የከተማውም የጫካውም የአብይ አህመድ ገዳይ ቡድን አቅሙ ሩጠው ማምለጥ፣ታግለው መጣል የማይችሉ አዛውንቶች ላይ ነው።
ነፍስ ይማር አባታችን!
ቦታው በርካታ ጸበልተኛ የሚገኝበት ነው። በቤተ ክርስቲያንና አገልጋዮች ላይ ያነጣጠረው ጥቃት ፤ በታላቋ የጸበል ቦታ በመካነ ቅዱሳን አርቱ ቅድስት አርሴማ የተፈጸመው ይኼ አሰቃቂ ድርጊት አስመልክቶ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ፣ የሰማዕታቱ ጸሎተ ፍትሐት እና ስርዓተ ቀብራቸው እየተካሄደ ፤ የቅዱስ ሲኖዶስ ዝምታ ለምን ይሆን ?!
ይድነቃቸው ከበደ
“ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቅ ደም ሁሉ ይደርስባችሁ ዘንድ።
እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ሁሉ በዚህ ትውልድ ላይ ይደርሳል።” ማቴ ፳፫: ፴፭ – ፴፮።
ካህኔን ከመቅደሱ ገድለውብኝ እንዴት ዕረፍት ይሰማኛል? እንዴት ዕረፍት ተሰማን?
ከገዳዮቹ ይልቅ የእኛ ነገር አሳሰበኝ።