November 13, 2014
3 mins read

ቤተክርስቲያን እንዳይፈርስ የተቃወሙት ዜጎች ታፍሰው የት እንደደረሱ አልታወቀም; “ይህ ሁሉ የሆነው የእምነቱን ተከታዮች በመናቅ ነው”

(ነገረ ኢትዮጵያ) ትናንት ህዳር 3/2007 ዓ.ም ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ በቦሌ ክፍለ ከተማ የማሪያም ቤተ ክርስቲያን እንዳይፈርስ በመቃወማቸው የታፈኑት ዜጎች የት እንደደረሱ አልታወቀም ሲሉ በወቅቱ ጉዳዩን ሲከታተሉ የነበሩ የአካባቢው ነዋሪዎችና የእምነቱ ተከታዮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡

በወቅቱ 600 ያህል ዜጎች ተገኝተው ቤተ ክርስቲያኗ እንዳትፈርስ ሲቃወሙ እንደተመለከቱ የገለጹት የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች የቤተ ክርስቲያኗን መፍረስ የተቃወሙትን ጨምሮ ሌሎች በአካባቢው የተገኙ ዜጎችም በፖሊስ መታፈሳቸውን ገልጸዋል፡፡ ነዋሪዎቹ ‹‹ህዝቡ በሰንደቅ አላማ አምላክ አታፍርሱብን እያለ ቢለምንም እነሱ ግን ጥይት ወደላይ በመተኩስ ህዝቡን ከማሸበራቸውም በላይ ያገኙትን እየደበደቡ በ9 የድንጋይ መጫኛ መኪና አስገድደው በመጫን ወዳልታወቀ ቦታ ውስደዋቸዋል፡፡ አድማ በታኝ ፖሊስ ቄስ፣ አዛውንት፣ ህጻንና ሴት ሳይል ያገኘውም አፍሶ ወስዷል፡፡ የኮብል ስቶን ጠራቢዎች ሳይቀሩ በአካባቢው በመገኘታቸው ታፍሰው ታስረዋል፡፡ አሁን የት እንዳሉ አይታወቅም፡፡›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ቤተ ክርስቲያኗ ከተሰራች ከሁለት አመት በላይ እንደሆነ የገለጹት አንድ የአካባቢው ነዋሪ ‹‹ቤተ ክርስቲያኗ ከተሰራችበት ጊዜ ጀምሮ እንድትፈርስ ጥያቄ እንደቀረበ ተገልጾልን አያውውም፡፡ አሁን ነው ደርሰው ያፈረሱት፡፡ የቤተ ክርስቲያኗን አገልጋዮች ጨምሮ በጣም ብዙ ሰው በዱላ ተደብድቧል፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው የእምነቱን ተከታዮች በመናቅ ነው፡፡›› ሲሉ ቅሬታቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
የአካባቢው ነዋሪዎችና አማኞች ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ እስከ 9 ሰዓት ቤተ ክርስትያኗ እንዳትፈርስ እንደተቃወሙ፣ አድማ በታኝ ፖሊስ በአካባቢው ያገኘውን ሰው ካፈሰ በኋላ ቤተ ክርስቲያኗን በማፍረስ ቆርቆሮውን በመኪና ጭኖ እንደሄደ የአይን እማኞች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

5 Comments

  1. እናንት እነማናችሁ ህገ ወጥ ህንጻ የምትሰሩ እንደውም መንግስት ታግሱዋችዋል ሌላው ቤተ እምነት በብዙ መቶ ሺ እና በሚሊዮኖች እየከፈለ እናንተ ያለግብር በነዻ መሬት እየወረራችሁ ይዛችሁ ወንጀል ስትሰሩ ነበር ኢትጵያ እኮ ሁሉም ሃይማኖቶች እኩል የሚኖሩባት ሃገር ናት ይላል ህገመንግስቱ…….በተግባር ግን ፕሮቴስታንቱ,ሙስሊሙ,ጆቫው …….ወዘተ ህግ አክብሮ በውድ ዋጋ የቤተ እምነት መስሪያ መሬት ሲገዛ ዳሩ ግን ኦርቶዶክስ ግን በነጻ መሬት እየተሰጣት በዚህ ላይ ህገወጥ በመሆን መሬት ትወራለች ዘመኑ ተቀይሩዋል በድሮ በሬ ያረሰ የለም!!!!

  2. ደሞ ፖሊሰ በድንጋይ መደብደብ…….ህግ አስከባሪ ካልተከበረ ማን ሊከበር…..

