“ሻዕቢያ አባረረኝ፤ ኢህአዴግም እየበደለኝ ነው ሀገሬ የት ነው ብዬ እጠይቃለሁ?” – የወ/ሮ ሰምሀር ከበደ ብሶት ከአ.አ.

May 22, 2014

ወ/ሮ ሰምሀር ከበደ እባላለሁ፡፡ በአሁኑ ወቅት የምኖረው በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 6 የቤት ቁጥር 336/68 ውስጥ ነው፡፡ በ1970 ዓ.ም. በአስመራ ከተማ ተወልጄ ያደኩ ሲሆን ከኤርትራ ተፈናቅዬ በ1983 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ መጥቻለሁ፡፡ ሻዕቢያ አብርሮኝ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣሁ በኋላ ሌላ በደል ደረሰብኝ፡፡ እናቴ ወ/ሮ አልማዝ ገ/ሕይወት በ1987 ዓ.ም. ከኪራይ ቤቶች ህጋዊ ውል ተዋውላ ቀጠና 4 ወረዳ 2 የቤት ቁጥር 202/ሀ በሆነውን የንግድ ቤት እየሰራሁ እያለሁ በ1995 ዓ.ም ልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት የንግድ ቤቱን በተመለከተ የነበረውን ክርክር ለእናቴ የተወሰነላት ቢሆንም የወሰነውን ውሳኔ በመጣስ ቤታችንን እስከነ ንብረቱ ለሌላ ወገን አስተላልፎብናል፡፡ የፍ/ቤቱም ውሳኔ በእጄ ላይ ይገኛል፡፡ amharic.zehabesha.com

በ1989 ዓ.ም. የኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ ከወ/ሮ አልማዝ ገ/ሕይወት ጋር ህጋዊ ውል ተዋውሎ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 6 የቤት ቁጥር 336/68 የሆነውን 1 ክፍል ሳሎንና 1 ክፍል መኝታ ያለውን ኩሽና አጥር የሌለውን የመኖሪያ ቤት አከራይቷት እኔ ግቢውን ሊሾ በማድረግ 4 ክፍል መኝታ፣ ቤት ሻወር ኩሽና የግምብ አጥር በማጠር የብረት በር በማስገጠም 3 ትንንሽ ልጆቼን ይዤ ስንኖርበት ቆይቻለሁ፡፡ ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር በመረዳጃ እድርና በተለያየ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊ የሆንኩና በወረዳው በልማት ጉዳዮች ላይ ተሳትፎ ሳደርግ ቆይቻለሁ፡፡ ወላጅ እናቴ ወ/ሮ አልማዝ ገ/ሕይወት ሰኔ 24 ቀን 2005 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት በመለየቷ በፍ/ቤት ወራሽነቴን አረጋግጫለሁ፡፡ እኔም ነዋሪነቴ በቦሌ ክ/ከተማ ወረደ 6 የቤት ቁጥር 336/68 በሆነው የቤተሰብ ቅፅ ውስጥ ከነቤተሰቦቼ ተመዝግቤ የነዋሪነት መታወቂያ ያወጣሁና በየጊዜው እያደስኩ መኖሬ የሚታወቅ ሲሆን በስሜ በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 01 የቤት ቁጥር ‹አዲስ› በሆነው ባርና ሬስቶራንት ከፍቼ እየሰራሁ እገኛለሁ፡፡ ይህ ደግሞ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ አውጥቼ የምሰራበት ንግድ ቤቴ እንጂ የመኖሪያ ቤት እንዳልሆነ የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ አስተዳደር በደብዳቤ ገልጾ ለመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ልኮልኛል፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ይሄንን ትክክለኛ መረጃ ቀርቦለት እያለ ሚያዝያ 24 ቀን 2006 ዓ.ም. በተጻፈው ደብዳቤ ቤቱን በ30 ቀን ውስጥ እንድለቅ ባልለቅ ግን ‹‹ግንቦት 21 ቀን 2006 ዓ.ም. ባታስረክቢ በፖሊስ እቃሽን በመውሰድ ልጆችሽን በመወርወር እናስወጣሻለን›› በማለት ማስጠንቀቂያ ሰጥቶኛል፡፡ ሻዕቢያ በኃይል አብርሮኛል፡፡ አሁን ደግሞ አገሬ ነች ብየ ከመጣሁበት ኢትዮጵያም ከፍተኛ በደል እየደረሰብኝ ነው፡፡ እኔም ፍትህ ፍለጋ ወደ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመሄድ አቤቱታዬን ያቀረብኩ ሲሆን ፍ/ቤቱ አቤቱታዬን ውድቅ አድርጎብኛል፡፡ ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ልጆቼ ከእናቴ /ከአያታቸው/ ጋር በዚሁ ቤት ያደጉ መሆኑን የክትባት ወረቀት ማረጋገጫ ነው፡፡ ይህን መረጃ ተንተርሶ ወረዳ 6 ልጆቹ በዛ ቤት ቅፅ ውስጥ የተመዘገቡ እና ነዋሪ መሆናቸውን ገልፆ ለመንግስት ኤጀንሲ ቢፅፍም ‹‹ልጆቹን አናውቃቸውም!›› በማለት ሥነ-ምግባር በጎደለውና የህፃናት ልጆቼን የዜግነት መብታቸውን በመግፈፍ፣ እኔ እናታቸውን በመስደብ እና በማዋረድ በልዩ ጉዳይ አቶ ግርማይ ቅርንጫፍ 3 የሥራ ሂደት ኃላፊ እና ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኃ/ማርያም እቤቴ ድረስ በመምጣት በአያታቸው ሞት የተጎዱ ህፃናትን እናስወጣችኋለን በማት ኃላፊነታቸው የማይፈቅድላቸውን በደል ልጆቼ ላይ ፈጽ መዋል፡፡

ልጆቼን ለማስተማር የከፈልኩት 36000 (ሠላሳ ስድስት ሺህ ብር/ እና ልጆቼ ዓመት ሙሉ የለፉበትን ትምህርት ግንቦት 21 ቀን 2006 ዓ.ም. ከሚኖሩበት ቤት በፖሊስ በማስወጣት ትምህርታቸውን የሚያስተጓጉል መሆኑን በመናገር ልጆቹ ከፍተኛ የሆነ የስነ ልቦና ጫና የደረሰባቸው ሲሆን እድሜዋ 12 ዓመት የሆናት ማሪያማዊት ዜና ሥላሴ ከአያቷ ሞት በተጨማሪ የኤጀንሲው ሠራተኞች በተደጋጋሚ ‹‹ቤቱን ትለቃላችሁ›› እያሉ ስለሚያስፈራሩዋት በከባድ ፍርሃትና ጭንቀት የተነሳ ለአዕምሮ በሽታ ተጋልጣ በቦሌ ከፍተኛ የአእምሮ ክሊኒክ እየተረዳችና መድኃኒት እየወሰደች ትገኛለች፡፡ ይህንን ህክምና ማስረጃ ለኤጀንሲው ባቀርብም ወረቀቱን በመቅደድ ‹‹የትም አትደርሽም ስለ ልጆችሽ አያገባንም›› በማለት ሊያስተናግዱኝ ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ ሻዕቢያ ኢ-ሰብአዊ በመሆነ መንገድ አባርሮኛል፡፡ ወደ አገሬ ከተመለስኩ በኋላም ይህ በደል አልለቀቀኝም፡፡ እኔም ሆነ ልጆቼ እንደ ዜጋ
መብታችን የሚያከብርልን፣ የሚያዳምጠን አካል አላገኘንም፡፡ ይህ ሁሉ በደል ሲደርስብኝ ‹‹አገሬ ግን የት ነው?›› ብዬ እጠይቃለሁ፡፡

በእኔ ላይ ኤጀንሲው የኢትዮጵያ ዜግነትንና ሰብአዊ መብቴን የሚነካ ድርጊት እየተፈፀመብኝ ሲሆን ፍትህ አገኛለሁ ብዬ ለከፍተኛ ፍ/ቤት አቤቱታ ባቀርብም ፍ/ቤቱ ውድቅ ያደረገብኝ በመሆኑ በከፍተኛ ጭንቀት ላይ እገኛለሁ፡፡ በአካባቢዬ ያሉ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ባልደረቦች እና ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ
አባላት የሆኑ ቤት ቀጥለው የሰሩ ሲሆን የሰሩትም በብሎኬት ነው፡፡ እኔ ግን የሰራሁት በጭቃ ነው፡፡ እኔ የቤት ኪራይ የምከፍለው 560 ሲሆን እነሱ ግን የሚከፍት 70 ብር ብቻ ነው፡፡ ይህ ደግሞ እየተፈፀመ ያለው ሙስና ምን ያህል እንደሆነና በዜጎች መካከል ያለውን መድልኦና በደል የሚያሳይ ነው፡፡

አሁንም በመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ሠራተኛ ሆነው የራሳቸውን ደብቀው የሌላውን በመጠቆም እንዲለካና ኪራይ እንዲጨምር በማድረግ ላይ መሆናቸውን አስፈላጊም ከሆነ ስማቸውንና ያላቸውን የሥራ ኃላፊነት መናገር ይቻላል፡፡ በመጨረሻም የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ያለ አግባብ ግንቦት 21 ቀን 2006 ዓ.ም. በፖሊስ ከነልጆቼ ሊያስወጣኝ በዝግጅት ላይ ስላለ በዚያን ወቅት በእኔና በልጆቼ ላይ የሚደርሰውን በደልና ግፍ ሚዲያዎችና ሌሎች ለኢትዮጵያውያን መብት የሚቆሙ አካላት ሁሉ በቪዲዮ በመቅረፅ ለዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና ለህፃናት መብት እና ለኢትዮጵያ
ህዝብ እንዲያሳውቁልኝ እጠይቃለሁ፡፡

8 Comments

 1. ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ደጋግመሽ ኣንዳልሺው ኣኢትዮጵያውንት መብቴ ኣልትክበርም ነው
  ኣገርሽ የት ነው መልስ ያግኘ ይመስላል ሌላው ኣስተዳደሩ ክራይ ይክፍልሽው ፍርድበቱ ያገርሽ መንግስት ነው
  ሊላው ከ አርትራ ይወጣሽው ወይ ይካድሬ ኣለዝያም የ ደርግ ደህንነት ልጅ ነሽ ስል ኣናትሽ ትናግርሽ ኣንጂ ኣባትሽ
  በንብስ ይጠይቕ ይሆና ግን ነገሩን ልማሳጠር ወደ ኣግራቹ ትላካቹህ ወንጀላችህ ትልክቶ ብዛ ልክ ትጫኑ ነበር
  ሻብያ ኣባረርኝ ግልጽ የዚኣረ ስንት ኣመት የኣኢትዮጵያ ፍርድቤት ከ ኣኢርትራ ጋ ንክኪ ይልውም ምህረት ኣንድወንጀል ከትቆጠረ መንገዱን ጨርቅ

 2. It is sad sister there is nothing you can do, there must be a TIGRIAN who wants your land, Tigrians will do everything to displace Ethiopians live in Bole and Merkato and you can not do anything except this Aparthaid regime overthrown good luck on your struggles

 3. your case is very complicated you said you born in ASMARA and as the same time you claiming you are ETHIOPIAN since weyanes gave ERITRIA to shabia you are no more ETHIOPIAN unless we took at it in good faith.So your situation is not different from others that they displace them from their own farm land.being said that ETHIOPIA is not for ETHIOPIANS anymore so GOOD LUCK. at least you have business to survive with.

 4. DERBABAW or dedebu kk we can infer that she was expelled from ASMARA for being Ethiopian, thousands of Ethiopians who born in Asmara from Ethiopian families were victims of SHABIA displacement after their property was confiscated and this lady case could be the same with other thousands of Ethiopians who were displaced and died on the streets of Addis Abeba for being neglected by WOYANE

  since this lady is living in BOLE the reason she is loosing her land should be because ONE TIGRAY person wants her land, hundreds of Ethiopians are forced to give up their land and house for TIGRES in BOLE and MERKATO this is the reality MERKATO , God be with you Lady you are not alone thousands of Ethiopians were losing their land and businesses for TIGRIANS

 5. Self inflicted wound…..she should sue her family members: her father, mother, siblings,other blood relatives and may be herself……for supporting her own destruction….for supporting EPLF and TPLF…..Well, sister now you may understand what tribalism and clan based politics could cause….Good luck!

 6. ወይዘሮ ሰምሃር – አንቺ የምትነግሪን ግፍ ባንቺ ብቻ የደረሰ አይደለም። በሃገሪቱ ሁሉ ያለ የፍትህ እጦት ጥሪ እንጂ። በሻብያ መገፋትሽም ያለ ነው። ሻብያ እውር ድርጅት ነው። ደማችን ንጽህ ነው። እኛ ኤርትራዊያን ከሌላው ሃበሻ የጠራ ደም አለን በማለት የሚመጻደቅ ጠማማ ድርጅት ነው። በህዝባችን ላይ ሻብያ የሰራው ግፍ ይህ ነው ብሎ በአሃዝ ለማስቀመጥ ይከብዳል። እና ሻብያ ከኤርትራ ምድር ቢያስወጣሽ አስገራሚ አይደለም። አንቺን ከሌሎቹ የሚለይሽ በህይወት ተርፈሽ ሃገርሽ መግባትሽ ነው። ስንቶች በበረሃ ወድቀው ቀርተዋል። በወያኔ ግፈኛ ድርጅት ነው፡፡ ባንቺ ላይ የሚደርሰውም ግፍ ሆን ብሎ ሰውን ለማሰቃየት የሚደረግ በደል ነው። ፍትህ በምድሪቱ የለም። መታገስና ባለው መንገድ ሁሉ ችግርሽን ለመጋፈጥ መሞከር ነው። ሌላው የልጅሽ የአእምሮ መረበሽና መድሃኒት መውሰድ ነው። ከቻይና እና ከህንድ የሚገቡ የህክምና መድሃኒቶች መግደል እንጂ ማዳን አይችሉም። በሃገራችንም ታሞ ሆስፒታል ተረድቶ ድኖ የወጣ ጥቂት ነው። የሚሞተውና ሌላ በሽታ ይዞት ነው ከሆስፒታል የሚወጣው። ይቅርባት! ሌላ መንገድ ፈልጊ። ፈጣሪ ልብሽን ያሳርፈው!

 7. My deepest sympathy goes to you and your family. Until the veil curse is lifted from our nation, I am afraid your saga may continue. My question for you now is: what can we diaspora Ethiopians do to help you?

 8. እህቴ በጣም የዋህ ነሽ አሁን ኢትዮጵያን እየገዙ ያሉት እዛው ኤርትራ እያለሽ ያባረሩሽ ሻብያዎች ናቸው ከነዚህ ምንም አይነት ፍትህ አትጠብቂ ግዜ እስኪያልፍ ከነሱ ጋር በፍርድ ቤት መጋፈጡ ያለሽን ገንዘብ ከመጨረስ ውጭ ምንም የሚፈይድሽ ነገር የለም። በእርግጥ ቀማኛና ስራት አለበኞች የሻብያ ቡችሎችን ግን ለሚዲያ አጋልጫቸው።

Comments are closed.

sew le sew
Previous Story

ይድረስ ለ‹‹ሰው ለሰው ድራማ›› ደራስያንና ፕሮዲውሰሮች

Next Story

መድረክ የፊታችን ቅዳሜ በአ.አ በሚያደርገው ሰላማዊ ሰልፍ ሕዝቡ እንዲቀላቀለው ጥሪ አቀረበ

Latest from Blog

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ | ስለአማራ ክልል ከነዋሪዎች የተሰማው | አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል” | “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል”| “እጅ ከመስጠት ውጭ አማራጭ አይኖረንም” ፊ/ማ “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

ከውጭ በተላከ ገንዘብ ሀብት አፍርቶ የተላከበትን ደረሰኝ ያላቀረበ ንብረቱ እንዲወረስ የሚደነግግ አዋጅ ቀረበ

ዮሐንስ አንበርብር በጥፋተኝነት ላይ ያልተመሠረተ ንብረት የመውረስ ድንጋጌም በአዋጁ ተካቷል አዋጁ የሚፀድቅ ከሆነ 10 ዓመት ወደኃላ ተመልሶ ተፈጻሚ ይሆናል ከውጭ በተላከ ገንዘብ ሀብት አፍርቶ የተላከበትን ደረሰኝ ያላቀረበ ሰው ወይም ሊታወቅ ከሚችል ገቢው በላይ ሀብት አፍርቶ ምንጩ ሕጋዊ መሆኑን ማረጋገጥ ያልቻለ ሰው፣ ንብረት በመንግሥት እንዲወረስ የሚፈቅድ ድንጋጌ የያዘ
Go toTop