May 16, 2014
2 mins read

የአሶሳው ግድያ የታቀደ ስለመሆኑ ተረጋገጠ

አብርሃ ደስታ እንደዘገበው:- ባለፈው ሳምንት 9 የትግራይ ተወላጆች በቤኑሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ታርደው መገደላቸው ይታወሳል። አንድ ሌላ የታክሲ ሹፌርን በጥይት ተገድሏል (ከትግራይ)። በአንድ የዕጣን ድርጅት ይሰሩ የነበሩ ሦስት የአማራና ኦሮምያ ክልል ተወላጆችን ተገድለዋል። ትናንት ሐሙስ ግንቦት 7ም አንድ መኪና በታጣቂዎች ተይዞ በእሳት ጋይቷል። በተሳፋሪዎቹ የደረሰ ጉዳት በትክክል ባይታወቅም አንዲት ተሳፋሪ ግን ቆስላ ተገኝታለች።

በ9ኙ የትግራይ ተወላጆች ላይ የደረሰውን ግድያ ለማጣራት በመኮርኩት መሰረት ግድያው ሆን ተብሎ ታቅዶ የፈፀመ ስለ መሆኑ አረጋግጫለሁ። ሙሉ መረጃ ያላቸው አሶሳ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች እንዳረጋገጥሉኝ ከሆነ ዓማፂ ቡድኑ የትግራይ ሰዎችን አርዶ ለመግደል ማቀዱ ይታወቅ ነበር። የወረዳው አስተዳዳሪ ይህን መረጃ ከግድያው በፊት ደርሶታል። ባከባቢው የሚገኘው የመከላከልያ ሰራዊት አዛዥም ግድያ እንደሚፈፀም ተነግሮታል። ባጠቃላይ መንግስት ግድያው በተመለከተ ሙሉ ቅድመ መረጃ ነበረው። መንግስት መረጃ እያለው ግድያው መከላከል አለመቻሉ ኗሪዎችን አሳዝኗል። በአሶሳ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች መንግስት ተገቢውን ፀጥታ የማስከበር ተግባር አለመፈፀሙ አስገርሟቸዋል። መንግስት ለስልጣኑ እንጂ ለህዝብ ደህንነት እንደማይተጋም አስረግጠዋል። አሁንም አሶሳ አከባቢ የሚኖሩ የሌላ ክልል ተወላጆች ስጋት ዉስጥ ናቸው።

መንግስት በትግራይ ልጆች ላይ ግድያ እንደሚፈፀም እያወቀ ለምን መከላከል እንዳልቻለ ለህዝብ መግለፅ ይኖርበታል። የሰለማዊ ሰዎች ደህንነት መጠበቅ ባለመቻሉም ይቅርታ ይጠይቅ፣ ተገቢውም ካሳ ይክፈል።