  3. ክቡር ፓትሪያርክ ሆይ ለቤተ ክርስቲያን የቆመውን መሀበረ ቅዱሳን ይፍረስልኝ ከሚሉ ቤተክርስቲያንን ያህል ነገር ተጠሪ የሆኑለት በርኩስ መንፈስ የሚነዳው መንግስት ነኝ ባዩ የማፊያ ቡድን የተቀደሰችውን የ እግዚአብሄር ቤት ሲያፈርስና የ እምነቱ ተከታዮችን እንደ ከብት እየደበደበ ሲያስር ምነው አፍዎ ተያዘ:: እንዲህም አይነት አባት አይተንም አናውቅ የሚባለው እንደ እርስዎ አይነቱን ነው::
    ሌላው ቅዱስ ሲኖዶሱስ ለምን ድምጹን ሳያሰማ ቀረ? ምንኩስናችሁ ለመቼ ይሆን ተመንኩሶ ተፈርቶ አይሆንምና? አንዱን መምረጥ ግድ ይላችሃል :: የመጀመሪያው የክርስቶስ ሀዋረያ ነን የምትሉ ከሆነ ለስጋችሁ ሳይሆን ለነፍሳችሁ በማደር ስጋን ብቻ ሳይሆን ነብስንም በገህነብ ለቀጣ የሚችለውን ጌታችንን በመከተል የቤትህ ቅናት አቃጠልኝ እንዳለውና ለዋጭ ሸቃጮችን በጅራፍ ገርፎ እንዳባረረ ሁሉ እናንተም እንደ ክርስቶስ ጅራፍ ይዛችሁ ለማባረሩ ወኔውን ብታጡ እንካ ቤተክርስቲያን እንዳትፈርስ ማድረግ ትችሉ ነበር ም እመናን ታፍሰው ሲጋዙ ይፈቱ ብላችሁ ማስፈታት ትችሉ ነበር:: ሌላው ቢቀር ሲኖዶሱ ተቃውሞውን በጹሁፍ መግለጽ ሲጠበቅበት ይህንን ባለማድርጉ መንግስት ነገ ደግሞ ሌላ ቤተክርስቲያን ወደ ማፍረሱ እንደሚሄድ አትጠራጠሩ::
    ሌላው ወደረ በሚል ስም አስተያየት ሰጪ እርምጃውን ከወሰዱት አረመኔዎች በበለጠ ድንክ ሆንህ ታየህኝ :: አንተ በብላህበት የምትጮህ ፍጡር ነህ:: ከዚህ ቀደም የንበሩ ነገስታቶችን ታግሰዋል ብትል ማንም ሊቀበልህ ይችል ነበር:: ደርግና ወያኔ ግን በኦርቶዶክስ አፍቃሪነት አይታሙም:: የምናውቃቸው ሲቃወሙ እንጂ ሲደግፉ አይደለምና:: በተለይ ወያነ የሚባል አገር አጥፊ ቡድን ስልጣን ከያዘ ጀምሮ በጸረ ኦርቶዶክስነት እንጂ የሚታወቀው በአፍቃሪነት አይደለም:: ለነገሩ ወያኔና ፍቅር አይተዋወቁም :: ስለዚህ አንተ እንዳልከው ያንተ መንግስት ታጋሽ ሆኖ ሳይሆን መሬቱን ሊሸጠው ስልፈለገ ብቻ ነው ::እንደገናም አንተም እንደ መንግስት ወንጀል ስትስራ እንደንበረች እየነገርከን ነው:: ውሻ በበላበት ይጮሀል:: ስለዚህ አንተም ብትጮህ አያስደንቅም”” ጊዜው መቀየሩን እናውቃለን የትኛው የጸሎት ቤት ከዚህ እኩይ መንግስት ጋር እንደወገነ ጸሀይ የሞቀው የአደባባይ ምስጢር ስለሆነ እባክህን ያንተን የ እምነት ድርጅት ከሙስሊም እምነት ጋር አታያይዘው ለመሆኑ አርብ አርብ ሙስሊሞቹ ድምጻችን ይሰማ ብለው ሲጮሁ የነበሩት እንዳንተ የ እምነት ድርጅት መብታቸው ስለትከበረ ነውን ? የ እምነት ድርጅትህ ነው ከመንግስት ጋር በመወገን ውንጀል አየስራ ያለው::

  4. @weder zem beleh be keft afhn atawera…eng ethiopiawyn nen endat bewch lebirr belen haymanotachn yeshetn sewech aydelemn.

Comments are closed.

36151
Previous Story

ቃለ ምልልስ (ነቢዩ ሲራክ)

Next Story

አዲሱ የመኢአድ አመራር ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር የተጀመረው ግንኙነት እንደሚያስቀጥል አስታወቀ

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop