት ግን እንደልባቸው ይለቅማሉ – የሚገርም እውነተኛ የነገር ምስስሎሽ (አናሎጂ)! ፡፡ እሱም አቅሙን አውቆ ይኖራል፤ አሳዳጅና ተሳዳጅ አንዳቸው ባንዳቸው በጎ ፈቃድ ‹አብረው› ይኖራሉ – መኖር ተብሎ፡፡ ]
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ዕዝ – ቀደም ሲል በግንቦት ሰባት እንደተገለጠውና እኛ በሀገር ቤት ያለነው ወገኖችም በቅርበት እንደምናውቀው – ለይስሙላና ለታይታ አልፎ አልፎ ከሚስተዋል የታችኛው የዕዝ መስመር ላይ የሚታይ የሌላ ብሔር ተወላጅ ምደባ በስተቀር ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ሥልጣኑና የውጊያ አመራሩ የተያዘው በትግሬዎች ነው፡፡ መቶ ወታደር ካየህ – ጨዋነት በተሞላበት ግምት – መላ አመራሩን ጨምሮ ሰማንያዎቹ ትግሬዎች ቢሆኑ አይግረምህ፡፡‹ታዲያ ምን ይጠበስ?› አትበለኝ፡፡ ምንም አይጠበስም፤ እኛው እንደለመድነው በአጋዚም በለው በትርሃስና በሐጎስ እንጠበሳታለን፡፡
አደራ! ወያኔ ወይም ትግሬ ስል መልካሞቹን ሳይሆን በአሁኑ ሰዓት በወያኔ አመራር ሥር ተኮልኩለው ሲያበቁ የኢትዮጵያውያንን ደም እንደመዥገር የሚመጡትን፣ እንደአልቅትና ትኋን የሚመገምጉትን ብቻ ነው፡፡ እርግጥ ነው ትክክለኛ ኢትዮጵያዊ መንግሥት ኖሮን ችሎታንና ብቃትን መሠረት ባደረገ ሁኔታ በእኩል የዜግነት መብታቸው የሚቀጠሩ ትግሬዎችን ለመለየት ባለመቻሉ ሁሉም የትግሬ ሠራተኛ እንደወያኔ መቆጠሩ ጊዜው ያመጣብን ፈውስ የለሽ ደዌ ነውና ይህን እውነታ ለመገንዘብ ጊዜና ትግስት እስኪኖረን ድረስ ይቅርታ መጠየቅ የሚገባን ጥቂት ትግራውያን ዜጎች መኖራቸውን ላስታውስ እፈልጋለሁ፡፡ ‹ከኑግ ጋር የተገኘሽ መጭ(ሰሊጥ?) አብረሽ ተወቀጭ› እንዲሉ እነዚህ በችሎታና ብቃታቸው ሊያውም ከሌሎች ጋር ተወዳድረው (በሜሪታቸው) ቦታውን ሊያገኙ ይችሉ የነበሩ ትግሬዎች በትግሬነታቸው ብቻ ሲታሙ ሳይ በግሌ ይሰማኛል – የሚገኙበት ሥነ ልቦናዊ ምስቅልቅሎሽ ይገባኛል፤ ህመማቸው ህመሜ መሆኑን ሳልገልጽ አድበስብሼ ማለፍም አልፈልግም፡፡ ችግራቸውን ልንረዳላቸው ይገባል እንጂ እኚህን መሰል ወንድምና እህቶቻችንን ከደናቁርትና ከእጅ እስካፋቸው ብቻ ማሰብ ከሚችሉ አንበጣ ወያኔዎች ጋር አዳብለን በነገርም ይሁን በርግማን መጎሸም እንደማይገባን እንወቅ፡፡ ይህ ችግር ደግሞ መጥፎና ማንም በቀላሉ ሊረዳው የማይችል ስስ ነገር ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ከፍርደ ገምድልነት እንድንቆጠብ ማሳሰብ እፈልጋለሁ፡፡ የምናያቸው ብዙ መጥፎ ነገሮች ዕድገታቸውን ጠብቀው ያልፋሉ፤ እንኳን ይህ ዘመን የአህመድ ግራኝና የዮዲት ጉዲትምም የመንጌ ቀይ ሽብርም የዘመነ መሣፍንት ትርምስም … ሁሉም በሰዓቱ አልፏል፡፡ ይህም ያልፋል – ሰንኮፉ ወድቋል፡፡ የቀረው ካልቀረው በእጅጉ ያነሰ ነውና እንዲያው አጃኢብ ከማለትና ከጸሎት ጀምሮ የበኩላችንን ለማድረግ ከመትጋት በስተቀር በስተቀር ብዙም አይሰማን፡፡ ከሁሉም ከሁሉም ቂም በቀል የሚቋጥር ሰው በተመሳሳይ አረንቋ ለመዳከር ያለመ ነውና ከዚህ አዙሪት ባፋጣኝ እንውጣ፡፡ በነሱም አላማረ፡፡ ስቃያችን እንዳይረዝም ከብቀላና ከሸፍጥ ነጻ ሆነን ፈጣሪ ሀራ እንዲያወጣን ከልብ እንለምነው – ይቻለዋል፡፡ እየሆነ ያለውን የፈቀደው ሆን ብሎ እኛን ለመፈተን መሆኑን እንረዳ፡፡ አለበለዚያማ እነኚህ ጉዶች ይህን ሁሉ ሚሊዮን ሕዝብ እንደከብት ሊነዱት እንዴት ይቻላቸዋል? …
በተረፈ ግን ሀገራችሁ እንዲህ ሆናላችኋለች፡፡ አዲስ ነገር እየነገርኳችሁ እንዳልሆነ እኔም አውቃለሁ፡፡
የምነግራችሁ በጥቅስና በምንጭ የተዥጎረጎረ ጥናታዊ ዘገባ አይደለም፡፡ ነገር ግን ሆን ብዬና በሥራዬ አጋጣሚ በመዘዋወር ያገኘሁት መረጃ ነው፡፡ መረጃየ እጅግ አስደንጋጭ በመሆኑ በቀላሉ የሚያኮርፍ ትግሬ ይህን ትንግርተኛ ጉድ የያዘ መጣጥፍ ባያነብ ይሻለዋል፡፡ በኋላ እኔ ላይ የሚለጥፈውን ታርጋ በመፈለግ እንዳይንገላታ ቀድሞውን አያንብ ዌም ድረ ገጽም ከሆነ አይለጥፈው፡፡ እዚያው በጠቡሉ እኔም እዚችው በጠበሌ፡፡ ያልተበረዘ ያልተከለሰ እውነቱ ግን ይሄውና፡፡
መከላከያ ሚኒስቴር ሄድኩ፡፡ ከበር ጀምሬ ስታዘብ ከሞላ ጎደል ሁሉም ትግሬ ነው፡፡ ወደ ውስጥ ለመግባት ምክንያቴን ገልጬ ተረኛው ዘብ ለውስጠኛው ሰው የይለፍ ፈቃድ ሊጠይቅልኝ በስልክ ሲያናግር የተጠቀመው ቋንቋ ትግርኛ ነው – አውቃለሁ፡- ከተጓዳኝ ፍካሬያዊ መልእክቱ ባለፈ ይህ ክስተት በራሱ ክፋት የለውም – የራስን ቋንቋ መጠቀምም የሚበረታታ እንጂ የሚያስነቅፍ አይደለም – መቼና የት ለምን የሚሉትን ጥያቄዎች ማጤን ግን የብዙ ልጆች እናት የሆነችን አንዲት ‹ፌዴራላዊት› ሀገር በ‹እኩልነትና በፍትህ› የሚያስተዳድሩ ወገኖች ሊያስቡበት ይገባቸው የነበረ ጉዳይ መሆኑን ማስታወስ እወዳለሁ – በዚያ ላይ የሚታሙበትን ብዙ ነገር መገንዘብና ለተጨማሪ ሃሜት በር መክፈትም ተገቢ አይደለም ፡፡ ብቻ እኔም በትግርኛ አናግሬው – በዚያም ምክንያት በጣም ተደስቶ – ገባሁ፡፡ በአገዛዙ ውስጥ በወያኔነት የተገጠገጡ ትግሬዎች – አዝናለሁ ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል መልክ – የዋሆች ናቸው- በቋንቋ የሚያመልኩ፣ ለጎሣዊ አንድነት በቀላሉ የሚንበረከኩና ለወያኔያዊ ማንነት የሚሰግዱ ጅሎች ናቸው፡፡ ትግርኛ ጥርት አድርገህ ከተናገርክ ብዙ ሥራ ልትሠራ ትችላለህ – ከደረሱብህ ግን አንተን አለመሆን ነው(ትግርኛ በመናገሩ ምክንያት አምባሳደር ሊያደርጉት የመለመሉት ሰው ኋላ ላይ ትግሬ አለመሆኑን ሲያውቁ መሸወዳቸው ገባቸውና ሥልጠናውን ጨርሶ ሊመደብ ሲል እንዳባረሩት ቀደም ሲል ሰምቻለሁ – ከዓለም በዘረኝነታቸው የሚስተካከላቸው የነበረና የሚኖር አይመስለኝም – ከአፓርታይድም ይብሳሉ፡፡ በሀገር የጋራ ሀብት እንደልባቸው የሚፏልሉ የአሁን ጅሎች የነገ የታሪክ ዝቃጮች መሆናቸውን በድፍረት የምመሰክረው የነገ ዕጣ ፋንታቸውን ከወዲሁ ቁልጭ አድርጌ እያየሁ ለነሱና ለጠፋው ትውልዳቸው ከልቤ በማዘን ነው)፡፡ ምን አለፋህ – ወያኔዎች ቂሎች ናቸው – ብልጥነት ሲበዛ ሰውን የሚያጃጅል ይመስለኛል፡፡ ለዚህ ይመስለኛል ይሉኝታና ሀፍረት የሚባል ጨርሶውን የሌላቸው፡፡ እነዚህ ወያኔ ትግሬዎች 0.000…1 በመቶ ይሉኝታ የላቸውም፡፡ የጅልነታቸው መሠረትም ይሄው ‹ሰው ምን ይለኝ ይሆን? ታዛቢ ምን ይለኛል? › ማለት አለመቻላቸው ነው፡፡ ሀገሪቱን እኮ የአንድ ቤተሰብ ንብረት ያህል ነው የቆጠሯት! አይገርምም? ‹የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም›ና እንደልቤ መናገሬን ከጥፋት ላለመቁጠር ሞክር፡፡
[አማራ እንደወይራና ደሬ ፍልጥ ሥጋውና አጥንቱ ወያኔዎች በሚለኩሱትና በሚያስለኩሱት እሳት እየነደደ ሳለ በደስታ እየቦረቃችሁ ይህን እሳት የምትሞቁ ትግሬዎችም ሆናችሁ ሌሎች ዜጎች ወዮላችሁ! እሳት በባሕርይው ተዛማች ነው፡፡ በሰው ስቃይ የምትደሰት ሁላ ነገ ወር ተራህ ሲደርስ አንተም አይቀርልህም፡፡ ይህን ፍርድ ሰው አይደለም የሚጥልብህ፡፡ ተፈጥሮ ራሷ ናት – እግዚአብሔርም ልትል ትችላለህ፡፡ … አንድ ጉብታ ቦታ ላይ ቤቶች በእሳት መቀጣጠል ይጀምራሉ፡፡ ሰዎች በኅብረት ሆነው ውሃ ያለው በውሃ፣ ሌሎች በአፈርም በቅጠልም ያን እሳት ብዙ ውድመት ሳያስከትል ለማጥፋት ይሞክራሉ፡፡ ከጉብታው ወረድ ብሎ በሚገኝ ረግረጋማ ኩሬ ውስጥ ዕንቁራሪቶች አሉ፡፡ አንዲት ቀበጥና የሰው ችግር የማይገባት ኮረዳ ዕንቁራሪት የእሳቱ ነበልባልና ጪስ በሚሰጣት የደስታ ስሜት ተውጣ የእልልታ በሚመስል ዕንቁርቁርታ ጩኸቷን ታስነካው ያዘች፡፡ እናቷ ግን ‹ተይ ዕረፊ፤ አያድርስ ነው› ብላ ብትመክራትም ‹እንዴ እማዬ! እዚህ ውሃ ውስጥ ሆኜ ምን እሆን ብለሽ ነው› በማለት የደስታ ቡረቃዋን ትቀጥላለች፡፡ … መንደርተኛው ባለው ‹ሪሶርስ› እሳቱን ለማጥፋት ያደረገው ጥረትና ሙከራ ሁሉ አልሳካ ይለውና እንሥራ ያለው በእንሥራው ቅል ያለው በቅሉ ውሃ እየቀዳ ያን ጠንቀኛ እሳት ለማጥፋት ወደኩሬው ይወርዳል፡፡ ሁኔታው ያላማራት እናት ወደታች ወርዳ ትመሽጋለች፤ ልጅ በሰው ስቃይ እየተደሰተች በኩሬው የላይኛው ክፍል ቡረቃዋን ትቀጥላለች፡፡ እንደተባለው አያድርስ ነው ያኔ በአንዱ ቅል ውስጥ ትጠለፍና እሳት ማጥፊያ ሆና አርራ ትሞታለች፤ እናትም ብዙ አላዘነችም – ቀድማ አስጠንቅቃለችና፡፡ ሁልጊዜ ፋሲካ የለም ወንድሜ፡፡ ዘመነ መርዓ እንዳለ ሁሉ ዘመነ ፃማ ወብካይ እንዳለም ማወቅ ተገቢ ነው ያገሬ ልጅ፤ ሁልጊዜ ጅልነት ከጥቅሙ ጉዳጡ ያመዝናል እህቴ፡፡ ጥጋብንና ቂላቂልነትን ገታ አድርጎ ወደኅሊና መመለስ ለሟች ብቻ ሳይሆን ለገዳይም የሚተርፍ እርባና አለውና ጎበዝ ነቃ እንበል፡፡]
መከላከያ ሠራዊት የሀገር ሀብት ነው፡፡ አሁን ግን የወያኔ ትግሬዎች ብቻ ነው፡፡ ማንም ሌላ ኢትዮጵያዊ ‹የኔ መከላከያ ሠራዊት› ብሎ የሚቀበል አይመስለኝም – ፖሊሱንም፣ ቤተ መንግሥቱንም፣ ባንዲራውንም፣ ብሔራዊ መዝሙሩንም እንዲሁ ‹የኔ ነው› ብሎ የሚቀበል የለም፤ ባይገርማችሁ ኢትዮጵያንም የኔ ናት ብ የሚቀበላት እየጠፋ ነው፡፡ ‹እነሱው እንደፍጥርጥራቸው ያድርጓት› ብሎ አብዛኛው ሰው ትቷታል – መጥፎ የነገሮች ሂደታዊ ዕድገት! (ባንዲራ ሲሰቀልና ሲወርድ ሰዓቱ ካለመጠበቁም በላይ አክብሮ የሚቆምነና ሰላምታ የሚሰጥ ወታደር አላይም፤ ጎበዝ እንደሕዝብም እንደሀገርም አልሞትንም ብለን እንዳንወሽ!) በአመራር ሳይሆን በሌሎች ድጋፍ ሰጪ የሥራ ክፍሎች የሚገኙ ሌሎች ወገኖች እንዴት በመሰለ ፍርሀትና መሽቆጥቆጥ እንደሚኖሩ አትጠይቁኝ፡፡ በደርግና በአፄው ዘመነ መንግሥቶች ሥልጣን ላይ የነበሩ ትግሬዎች ወንበራቸው የፈቀደውን የሥራ ኃላፊነት ያለመሸማቀቅ ሲያከናውኑ የዛሬው የይስሙላ ኮሎኔል ተብዬ ‹አዛዥ› ከተላላኪ የትግሬ ወያኔ ፈቃድ ሳያገኝ አንዳችም ነገር አይሠራም፤ አስገራሚና ከአእምሮ የመቀበል አቅም በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ዘመን! ኧረ በኢትዮጵያ ጉድ ፈልቶላችኋል! የት ነበርክና ዛሬ እንዳዲስ እንዲህ ያንዘረዝርህ ያዘ እንዳትሉኝ ብቻ፡፡ አጠቃላይ ነገረ ሥራቸውና እያደር ጥሬነታቸው ደም ፍላቴን ቀስቅሶብኝ ነው አሁን በብዕር የማወጋችሁ፡፡
ሜክሲኮ ወደሚገኘው ፌዴራል ፖሊስ ሄድኩ፡፡ ዘብ አካባቢ ጥቂት ኢትግሬዎችን አየሁ፤ ወደውስጥም ገባሁ – ግን ያው እንደመከላከያው የተሞላው በአብዚ አብዚ ነው፡፡ በጥልቀት ለተመለከተው ወያኔ ትግሬዎች ያሳዝናሉ፡፡ ይህን ሁሉ ሀገራዊ ሥልጣን ለብቻቸው የያዙት እኮ ለኢትዮጵያ ዕድገትና ብልጽግና የሚጨነቅ ከሌላው ብሔር ሰው ስላልተገኘ ነው! ሸክማቸው ከበደ፤ አጋዥም አልፈለጉ፤ ብቻቸውን ይዳክራሉ፡፡ በየመሥሪያ ቤቱ ብቻቸውን ሲባዝኑ ስታዩዋቸው አንጀታችሁን ይበሏችኋል፡፡ እናግዛችሁ ብትሏቸው ‹በገዛ ሀገራችን አንተን ምን አገባህ?› ከሚል ይመስላል አይፈቅዱልህም፡፡ አንድ ጊዜ በአንድ መሥሪያ ቤት አንድ ባለዲግሪ ሰው አወዳድራችሁ ላኩልን የሚል ትዕዛዝ ይወርዳል፡፡ ትግሬው አለቃ ትግሬ ባለዲግሪ ቢያፈላልግ ያጣል፡፡ ነገሩን የሚያውቅ አማራ ባለዲግሪ ቢጠይቀው በለበጣ ስቆ ‹ያንተን ዲግሪ እንጨት ስበርበት፤ ውሃ ቅዳበት› በሚል ምፀታዊ የምልክት ቋንቋ ጥያቄውን ውድቅ እንዳደረገበትና ባለዲፕሎማ ትግሬ እንደላከ አጫውቶኛል – ልጆቼን ይንሳኝ የምነግራችሁ እውነቴን ነው፡፡ ቢሆንም ይህም ያልፋልና በግብዞች ተናድዳችሁ ግብዝ እንዳትሆኑ ተጠንቀቁ፡፡ ሆድ ብዙ ይችል የለም? ባይሆን በዚሁ ይብቃችሁ እንዲለንና እንዲምረን ጌታን መማፀን ነው፡፡ በመሠረቱ የመንግሥት ሥልጣንና ደመወዝ የሚቀኑበትና የሚጎመዡለት ሆኖ አይደለም፡፡ ሊስትሮ ሆኖ መኖር ይሻላል፡፡ የሚያናድደን ግን ካለችሎታቸውና ካለዕውቀታቸው ሱቅ ውስጥ እንደገባ ሕጻን በዐይነ ዐዋጅ ሁሉንም ነገር እየያዙ ሥራ ስለሚያበላሹ ነው፡፡ ከዚያ ውጪ በበኩሌ ሀገራዊ ሥራ እስከተቃና ድረስ፣ አስተዳደራዊ ግፍና በደል እስከተወገደ ድረስ እንኳንስ አንድ ብሔር አንድ ቤተሰብም ሀገሪቱን ቢገዛ ጉዳየ አይደለም፡፡የነዚህ ግን ለዬቅል ነው፡፡ ከዘበኝነት በቀጥታ ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ሲመደብ ብታይ፣ ከጽዳት በቀጥታ የመኪና አሽከርካሪ አሰልጣኝነት በአንዲት ቀላጤ ተመድቦ ብታይ ከመገረም ባለፈ የምትለው ነገር የለህም – ኢትዮጵያ የነሱ እንጂ የአንተ ሀገር አይደለችማ! ለካንስ ዜጎች በነቂስ ከሀገር ለመውጣት የሚጥሩት ለዚህ ኖሯል?
የመኮንኖች ማሰልጠኛ ኮሌጅ ሄድኩ፡፡ የግቢው ኦፊሴል ቋንቋ ከበር ጀምሮ ትግርኛ ነው፡፡ ቤተ መጻሕፍትም ግባ መስተንግዶም ግባ የትም ግባ የትም የምታገኘው ትግሬ ነው፡፡ አደራችሁን ጥሩዎች ትግሬዎች በጉዱ ካሣ ‹ዕብደትና ምቀኝነት› የተሞላበት ንግግር እንዳትከፉብኝ፤ የመንታ እናት ተንጋላ ታጠባ ዓይነት ሆነብኝ፡፡ ራሴው ፈርቼ ሰውን አደራ ማለት ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው እባካችሁን? ግን ለምን ፈራሁ? አሃ – በይሉኝታ ባህል ነዋ ያደግሁት፡፡ እነሱ ቢተውት እኔም ልተው?
ምግባረ ሠናይ ወደተባለው ሆስፒታልም አመራሁ፡፡ ከዘበኛ እስከ ላይኛው ሜዲካል ዳይሬክተር ትግሬ ነው – በነገራችን ላይ የአሁኑን አታስዋሹኝ ማን እንደሆነ አላውቅም – እኔ በሄድኩ ሰሞን ግን ሁሉም ትግሬዎች ነበሩ፡፡ በጣም አልፎ አልፎ ጽዳቶችና ዕቃ አቀባባዮች ከሌሎች ጎሣዎች አይቻለሁ – የሄድኩበት ጊዜ ራቅ ስለሚል ነው የአሁኑን አለማወቄን የተናዘዝኩት፤ ለነገሩ ገዢዎቻችን ይሉኝታቸውን ቀቅለው የበሉ ወይም ባወጣ የሸጡ በመሆናቸው ለውጥ ይኖራል ብዬ አልጠብቅም፡፡ ሰው በጊዜ ሂደት ይማራል እነሱ ግን እየባሰባቸው ነው የሚሄድ፤ ሰዎች አልመስልህ እያሉኝ ነው ወገኖቼ፡፡
እዚያው ሆስፒታል አካባቢ የሚገኘውን የመኮንኖች መኖሪያ ካምፕ ውጪ ሆኜ ወጪ ገቢውን ታዘብኩ፡፡ እንደወያኔ የምርጫ ውጤት 99.98 የሚሆነው ወጪ ገቢ ያው ትግሬ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በአንድ የወታደር ሚኒባስ ወይም የራሽያ ዋዝ ሊፍት አግኝተህ ብትሳፈር ከአሥሩ ወታደራዊ መኮንኖች የሌላ ጎሣ የምታገኘው – ለዚያውም ዕድለኛ ከሆንክ – አንድ ቢሆን ነው፤ አንድ ጊዜ ይህን ዕድል አግኝቼ ሾፌሩ ብቻ ኢትግሬ ሆኖ ታዝቤያለሁ፡፡ እኛ በትግርኛችን ወሬያችንን እስከጣራ ስናቀልጠው ሾፌሩ ከሃሳቡ ጋር ነበር የቤቱን ጣጣ ያወጣ ያወርድ የነበረው – ያልታደለ፡፡ ምን ቅብጥ አድርጎት አማራ ሆነ?
ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ሄድኩ – ይገርማችኋል አሁን አሁን እርሱ ሳይሻል አይቀርም፡፡ ብዙ ተቀጣሪ ኢትግሬዎች አየሁ፡፡ የኃላፊነት ቦታዎችን ግን አትጠይቁኝ፤ ግቢው የተጥለቀለቀው የሚመስላችሁ በ‹ጌትነታችን ይታወቅልን› ሥነ ልቦናዊ ደንባራ ስሜት እየተነዱ ጮክ ብለው በሚያወሩ ወያኔ ትግሬዎች ነው፡፡ ይሄ ‹ምቀኝነቴ› ዛሬ የት እንደሚያደርሰኝ አይቼው፡፡ በነገራችን ላይ ቦታው ለመንግሥት ሥልጣን አሰጋም አላሰጋም በተለይ የሚበላበትና የሚጠጣበት የሥልጣን ቦታ ላይ ወያኔ ትግሬ ይጠፋል ማለት ዘበት ነው – ዋና ቦታ ለይምሰል ኢትግሬ የያዘው ቢመስል ጉዳዩ ሌላ ነው፡፡ ሀገሪቱ በአንድ ብሔር ሥር በጥገትነት ስለተያዘች ትግሬ በሥልጣን የሌለበትን መሥሪያ ቤት ለማግኘት እንደዲዮጋን ጠራራ ፀሐይ ላይ ፋኖስ ጨምረህ ብትዞር አታገኝም – እንዴት ብሎ? ሀገርን የፊጥኝ አሥሮ የመምራት ታሪካዊ ኃላፊነት በትግሬዎች ጫንቃ ላይ ወድቆ ትግሬን ከማንኛውም የሥልጣን ቦታ ማጣት በፍጡም አይታሰብም፡፡ ማንንስ ያምናሉ? ማንንም! ‹ሌባ እናት ልጇን አታምንም› ይባላል፡፡
የዚህ ሁሉ ከንቱ ተግባራቸው መንስኤ ሌሎችን ያለማመን ችግር ነው፡፡ ማይም ወያኔ ትግሬ የቢሮ ኃላፊ ሆኖ ሲሾም የተማረ ኢትግሬ አስፋልት ለአስፋልት ጫማውን ሲጨረስ እሚውለው ሀገሩ የርሱም ስላልሆነች ሳይሆን ወያኔዎች ‹ጥቅማችንን ይጋራብናል፤ ንግሥናችን ይጨናገፍብናል› ብለው ስለሚያምኑ ማንንም ወደመንግሥት የኃላፊነት ቦታ ማስጠጋ ስለማይፈልጉ ነው፡፡ የቬንዞላው ኒኮላስ ማዱሮ ከአውቶቡስ ዘዋሪነት በቀጥታ ወደ ምክትል ፕሬዚደንትነትና ከዛም ሳይታሰብ ወደ ዋና ፕሬዚደንትነት የተሸጋገረው በችሎታው ሳይሆን በአምባገነኖች በጎ ፈቃድ መሆኑን ለሚገነዘብ ሰው የወያኔ ደናቁርት፣ ማይምና ነቀዝ ባለሥልጣናትን የሹመት ሂደት መረዳት አያቅተውም – ወዮ ለሀገራቱ ሕዝቦች፡፡ የመማር ያለመማር ጉዳይ አይደለም፤ በመታመንና ባለመታመን መሀል ያለው ክፍተት በታሳቢነት እንደተጠበቀ ሆኖ በበላዮች ለማመን የመፈለግና ያለመፈለግ ጉዳይ ነው ዋናው ወሳኝ ነገር፡፡ ለአፍሪካዊ የፖለቲካ ሥልጣን መማር እንዲያውም አስፈላጊ አይደለም፡፡ ከተማርክ ለምን ትላለህ፤ ካልተማርክ ግን ለምሳሌ ግደል ብትባል ስንት እንጂ ለምን ብለህ አትጠይቅም፡፡ ሆድ እንጂ ራስ እንዲኖርህ አይፈለግም፡፡ የዘር ራ እንጂ የዕውቀት ምጥቀት የትም አያደርስህም፤ ደምህ እንጂ ችሎታህ አያዋጣህም፤ አጭበርባሪነትና መስሎ አዳሪነት እንጂ ለኅሊናና ለሀገር ታማኝነት ዘብጥያ ሊያወርድህ ይችላል፡፡
[ኢትዮጵያ የጉድ ሀገር ናት፡፡ ሕገ መንግሥት ተብዬውን ጨምሮ እያንዳንዱ ሕግ ሁለት ‹ቨርዥን›/መልክ አለው፡፡ አንዱ የተጻፈውና ይበልጡን ለኢትግሬዎች የሚሠራው ነው፤ ሌላው ያልተጻፈውና ለወያኔ ትግሬዎች ብቻ የሚሠራው ነው፡፡ የሰማይና የምድር ያህል የሚራራቁ አንደኛው የእንጀራ ልጆችን የሚያሰቃይ ሌላኛው የአብራክ ልጆችን የሚያስተዳደር ሁለት መንግሥታት በአንድ መንግሥት ሥር ይሉሃል እንዲህ ነው፡፡ ትግሬም ሁን ትግሬም አትሁን ወያኔ ትግሬን በሕግ አስተዳድራለሁ ብለህ ከተነሣህ መዳረሻህ ቃሊቲ ነው – እነሱ ሕግና ሥርዓት ጠላታቸው ነው ወንድሜ፡፡ ዘብጥያ የምትወርድበት ሰበብም አሸባሪነት፣ ሙሰኝነት፣ ነፍጠኝነት… ብዙ የክስ ቻርጅ ሞልቶልሃል፡፡ በአንጻራዊ ሁኔታ ደህና ልትኖር የምትችለው ያገኘኸውን እንደከብት እያመነዠክህ እንደነሱው እንደከብቶቹ ለመኖር ከወሰንክ ነው፡፡ ያ ደግሞ ለብዙዎች ስለማይስማማ ብዙው ሕዝብ ከቀን ቀን ወደዕብድነት እየቀየረ ነው፡፡]
ወደ ጥቁር አንበሣ ሆስፒል ተጓዝኩ፤ እዚያ ይልቅ የተሻለ ነገር አየሁ፤ በግቢው በአማርኛ የሚነጋገሩ ሠራተኖችን ተመለከትኩ – ያኔም የኢትዮጵያዊነት ስሜቴ በውስጤ ሲያንሠራራ ተሰማኝ፡፡ ትግርኛችን ከሰማንያ በላይ ከሚገመቱ የኢትዮጵያ ቋንቋዎቻችን አንዱ እንጂ ሁሎችንም በጋራ ቋንቋነት ሊያግባባ የሚችልን የጋራ መግባቢያ በ‹ፌዴራል› ደረጃ እንዲተካ ሕገ መንግሥቱም አያዝምና በትምክህተኝነት የሚከሰኝ ሰው ቢኖር እኔ የለሁበትም – ራሱ ይኮነንበታል፡፡ በኃላፊነት ደረጃ አሁንም አትጠይቁኝ፡፡ ከትግሬ እጅ የሚወጣ የሀገሪቱ ሥልጣን የለም – የነብርን ጅራት አይዙም ፤ ከያዙም አይለቁም ወዳጄ፡፡ ከንቱነታቸው ግን አሁንምና መቼም ያሳዝናል፡፡ ልበ ውልቆች! ጥንጥዬ ይሉኝታ እንዴት አጡ? በየመንግሥት መሥሪያ ቤቱ ከሚተራመስ ከዚያ ሁሉ የወያኔ ትግሬ ሠራተኛ ውስጥ ‹ኧረ ጎበዝ ይሄ አካሄዳችን የኋላ ኋላ መዘዝ ያመጣብናል! ይሄ ጥጋባችን ወደርሀብ እንዳይነዳን ብዙ ሳይመሽ ቆም ብለን እናስብ!› ብሎ በዝግ ስብሰባቸው ላይ የሚያስታውስ አንድ ቆራጥ ወያኔ እንዴት ይጥፋ? እንዴት ነው ሁሉም እንደተራበ ጅብ የሚሰለቅጠውን እየሰለቀጠ፣ የሚግጠውን እየጋጠ ተያይዞ ለማለቅ የወሰነው? ምን ዓይነት አጥፍቶ የመጠፋት ቃል ኪዳን ነው? የሰውስ ይቅር የፈጣሪ ፍርድ እንዴት ተዘነጋ? ይህ ሁሉ ጉድ አልፎ አይቼው መቼስ!
ለናሙናነት እንዲሆኑኝ ወደጥቂት ወረዳዎችና ቀበሌዎች ሄድኩ፡፡ ድፍን ያልተማረ ትግሬና አጨብጫቤ ኢትግሬ በብቃት ሳይሆን በታማኝ አገልጋይነት ከሚሰገሰጉባቸው የመንግሥት ተቋማት መካከል እነዚህ ዋነኞቹ ናቸው፡፡ እንደጣሊያን ሶላቶ እዚህም እዚያም እንደልቡ ሲጮህና ሲያናፋ የምታዩት የወያኔ ትግሬው ባለሥልጣን ነው – ቀላልነታቸው ሲታይህ ውስጥህ በሰዎች ማንነትና ሰዎች ስንባል አንድ ያልተጠበቀ ነገር ስናገኝ ከሚታይብን ብርቅ ድንቃዊ ጠባይ አኳያ የማንነታችን ትርጓሜ ከእንደገና ይደነፈይ(to be redefined) ዘንድ ትመኛለህ፡፡ በነዚህ አካባቢዎች ጥቂት የማይባሉ ኢትግሬዎች ቢኖሩም በሥልጣናቸው የሚያደርጉት ነገር ከስንት አንድ ነው፤ ሁሉም ለትግሬዎች እጁን ሰጥቷል፡፡ የቀበሌ ምርጫ እንኳን ሲኖር ኢትግሬዎች ራሳቸው የሚጠቁሙት ታሪክ ‹ኢትዮጵያን አደራ› ያላቸውን የወያኔ ትግሬዎችን ነው – እነሱው እንዳቦኩት እነሱው ይጋግሩት› ለማለት ይመስላል፤ ሌላው በሀገሩ ውስጥ የሚኖር መስሎ ከሀገሩ ወጥቷል – ይህን ደግሞ ትግሬዎቹ አይረዱም ወይም መረዳት አይፈልጉም፤ የሌሎቸ ዜጎችን የ‹ሬዚግኔሽን› ወይም ‹ዊዝድራዋል› ስሜት ወያኔዎች የሚወስዱት እንደሽንፈትና እንደመንበርከክ እንደበጎ አጋጣሚም ነው፡፡ ብቻ የትም ቀበሌ ሂዱ ፈላጭ ቆራጩ ባብዛኛው ያው ታሪክ የፈረደበት ሀፍረተቢሱ ወያኔ ትግሬ ነው፡፡
ወደጦር ኃይሎች ሆስፒታል እንዲሄድ የምናብ ሳይሆን እውነተኛ ፈረሴን ኮለኮልኩ፡፡ ይዘገንናችኋል፡፡ ለነገሩ ከሀገሪቱ ስድስት በመቶ ከሚሆን ሕዝብ በብቃታቸውና በደም ጥራታቸው ተመርጠው የአንዲትን የ87 ሚሊዮን ሕዝብ ሀገር የጦር ኃይሎች ሆስፒታል ለብቻቸው ቢቆጣጠሩ እነሱን ካላደከማቸው ምን ችግር አለው? በዚህ ጉዞየ ለነሱ ተሳቀቅሁላቸው፤ ክፉኛ አፈርኩላቸው፡፡ በተወሰነ ዲግሪም ቢሆን በደሜ ውስጥ ያለችውን ትግሬነት አውጥተህ ጣላት የሚለኝ እርኩስ መንፈስ አንሾካሾከብኝ፡፡ ወንድሞቼ – ማርም ሲበዛ ይመራል፡፡ ሰው ባይቆጣ፣ ተቆጥቶም ባይናገር፣ ተናግሮም ባይደመጥ… ፈጣሪ ምን ይለኛል ተብሎ ሀፍረተቢስነትን በትንሽ ይሉኝታ ሸፈን ማድረግ ማንን ገደለ? በዚህ ሆስፒታል የትም ግባ የትም ካለትግሬ ሌላ የሆስፒታል ሠራተኛ ለማግኘት ያለህ የመቶኛ ስሌት ዕድል በዜሮና በአንድ መካከል ነው ቢባል ከእውነቱ አንጻር ሲታይ ግነቱ እጅግ ጥቂት ነው፡፡ በተለይ አንተ ጤናማ ትግሬ ሆነህ ወደዚያ ቦታ ለጉብኝትም ሆነ ለሥራ ወይም ለህክምና ጎራ ብትል በሀፍረት ተሸማቀህ የጎሣ አባሎቼ ናቸው በምትላቸው ሰዎች በሚሠራው ያልተገባ ሥራ በመናደድ ራስህን ልትሰቅል ትደርሳለህ፡፡ የነፍጠኛ ሥርዓት ናፋቂ እንዳትባልና መቀበሪያም እንዳታጣ በመሥጋት ግን ትተሃቸው ትወጣና ወደሚመስሉህ ወገኖችህ ትቀላቀላለህ፡፡ በዚህ ሆስፒታል በዝቅተኛ ሥራ ላይ የሚገኙ ጥቂት ኢትግሬዎችን አይቻለሁ፡፡ በተረፈ ንግግራቸው ብቻ ሳይሆን ሳቃቸው ሁሉ ትግርኛ የሆነ የ‹ፌዴራል ሪፈራል የመከላከያ› ሆስፒታል ነርሶችን፣ የጤና መኮንኖችንና የህክምና ዶክተሮችን ለማየት ወደዚህ ቦታ አምራ – የሆነ ቀጭን ሰበብ ፈልግና፡፡ ግን አትናደድ – ሁሉም ሊሆን የግድ ነውና በሞኝነታቸው ለነሱው ከማዘን በስተቀር ቂምና በቀልም አትያዝባቸው፡፡ አትፍረድባቸው – እየፈሩ ነው እንዲህ ያለ የነሱን ኅሊና ሳይቀር ሊረብሽ የሚገባው መጥፎ ሥራ ውስጥ (ወጥመድም ብለው እችላለሁ) የገቡት፡፡ እልሁንና ለሥልት የሚጠቀሙበትን የዘር ጥላቻ ለጊዜው ወደጎን ትተን ለመሆኑ አንድ ወያኔ ትግሬ ከኔ የበለጠ ሆድ አለው? ለዚህች ከአንድ እንጀራ ለማታልፍ ለቆታስ ይህን ያህል ርቀት ተጉዘው ለታሪክና ለሕዝብ ትዝብት መዳረግ ነበረባቸው? አልፎ አይተነው!
ቦሌ ካርጎ ማራገፊያም ሄድኩ፡፡ ያው ነው፡፡ ትግሬ ብቻ! ወይ ዕዳቸው፡፡ በየትም ሊገጥምህ የሚችል ነገር ደግሞ ላስታውስህ፡፡ በጦርነትም ይሁን በግል ጠብ፣ በጥይትም ሁን በጎራዴ እጁ የተቆረጠ ወይም ሌላ አካሉ የጎደለ የትግሬ ሠራተኛ በብዙ ቦታ ማግኘት የተለመደ ነው – አሃ! እሱ እኮ ‹የነሱው› ነው – ደሙን ለሕወሓት ያፈሰሰ ጅግና ተጋዳላይ፡፡ ይህ ዓይነቱ ዕድል ለኢትግሬ እንደሚሰጠውና እንደማይሰጠው ለማወቅ ‹ያደረግሁት ጥረት ለጊዜው አልተሳካም›፡፡ በዚህም ቦታ አዛዥ ናዛዡ ትግሬ ነው፡፡ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሂድ፣ ቤተ መንግሥት ግባ፣ ፓርላማ ሂድ፣ በማንኛወም የሚኒስቴርና የኮሚሽን መሥሪያ ቤቶች ግባ፣ ኢቲቪና ዋልታ ሂድ፣ ኢዜአም ሂድ፣ ጅምሩክ ሂድ፣ ባቡር ጣቢያ ግባ፣ አየር መንገድ ግባ፣ ሲቪል አቪየሽን ሂድ፣ ቴሌ ግባ፣ ኤልፓ ሂድ፣ ቤተ ክርስቲያን ግባ ፣ መስጊድ ሂድ፣ የትም ግባ አብዛኛውን የሀገሪቱን ሥልጣንና የጥቅም ቦታ የያዙት እነሰውና እነሱ ብቻ ናቸው፡፡ አዲ አበባ ላይ በንግዱም በፖለቲካውም ትግሬዎች ከመብዛታቸው የተነሣ መቀሌ ላይ እንዳለህ ቢሰማህ ወቅቱ የፈቀደው ፖለቲካዊ ፋሽን ውና ብዙ አትደነቅበት፡፡ መዝናኛማ በአብዛኛው የነሱ ርስተ ጉልት ነው፡፡ ሌላው ገንዘቡን ከየትአባቱ አምጥቶ ይዘባነናል? አይ ያለው ማማሩ! (የሌለው ደግሞ መደበሩ)፡፡ ወዩ አንቺን በጎጥና በሸጥ እየከፋፈለ በነገርና በቡጢ ሲያደባድብሽ፣ ለስደትና ለእንክርት ሲዳርግሽ፣ የጋራ ሀገርሽን ሲመዘምዝልሽ… እያንዳንድሽ በ‹ከነገሩ ጦም እደሩ› የማምለጫ መንገድ ራስሽን ለማዳን አላስካና ሶሎሞን ደሤቶች ድረስ እግር አውጪኝ ትያለሽ፡፡ እዚህ ያለው ደግሞ ሰማይ ምድሩ ተደፍቶበት እንደክርስቶስ ኤሎሄ ይላል፡፡ ምን ይበጃል? መጠበቅ ነው፡፡
አንድ ቀበሌ ለንግድ ከገነባቸው አሥራ ሦስት ክፍሎች ውስጥ ለላንቲካ አንዱ ብቻ ለኢትግሬ ሲከራይ አሥራ ሁለቱ ለትግሬ መከራየታቸውን የማረዳህ ይህ ሸፋፋ አካሄድ ነገ ሊያመጣ የሚችለውን ሀገራዊ ዳፋ በዓይነ ቁራኛ አጮልቄ እየተመለከትኩ በሚሰማኝ ከፍተኛ ሀዘን ተውጬ ነው – ያን ሰውዬ ከሠልፉ ለማስወጣትም ጥረት እየተደረገ እንደነበር ራሱ አጫውቶኛል፡፡ ወያኔ ትግሬ ሁሉ በጁ ሁሉ በደጁ ነው፤ ያልተሞዳሞደ ኢትግሬ ዜጋ ግን በግብር ቁልል፣ በኪራይ ቁልል፣ በ‹እንዳያማህ ጥራው፣ እንዳይበላ ግፋው› ዘዴ ከንብረትም ከሀብትም ከቤትም ከትዳርም እንዳይሆን እየተደረገ ሜዳ እንዲወድቅ ሁኔታዎች ሁሉ ይመቻቻሉ፡፡ አንድ ወያኔ ትግሬ ያለውን መብት አንድ መቶኛ ያህል እንኳን አንተ የለህም፡፡ ኢ. ቅጣው ሰባተኛ ዜጋ እንደሆንን የገለጸውን አሁን በሕይወት ኖሮ የመከለስ ዕድል ቢገጥመው ወደ ዐርባና ሃምሳ የዜግነት ደረጃ ያወርደው ነበር፡፡ እየተሠራ ያለው ግፍ ሰማይና ምድር አይችሉትም፡፡ ክፍያውን ግን ማን ሊችለው ይሆን?
አንድ ነገር ትዝ አለኝ፤ የዛሬ 23 ዓመታት ገደማ በፊት ከሬዲዮ የሰማሁት ነው፡፡ በዚያ የሬዲዮ መጣጥፍ ላይ የተገለጸው ትንቢታዊ ቃል አሁን ድረስ ከጆሮየ አልጠፋም፡፡ እንዲህ ነበር ሲባል የሰማሁት – እጠቅሳለሁ -‹ወያኔ የሚቃዥባትን የአራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ከተቆጣጠረ አማራን እንኳንስ ለኃላፊነት ቦታ ለዘበኝነትም አያበቃውም› የጥቅሱ መጨረሻ፡፡ ትንቢት ይቀድሞ ለነገር ይላሉ ካህናት፡፡ ትክክለኛ ግን መጥፎ ትንቢት፡፡
ለኢትግሬዎች ታዲያ ምን ቀራቸው ብሎ መጠየቅ ከብልህ አንባቢ ይጠበቃል፡፡ ለቀሪው ሕዝብ የተረፈው በስደት ዓለምን መዞርና ዕድል ካልቀናም በመንከራተት ሕይወትን በጨለማ አዘቅት ውስጥ ሆኖ መግፋት፤ በሀገር ውስጥ ለእሥርና እንግልት መዳረግ፤ በአማራነት ሰበብ ከምድረ ገጽ መጥፋት፣ ወያኔ ትግሬ በሀገርና ከሀገር ውጪ እየተንደላቀቀና እየተንፈላሰሰ ሲኖር በበይ ተመልካችነት መታዘብ፣ ከሲዖል ለመውጣት በሚደረግ ጥረት በየበረሃው የአውሬና የሰውነት ክፍልን በቁም እየበለቱ ለሚሸጡ ጨካኞች ሲሳይ ሆኖ መቅረት፣ (ፀረ-አማራ ፍሊት ከየት እንደሚገዙ አላውቅም ያን ወዳማራው ክልል በብዛት ሲልኩ ወደትግራይ ደግሞ ኢንኪውቤተር የሚልኩ ይመስለኛል – ሊያውም ማርገዝ፣ መውለድ፣ ማሳደግና ማስተማር ሳያስፈልግ ሰውን ያህል ፍጡር ትልቅ አድርጎ ለአቅመ አገዛዝ አድርሶ የሚፈለፍል ኢንኪውቤተር፤ አለበለዚያ ይህን ሁሉ የኢትዮጵያ የመንግሥት መሥሪያ ቤት የሚሞላ ትግሬ ወያኔ በነዚህ ጥቂት ዓመታት ውስጥ ከየት አፈለቁት ሊባል ነው? አማራን መፍጀት – በምትኩ ትግሬን ማብዛት! ትልቅ የሚሌኒየሙ የወያኔ ዕቅድ፡፡ ወዮ ለመጨረሻው የ‹ቂያማ ቀን›!)
ምን ቀረኝ? ሁሉንም ቢያወሩት ሆድ ባዶ ይቀራል፡፡ ስለዚህ ተመራርቀን እንለያይ፡፡ ወያኔዎች ሆይ መልካም የደስታና የሥልጣን ዘመን ይሁንላችሁ፡፡ ለሌላውም ልብ ይስጠው፡፡ ፈጣሪ ለሁሉም ጊዜና ዕድልን አመቻችቶ ይሰጣል፡፡ አንዱ ከአንዱ እየተማረ ይህችን አጭር ግን አሰልቺ የምድር ሕይወት ማጣፈጥ ሲቻል እያመረሩ መጓዝ ለምንም ለማንም አይጠቅምምና ሁላችንም እያሳለፍነው ካለነው የመከራና የስቃይ አዙሪት ተምረን መልካም ሰዎች እንድሆን ፈጣሪ ይርዳን፡፡
እግዚአብሄር ሆይ ና፤ የቅድስቲቱን ምድርም ባርክ፤ ሕዝብህንም ከብዔልዘቡሎች የእሳት ጅራፍ አድን፡፡ አሜን፡፡
(ሰበር ዜና፡- ይህን ወረቀት ጽፌ ከጨረስኩ በኋላ የሰማሁት ነገር ነው፡፡ የአንድ ኩንታል ጤፍ ዋጋ ነጩ ብር 2200 ሲገባ ጥቁሩ 2000ን ዘለቀ አሉኝ – ከገዛ ሰው ነው የሰማሁት፡፡ ወያኔ ዕድገታችንን ማለቴ ሞታችንን በየአቅጣጫው እያፋጠነልን ነው፡፡)