11 Comments

  1. ይድረስ ለወንድም አብረሀ የምታቀርባቸውን ድፍረት የተሞላባቸውን እውነተኛ ዘገባህን ከሚከታተሉትና ከአክባሪዎችህ አንዱ ነኝ። በአሶሳ ስለተካሄደው ግድያ ላይ ግን ትንሽ ወረድክብኝ ። በአሶሳ ወስጥ የትግራይ በቻ ሳይሆን ሌሎችም ብሄረስቦች ይኖራሉ። አንተ ግን ያነጣጥርከው የትግራይ ተወላጆች ላይ ነው። ድምዳሜህ ላይም መንግስት በትግራይ ተወላጆች ላይ ግድያ እንደሚፈጸም እያወቀ ለምን መከላከል እንዳልቻለ ለህዝብ መግለጽ ይኖርበታል። ይቅርታም እንዲጠይቅና ተገቢውን ካሳ ይክፈል። በሚል ዝግብህዋል።አንት እራስህ ላነሳሃቸው ለሞቱት አማራና ኦሮሞችስ ምን መደረግ አለበት ትላለህ?።
    ይሄውልህ የጎሳ ፖለቲካው መጨረሻው እንዲህ ነው። ዬርስ በርስ እልቂት።ይሄንን ደግሞ ወያኔ ከፍጥረቱ ጀምሮ ሲመኘውና ሲጠብቀው የነበረ ጉዳይ ነው።ትላንት ከዚሁ ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አማራዎች ሲፈናቀሉ የጮሁት በጠም በጣም ጥቂቶች ነበሩ ሰሚ ግን አላገኙም።አሁን ደግሞ ግድያ ተጀመረ ።ቀደም ስልም አማራዎች በተለያየ ቦታ ተገለዋል ተርደዋል ዝም ተባለ ዛሬ ይሄው አድማሱ ሰፍቶ ያችን ሀገር እግዚአብሄር በኪነ ጥበቡ ካልጠበቃት በቀር የነ መለስ ስብሀት ምኞት ሊሰምር ነው።መለሥ ሞታል እነ ስብሀት. ስዩም. አባይ . እና ሌሎችንም የህ ወ ሀ ት አመራሮች እንካን ደስ ያላችሁ እንበላቸው ይሆን? ህሊና የሌላቸው ስዎች ያመጡት ጣጣ ተጀምራል። በህብረት ተነስተን ካልቆምን በቀር አንተም የዘርህን ሌላውም የዘሬ ያንዘርዝረኝ ካልን ዛሬ 9 ነው ነገ ደግሞ 90 ሲቀጥል ያስፈራል።
    ሌላው ወያኔን አሳምረህ ታውቀዋለህ ይቅርታም አይጠይቅም ካሳም አይከፍልም እንደገናም ድግሞ የህወሀት አባል እስካልሆንክ ድረስ ትግሬ በመሆንህ ብቻ ጥበቃ አያደርግልህም። የፖለቲካ ትርፍ ከገኘበት የራሱን አባል አርሱ ገሎ እነ እከሌ ገደሉት ብሎ የሚገድል ድርጅት ሆኖ እያለ ይህን አድርግ ብለን ወያኔ ኢህ አዴግን ባናስቸግረው መልካም ነው። ይልቅየስ ወያኔ ኢትዮፕያን ለማጥፋት እየፈጠነ እንዳለ ሁሉ እኛም እንድ ሆነን የጋራ ሀገራችንን ለማዳን ፈጥነን እንነሳ።
    እግዚአብሄር ኢትዮፕያን ይጠብቅልን፡ አሜን።

  2. Abraha, The EPRDF/TPLF has been playing on human life since its inception. It has a long trend of orchestrating mayhem for its illicit interest. I didn’t forget a story published on Tobia Metsehet in mid or late 80’s regarding to Hawzin mayhem written by Tsegaye G/Madhin Areya. Why didn’t the gov’t act according to the information it received has led me to the above conclusion-EPRDF/TPLF has been playing on human life.

  3. If the government knew about the murder, don’t you thing the murder was then actually planned and organised by the government itself. This is stating the obvious. is it not?

  4. It is all fabricated news by weyane.aberha desta we know that you are weyane.who speaks in the name opposition .how can you have all this freedom of writing on the cantry that even a family can not speak and play freely.is that because you are a …….. Every body know the answer.

  5. ወያኔ ጥርሱን ነቅሎ ያደገበት ሞያ ነው።ማስመሰል ማታለል ና ማጭበርበር ፥በቅርቡ በአምቦና በወለጋ ለሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ንጹሃን ዜጎችን የጸረ ሰላም ሃይሎች የፈጠሩት ነው በማለት የቆሙ መኪናዎችንና ህንጻዎችን በማቃጠል አይደል ሰላማዊ ዜጎችን የጨፈጨፈው ።ድሮስ ቢሆን በተለያዩ ሆቴሎች ፈንጂ እያጠመደ አሸባሪዎች ናቸው ይል የነበረው አሁንስ ምን ይገደዋል ሌሎች የመንግስት ተቃዋሚዎች ቢሆኑ እንኩዋን ሀገር ቤት ሌላም ሀገር እየሄደ እያፈነ እያመጣ ያስራል እዛውም ይገድላል።የአሁኑስ የተገደሉት የትግራይ ዜጎች ወገኖቻችን ቢሆኑም አሁንስ ራሱ ከግድያ ው በስተጀርባ የመጀመሪያ ተጠርጣሪ የማይሆነው ለምንድነው? አሁን ሙሉ ለሙሉ የካድሬውንና የትግራይ ህዝብን ድጋፍ ለማግኘት የተደረገ ዘግናኝ ግድያና አደገኛ ሴራ ነው፥የኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ የተቃዋሚ ድርጅቶችም በተለይ የትግራይ ህዝብ ይሄንን በስሜት ሳይሆን በጥንቃቄ መመልከት ይገባዋል።እድሜያቸው ያጠረ ወይም ያለቀ ስለሆነ የኢትዮጵያን ህዝብ ከማይወጣበት ገድል ውስጥ ከትተው ለመጥፋት የተዘጋጁ ስለሚመስለኝ ጥንቃቄ እናድርግ፣በተረፈ በኦሮሚያና በትግራይ ክልል የወያኔን እድሜ ለማራዘም ያለ አግባብ ህይወታቸውን ላጡ ጊዜና እግዚአብሄር ፍርዱን ይስጥን

  6. Here you go again Mr. Abrham Desta,

    From my personal principle point of view and from the aspect of humanity and democratic process of 21st century, I am personally against any form of killing and jailing of fellow person without due process. Not killing, but putting someone in jail for more than the legally limited 48 hours is an action done in contravention of due process of law and I am definitely against it.

    Before again challenge you as I did on your first posting, I want to make put my view forward about the acceptable and unacceptable scenario in this case of killing in Assossa.

    I have sympathy for family of those Tigrean who were killed in Assossa area, if the dead are innocent and laboring individuals like any other Ethiopians to win bread for their family. But as I once mentioned, if they were engaging themselves in dual activities and serving the TPLF as informants in the area, the action of the killers should not be a surprise for you or for any body. Those people who committed the killing are probably moving in the area to break the yoke of the TPLF/EPRDF power from the life of their generation and their children. I am sure you would have done the same against informants of the enemy of your livelihood.

    My challenge to you this time focuses on the last part of your essay.
    1. How did you get the information about the view of the Tigreans in Assossa on the government’s failure to protect the Tigreans at about 730 KM away from Addis/Finfinee when you were not even getting and mentioning the killings of the Oromo people just about 185 KM from Addis in the same direction? I am sure you immensely failed yourself and your preaching about yourself – Advocator of Democracy for all.

    2. You mentioned “መንግስት በትግራይ ልጆች ላይ ግድያ እንደሚፈፀም እያወቀ ለምን መከላከል እንዳልቻለ ለህዝብ መግለፅ ይኖርበታል። የሰለማዊ ሰዎች ደህንነት መጠበቅ ባለመቻሉም ይቅርታ ይጠይቅ፣ ተገቢውም ካሳ ይክፈል።” . This part of your writing naked you on a forum of democrats. Why do you expect the government which is officially killing very young university students who are asking legitimate questions and requests to address its failure to protect NINE Tigreans in Assossa? . Why didn’t you ask the same question the some people from Gare ethnic group who were armed by this the same government killed hundreds of Borena Oromo? When several hundreds, if not in thousands, of one group of people being killed by other ethnic group in the last 10 years? Is your question posed because of that the government on power is covertly an absolute power of Tigrai elites and the victim in this case are Tigreans? The absolute power Tigrean elite within this government is really not covert power. It is an open power of the Tigrans.

    I hope you either address your view about the mercilessly killing of five or more dozens of innocent Oromo students by the direct order of TPLF high officers just because of opposing a autocratically drafted and processed “master Plan “ of Addis without a thorough discussion with the affected Oromo people or you go down in the direction of TPLF dictators.

    Your stand or view on this piece of merciless killing of TPLF government is a test for you. Whether you are truly working hard in the last few years to contribute your part to bring a democratic system to all Ethiopians without any restriction or your discourse is an empty noise.

  7. >>”ሆን ተብሎ በፈረሰ ቤት ውስጥ ሆን ተብሎ ሰው ዘርማጥፋት(ግድያ) አይኖርም ተብሎ ለማሰብ እንዴት ፳፫ ዓመት አስፈለገ!? “በ፱ኙ የትግራይ ተወላጆች ላይ የደረሰውን ግድያ ለማጣራት በመኮርኩት ግድያው ሆን ተብሎ ታቅዶየተፈፀመ ስለመሆኑ አረጋግጫለሁ።” ተመስገን በአሶሳ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ተቆርቃሪና ለመኖርም ሙሉ መብትና ፍቃድ አላቸው። አሃ!

    *ዓማፂ ቡድኑ ትግራይ ሰዎችን አርዶ ለመግደልማቀዱ ይታወቅ ነበር።( በምላጭ ነው በሜንጫ!?) እንግዲህ ካሰበው- የፈፀመው፣ ከፈፀመውም -የተራዳው ፣የወንጀሉን ምንጭና ባለቤቱን(ዓማፂ ቡድኑን) አውቆ አደጋው ከመድረሱ በፊት አለመከላከሉና ከደረሰም በኋላ እጅ ከፍንጅ ይዞ ለሕግ ባለማቅረብ የዜግነት ግዴታውን ያልተወጣው የወረዳው አስተዳዳሪም ይሁን የአካባቢው መከላከያ ሠራዊት አዛዥ እንዲሁም የዚህ ዜና አቀባይ ከመንግስት ቀጥሎ ህግ ፊት መቅረብ አለበት።ግን መንግስት ማነው? who is in charge! እዚህ ጋ ያስፈልጋል።ህወአትሻቢያ ኢህአዴግ ገድሎ በማርዳት፣ ቀብሮ ንፍሮ ቀቅሎ፣ ድንኳን ጥሎ፣ አበባ ጎዝጉዞ፣በጥቁር መነፅር ተከልሎ፣ ባነር ወጥሮ በጥቁር ልብስ ተወጥሮ የዕርዳታ ንፍሮ አስጨፍሮ የሚያስነፋ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ የዓማፂ ቡድን አደለምን? በለው!

    “በጣም እናዝናለን ሲሞት ለፍቶ ጥሮ አዳሪ
    ገበሬ ሲፈናቀል ጋዜጠኛ ሲታሰር ሁሉሲሆን ፈርቶ አዳሪ
    ሕግ እንዳለ ይከበር ስትሉ!ጥቅማጥቅመኛ ሆኖ ገዳይ አጫፋሪ
    እንደከብት ተከልሎ እንዳይናገር ተከልክሎ የዘመነኞች አኗኗሪ
    መንቀሳቀስ መዘዋወር ንብረት ማፍራት ተከበረ በወሬ ነጋሪ
    ሰው በቋንቋ በዘር በባሕሉ በመታወቂያው ተለይቶ እየተባለ አሸባሪ
    ፌደራሊዝሙ ብሔር ብሔረሰብና ሕዝቦች ተከበረ ወይስ ሆነ ቀባሪ?
    ግና አንተ አልነበርክም ወይ የሜንጫ አብዮተኛ ቀደሞ ተቆርቋሪ?
    *****በ***********ለ********ው!

  8. R.I.P for those who lost their life ,but what i surprised me is: other Ethiopians are lived more than 20 years in such condition; but now it becomes a big deal cause they are……..it does not make sense. now It is their turn… test it how much it is sour

  9. R.I.P for those who lost their life ,but what i surprised me is: other Ethiopians are lived more than 20 years in such condition; but now it becomes a big deal cause they are……..it does not make sense. now It is their turn… test it how much it is sour.

  10. Sooooooooooo, you guys are crying just because they are Tigrayans? Are you serious? What about hundreds of Amharas killed on the day light by Woyane and Oromos, even, this month? I don’t really understand why the respected zehabasha website even post such kind of silly news stories from silly self named political analysit like Abreha? In the first place, where does he get the info? How he got it? This guy is not a journalist, or close to any political circle of the other regions as long as he told as that he is opposition, how on earth he is getting this info? Believe me this guy is Woyane, trying to convice Ethiopians that these Tigrayans were killed in retaliation for Amhara, Oromo or Gambella etc massacre.

  11. አይ ወንድሜ አብርሃ – ወያኔ የተካነው ሰውን በሰው ማጠላለፍ ነው። የበረሃ ታሪካቸው የሚያመላክተውም ይህኑ ነው። ማን ነው ዶ/ር ቀጸላን የገደለው? ወያኔ አይደለምን? ስንት የትግራይ ሴት ልጆችና ወንድ ልጆች ነው በትግራይ፤በጎንደር፤በሱዳን፤በኤርትራ በረሃ በራሳቸው ድርጅት የተገደሉት። ወያኔ ህዝባችንን መግባቢያ ቋንቋ ያሳጣ፤ በዘር በጎሳ ከፋፍሎ የሚገዛ፤ ሃገር ድንበርን የሚሽጥ መሰሪ ድርጅት ነው። አሁን በአሶሳ ተገደሉ የምትለንን የትግራይ ተወላጆች ወያኔ አደጋ እንደሚደርስባቸው እያወቀ ለምን ዝም አለ ስለምትለው ጉዳይ – ራሱ ወያኔ ሊሆን ይችላል የገደላቸው። ለምን ብትል። ህዝብን ከህዝብ ጋር ማፋጀት ሥራው ነውና! ወያኔ ለትግራይ ህዝብ አይገደወም። ለራሱ ሆድ እንጂ! መለስ ብለህ በበረሃ በትግራይ ህዝብ ስም የተፈጸመውን ግፍ መርምር። መራራ ነው።
    ወያኔ አረመኔ ድርጅት ነው – ከደርግ የከፋ! እስቲ ካፒቴን ተንኮሉ “ሞቶ መነሳት” በሚል የጻፈውን ፈልገህ አንብብ። የወያኔ የስለላ መረብ ሃላፊ የነበረውን ክንፈ ገ/መድህንን ማን እንደገደለው ታውቃለህ? ማን ነው ጄኔራል ሃያሎምን የገደለው? ለምንስ ተገደለ? የትግራይ ተወላጆች በአ.አበባ በቤታቸው ታንቀው ተገኙ እየተባለ መርዶ የሚነገረን የወያኔን ሴራ ስላጋለጡ ነው። አንድ ነገር ላጫውትህና ነገሬን ልዝጋ። አንድ የወያኔ አመራር ውስጥ የነበረ ሰው በድርጅቱ አሰራር ይናደድ እና ወያኔ ተነጥሎ ሌላ ሃገር ይኮበልላ። ይህ የሆነው በርሃ እያሉ ነው። እሱ በሜዳ እያለ ፍቅረኛ (ተጋዳሊት) ነበረቸው። ተፈቅዶሎት ያገባት። እሱን ለመበቀል መርዝ አብልተው ገደሎአት። ነፍሰ ጡር ነበረች። ይህ ድርጅት ነው ሃገር የሚመራው። እና አንተ በወገኖቻችን ላይ ጥቃት እንደሚደርሰ እያወቀ ወያኔ ለምን ዝም አለ ስለምትለው ጉዳይ ራሱ ያመቻቸው የግድያ ወጥመድ ሊሆን ይችላል። በርግጥ ተቃዋሚ ድርጅት በትግራይ ተወላጅነታቸው ብቻ ጥቃት አድርሶባቸው ከሆነ አህያውን ፈርተው መደላድሉን እንዲሉ ነው። ድሃውና ሰርቶ አደሩ የትግራይ ህዝብ እንደሌላው ወገን የወያኔ የመከራ ዶፍ የሚወርድበት ነው። አይገባም። ድንቁርና ነው። ይልቅስ ህዝባችንን የሚያምሱትን አስፈራሩልን። ደሃ ሰው አትግደሉ!!

Comments are closed.

Previous Story

“ተንበርካኪ የኦህዴድ አመራሮች” የሚለው የትግል ስልት አደገኝነት እንዴት ይታያል?

Next Story

(በስደት ያለው ሲኖዶስ ጉባዔ የመጀመሪያ ቀን ውሎ) የቀረበው አንድ ወጥ የሆነ ቃለአዋዲ ጸደቀ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop