ከአንድሺህ በላይ የብልጽግና ካድሬ ሰልጣኞች «ምርቃት» ላይ ተላልፎ ያፈተለከ ምስጢራዊ ንግግር – ወንድወሰን ተክሉ

ፋሺስታዊው የኦሮሙማው ቁንጮ አቢይ አህመድ ውስጥ ለውስጥ ሲያሽከረክር የቆየውን ጸረ ኤርትራ መንግስትና ጸረ የኤርትራ ሕዝብ ድብቅ ፖሊሲውን ሰሞኑን እያሰለጠናቸው ባሉት ካብኔት ምኒስትሮችና ከፍተኛ የብልጽግና አመራር ካድሬዎች ስልጠና ምርቃት ላይ በይፋ አውጥቶ አፈንድቶታል።

« የኤርትራን መንግስት እንደመሥሳለን። የኤርትራንም ሀገር አፍርሼ እቀላቅላታለሁ» በማለት አቢይ ድንግጥ ፍዝዝ ቅዝዝ ብለው ለሚያደምጡት ድንጉጥ ካድሬዎቹ በይፋ በመናገር በኤርትራ ላይ ያለውን ድብቅ ውስጣዊ ፖሊስን ይፋ ያደረገው እንዲህ በማለት ነው፦

«…. ኤርትራን ፣ ቀኑ መቼ እንደሆነ አልነግራችሁም እንጂ አፈራርሼ አምጥቼ እቀላቅላታለሁ።ኤርትራ የምትባል ሀገር እንዳትኖር አደርጋታለሁ።አፍርሼ እቀላቅላታለሁ።» በማለት ከተናገረ በኋላ ለጥቆም

« ያኔ አሰብን ብቻ ሳይሆን የመላው ቀይ ባሕር ባለቤትም የምንሆን ስለሆነ ኤርትራ እምትባል ሀገር አትኖርም። እንድትኖርም አናደርግም» በማለት እንዴትና ለምን አንዱት ሉዓላዊ የሆነችን ጥሩ ወዳጅ ጎረቤት ሀገር ለማፍረስ እንደፈለገ ለሰበሰባቸው ምኒስትሮችና ታላላቅ የብልጽግና ካድሬዎች ተናግራል። ግን አንድም ትንፍሽ ብሎ ለምን እና እንዴት ብሎ የጠየቀው የለም። ድንፋታውን ግን በጭብጨባ አጅበውለታል።

የፋሺስታዊው ኦሮሙማው ቁንጮ አቢይ አህመድ በዚህ ብቻ አላበቃም። ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ ሲል ተናግራል።

« ለቀይ ባሕርና ለአሰብ ትልቅ እንቅፋት የሆነብን የኤርትራ ሕዝብ ሳይሆን ሕዝቡን ቀጥቅጦና አንበርክኮ እየገዛ ያለው መንግስት ነው» በማለት የአሰብን ወደብና ብሎም አጠቃላዩን የቀይ ባሕር ቀጠናን ብንወስድ የኤርትራ ሕዝብ ፍቃደኛና ደስተኛ ሆኖ ቄጤማ ጎዝጉዞ ፈንዲሻ እየበተና እልልልል እያለ እንደሚሰጠን አድርጎ በመግለጽ ሻእቢያ የሚባለው መንግስት ግን እንቢ አልሰጥም በማለት እንቅፋት ስለሆነብን ነው ስርዓቱን ደምሥሰን ኤርትራን ወደ ኢትዮጲያ የምንቀላቅለው ሲል የተደመጠው።

እንደ አቢይ አባባል ለአሰብ ወደብና ለቀይ ባሕር ብዬ ነው የኤርትራን መንግስት የማፈርሰውና ሉዓላዊ ሀገርነታን እንዲያከትም የማደርገው እያለ ሲለፋደድ ነው የተሰማው።

ንግግሩን ሲደመድምም «… ስራ እየሰራን ነው።እዚያ ያለውን አገዛዝ (አስመራ ያለውን ማለቱ ነው) ለማስወገድ የሚያስችለንን ስራ እየሰራን ነው። እዚያ ያለውን አገዛዝ እናስወግደዋለን » በማለት ከፊት ለፊቱ ለተኮለኮሉት ደናቁርት ድንዙዝና ሆዳም ካድሬዎች ምኒስትሮችና ዶክተርና ፕሮፌሰር ነን ተብዬዎች የቁም ምውታን ተናግራል።

የፋሺስታዊው ኦሮሙማ ስርዓት ቁንጮ ነኝ የሚለው አቢይ በኤርትራ ብቻ ሳያበቃ በደቡብ ከምትጎራበተን እጅግ የኢትዮጲያ ወዳጅ በሆነቺው ኬኒያ ላይም ፊቱን በማዞር «…የኬኒያን መንግስት በቀላሉ ለመደምሰስ የሚያስችል ዝግጅት ሙሉ በሙሉ አዘጋጅተን አጠናቀናል» በማለት የብራ መብረቅ የሆነ ዛቻን ተናግራል።

የኬኒያን መንግስት ለመደምሰስ የሚያስችል ዝግጅት አካሂደን አጠናቀናል

« ኬኒያ .., የረባ የመቶ ዓመት ታሪክ የሌላት የበሬ ግንባር የምታክል ሀገር ስንዴና በቆሎ ስንልክላት ቆይተን የቀጠናው መሪ እኔ ነኝ ብላ እየተንጠራራች ነው። እኛ በላክንላት ችግኝ ተጠቅማ በአረንጋዴ ልማት የቀጠናው መሪ ነኝ ብላ የዓለም መሰብሰቢያ ለመሆን እየተንጠራራች ነው» በማለት በ2005 በአረንጋዴ ምርት በተለይም ከሰላሳ ሚሊዮን በላይ የጸደቁ ዛፎችን በመትከል የዓለም ኖቤል ሽልማት አሸናፊ የሆነቺውን ፕ/ር ዋንጋሪ ማታሂን ባፈራች ሀገር ላይ ችግኝ ልኬላት ሲል የተናገረው። ፋሺስቱ ስንዴና ባቄል ስንልክላት ቆይተን ብሎ ሲል በታሪኴ አንድም ግዜ ተርባ ስንዴን በእርዳታም ይሁን በግዢ ገዝታ ስለማታውቀው ኬኒያ ሳይሆን ስለማእከላዊ መንግስት የለሿ ሱማሊያ የሚናገር ነበር የሚመስለው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ትንሽ ስለ ተስፋዬ ገብረአብ - አብርሃ ደስታ ከመቀሌ

በዚህም ሳያበቃ የዛቻ ንግግሩን በመቀጠል «… ኬኒያን እየመራ ያለው መንግስት በቀጠናው ከእኔ በላይ የለም ብሎ እየተንጠራራ ስለሆነ እሱን በቀላሉ ለመደምሰስ የሚያስችል ዝግጅት እጠናቀን ጨርሰናል። የኬኒያን መንግስት በቀላሉ እንደመሥሰዋለን» በማለት ከኢትዮጲያ ጋር አንድም የድንበር ወግብ ከሌለባትና ከንጉሳዊው የዘውድ ስርዓት እስከ ዘመነ ኢሕአዴግ ባሉት ሶስት ተከታታይ መንግስታት የኢትዮጲያ ወዳጅ ኢትዮጲያን አክባሪና አፍቃሪ የሆነቺውን ጥሩ ወዳጅ ጎረቤታችንን ኬኒያን እንደመሥሳለን ብሎ ፊትለፊቱ ለተኮለኮሉት ከሺህ በላይ ታላላቅ የብልጽግና ካድሬዎች የለፈለፈው።

የፋሺስታዊው ኦሮሙማ ስርዓት የክህደት ሰንሰለት ከሀገር ውስጥ አልፎ ድንበር ተሻግሮ በወዳጅ ጎረቤት ሀገራት ላይ መድረስ – የሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል የሆነበት ሁኔታ፦

የኢትዮጱያን ውስጣዊ ፖለቲካና ኢኮኖሚን ሁኔታ በቅርበት ለሚያውቅ – በተለይም መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ኋይል ባለቀበት የሰሜን ጦርነት ማግስት በአማራ ሕዝብ ላይ በተከፈተ ጦርነት በብርሃኑ ጁላ ወደ አማራ ክልል ከተላከው 100ሺህ በላይ ሰራዊት ውስጥ ከ80ሺህ በላይ ሙትና ቁስለኛ ሆኖ በተደመሰሰበትና ፋሺስቱ ጦርነቱን በኦሮሚያ ክልል ልዩ ኋይል ተክቶ እየተዋጋ ያለበትን ቅርቃራ ሁኔታን የሚያውቅ ሰው ጭንቀት የወለደው የእብደት ንግግር ብሎ በማቃለል ሊያልፈው ይችላል። እንደዚህ ጸሓፊ እምነት ግን ይህ ጭንቀት የወለደው የእብደት ንግግር ሳይሆን ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል እንደሚባለው ጭንቀት በወለደው እብደቱ ውስጥ «እኔ እኮ አይደለም የአማራን ፋኖ ይቅርና ገና የኤርትራን እና የኬኒያን መንግስታቶችን ደምሥሼ አዲስ ግዛት የምመሰርት ፈርጣማ ገዢ ነኝ » ብሎ መናገሩን ነው የምረዳው።

የፋሺስቱ ድንፋታ ተራ ጭንቀት የወለደው የእብዳት ዛቻ ሳይሆን ተጨባጭ አመክኒዮ ያለው መሆኑን ለማየት የጠቀሳቸውን ምክንያቶች ማየት ይበቃል። በኤርትራ በኩል የጠቀሰው ምክንያት የአሰብና የቀይ ባሕር ጉዳይ ሲሆን ይህንን በተመለከተ በአማራ ላይ ጦርነት ከማወጁ መጋቢት ወር በፊት በየካቲት ላይ በፕሬዚዳንታ ሳህለወርቅ ዘውዴ በይፋ የተጀመረ የቀይ ባሕር ፖለቲካ የሚል ፕሮጄክት በይፋ መጀመሩን ለማስታወስ እወዳለሁ። ይህ የቀይ ባሕር መንግስታዊ ፕሮጄክት ይፋ ከመደረጉ በፊት ቢያንስ ከዓመት ከስድስት ወር በላይ ጥናት መንግስት ጥናት አድርጎበት ኢትዮጲያን የባሕር በር ባለቤት ለማድረግ አልሞ መነሳቱ የተገለጸ ሲሆን ይህንንም ዓላማውን ለማሳካት ከኤርትራ መንግስት ጋር በድርድር አሊያም በኋይል ተጠቅሞ እንደሚያሳካ በይፋ መግለጹና እንዲያውም የኢትዮጲያን አየር መንገድ ባለቤትነት ድርሻ (ሼር አክሲዮን ባለቤት ) ለኤርትራ መንግስት እንደቀረበለት በመረዳት የዛሬው ድንፋታ ጭንቀት የወለደው የእብደት ንግግር ብቻ ሳይሆን አቅም ቢኖረው ሊፈጽመው ያቀደው ውጥኖቹ መሆናቸውን ነው መረዳት የሚቻለው።

በኬኒያ ጉዳይ ላይ ያነሳውንም አመክኒዮን ስንመለከት እውነትነት ያለበት ሆኖ ነው የምናየው። ኬኒያ ዛሬ በፋሺስቱ አቢይ ዘመን ብቻ ሳይሆን ላለፉት አርባና ሃምሳ ዓመታት የምስራቃዊው የአፍሪካ ቀጠና በዲሞክራሲ፣ በኢኮኖሚ እድገት፣በአረንጋዴ ልማት፣በውስጣዊ የተረጋጋ ሰላም፣በጸረ አክራሪና አሸባሪ ኋይሎች ውጊያና በአፍሪካ የግዙፍ ስደተኞች መሸሸጊያ ሀገር በመሆን የቀጠናው መሪ የሆነች ሀገር ነች። ይህ አለሁ አለሁ ባይ ለሆነው እብዱ አቢይ አህመድ የሚዋጥ አልሆነምና በኬኒያ ላይ ያለው ቂምና ንዴት ኬኒያ እኔን እንደ ትልቅ ዝግባ ጋርዳኛለች በሚል የቅናት ንዴት የተመሰረተ በመሆኑ ዛቻና ፉከራው ተራ ጭንቀት የወለደው የእብደት ዛቻ ሳይሆን በትክክል ከመበለጥ የመነጨ ንዴት መሆኑን መረዳትና ማየት ያስፈልጋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአንድ አገር ህዝቦች ሁለት ዜግነት - ቬሮኒካ መላኩ

በእርግጥ ኬኒያ ትልቅ ጥፋት አጥፍታለች። ያም ጥፋት ከዚህ ከፋሺስቱ የኦሮሙማ ስርዓት ጋር በመተባበር ፋሺስቱ ከዩክሬይን የተላከልንን የእርዳታን ስንዴ ዶላር ፍለጋ ለመሸጥ ሲቅበዘበዝ ኬኒያ ተስማምታ የመግዛታ ጉዳይ ትልቅ ጥፋትና ስህተት ፈጽማለች ብሎ ይህ ጸሓፊ ያምናል። የስንዴና ጥራጥሬ ምርት አቅርቦት እጥረት የሌላት ኬኒያ ለርሃብተኞች የተላከን ስንዴ ከፋሺስቱ እጅ ተቀብላ መግዛት አልነበረባትም ብዬ በግሌ አምናለሁ። የሆነው ሆኖ ግን ኬኒያ ፋሺስቱ እንዳላት የስንዴና የባቄላ እጥረት የሌላባት ሀገር ከመሆናም በላይ የዛፍ ችግኞችን በተመለከተ ግን ኬኒያ ለኢትዮጲያ ብትልክ እንጂ ከኢትዮጱያ የዛፍ ችግኝ የምትቀበል ሀገር አይደለችም።

በኬኒያ ችግኝ አፍልቶ ዛፍ መትከል በመንግስታዊ ዘመቻ የሚሰራ ስራ ሳይሆን በእያንዳንዱ ኬኒያ ደም ስር ውስጥ ያለ የዘልማድ ባሕላዊ ስራ ነው። በዚህም ምክንያት ነው የሀገሪቱ ዋና ከተማ ናይሮቢ በደን የተሸነችና በየመንገዱም ችግኝ እያፈሉ በሚሸጡ ሰዎች ተጥለቅልቌ የምትታየው። በተጨማሪም የሀገሪቱ ዋና ከተማ ናይሮቢ ከእንበሳ ጁምሮ ዝሆን ቀጭኔ ነብርና መሰል የዱር አራዊቶች የሚርመሰመሱበትን ናይሮቢ ብሔራዊ ፓርክ (የናይሮቢ ደን) በዋና ከተማ ውስጥ በመያዝ የዓለማችን ብቸኛ ከተማ በመሆን የመንግስታቱ ድርጅት UN ጽህፈት ቤት ከኒዮርክና ከስዊዘርላንድ ጄኔቫ ቀጥሎ የናይሮቢው UNEP ጽህፈት ቤት ባለቤት ለመሆን የቻለቺው።

ስለዚህ እነዚህን እውነታዎችን ስንመለከት ከኢትዮጲያም አልፎ በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና እኔ ብቻ ነኝ ተደማጭ ሆኜ ፈላጭ ቆራጭ መሆን ያለብኝ ለሚለው ሁሉንም ኬኛ ባይ አቢይ አህመድ ኬኒያ በትክክል ዝግባ በመሆን እንደጋረደቺው በማየት ዛቻው ጭንቀት የወለደው ተራ የእብደት ዛቻ ሳይሆን መሰረታዊ የሆነ ምክንያት ያለውና ፋሺስቱ አቢይ ሁኔታዎች ከተመቻቹለት መፈጸም የሚፈልገው ውጥን ምስጢሮቹ መሆኑን ነው የምረዳው።

ወደ ኤርትራ ልመልሳችሁና – የኢሱና የአቢቹ ስንብት በሚል ርእስ ስር የሁለቱን ሃይሎች ስንጥቃትን የጻፍኩት ባለፈው ዓመት መስከረም 2022 ላይ ሲሆን የተፈጠረው ልዩነት ግን አቢይ ሉዓላዊት የሆነችውን የኤርትራን ሀገር አፍርሶ እስከመጠቅለል የሚያደርስ ህልምና እቅድ ይፈጥራል ብዬ አለመገመቴን ልሸሽግ አይገባም።

በወዲ አፈወርቅ የሚመራው የኤርትራ መንግስት ለፋሺስታዊው የኦሮሙማው ብልጽግና ቡድን ትልቁን ውለታ የዋለ – ይህ ፋሺስታዊ ቡድን ቢያንስ ዛሬ ላይ ያደረሰውን ስልጣን ይዞ ይህን ያህል እንዲቆይ ያስቻለውን መደላድሎችን በመፍጠር የኤርትራን መንግስት የሚያክል ታላቅ ውለታ የዋለ የለም። ፋሺስቱ አቢይ ግን መጀመሪያ «ሀ» ብሎና ከማንም ቀድሞ በሰኔ ወር 2018 ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ በማድረግ ፍቅሩን ድጋፉን በሰጠው የአዲስ አበባ ሕዝብ ላይ ክህደት በመፈጸም የጥቃት ዝናቡን ማዝነብ እንደጀመረ ሁሉ ለጥቆም ለአቢይ ወደ ስልጣን መምጣት ሌሎች ሳይገልጹ ታላቅ ድጋፉን በገለጸለት የትግራይ ሕዝብና ሰልሶ አማራ አቀፍ የድጋፍ ሰልፍ አድርጎ ፍቅር ክብርና ድጋፉን ለገለጸለት አማራ ሕዝብ ላይ የክህደት ሰንሰለቱን እያራዘመ መጀመሪያ በትግራይ ሕዝብ ላይ ለጥቆ በአማራ ሕዝብ ላይ እንደዘመተ ሁሉ አሁን ደግሞ የክህደት ሰንሰለቱን በማራዘም ባለውለታው በሆነው የኤርትራ መንግስትና የኤርትራ ሕዝብ ላይ የጥፋት ድግስ መደገሱን – ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል እንደሚባለው በነበልባሉ ፋኖ ፋታ ነሺ ቅጥቀጣ የተጨነቀው አቢይ ጭንቀት በወለደው እብደቱ ይህንን በውስጡ ያመቀውን ምስጢር እንዲናገር መገደዱን ነው የምንረዳው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አዲሱ የህወሓት ዕቅድ እና “ጠንቋይ” አክቲቪስቶቹ! - ስዩም ተሾመ

በሀገረ ኤርትራም ሆነ በመላው ዓለም ያሉ ኤርትራዊያን እንደማንኛውም ሕዝብ በመንግስታቸው ላይ ጥያቄ ሊኖራቸው ይችላል። መንግስታቸውን በጽኑ የሚደግፉ እንዳሉ የሚቃወሙም ይኖሩ ይሆናል። ግን አይደለም በኤርትራ መንግስት አምነው መንግስትን የሚደግፉት ይቅርና መንግስት ላይ ጥያቄ የሚያነሱት እንኴን ሳይቀር በኤርትራ ሉዓላዊነት ላይ አንዳቸውም ጥያቄ የላቸውም። ሁሉም በሚያስብል ደረጃ የኤርትራ ሉዓላዊነት ተከብሮ ተጠብቆ መቀጠል አለበት ብለው የሚያምኑ ናቸው። ዛሬ ፋሺስታዊው የኦሮሙማው ቡድን ቁንጮ አቢይ ብድግ ብሎ ይህንን ሕዝብ ነው የኤርትራን መንግስት አፍርሼ በመቀላቀል ኤርትራ የምትባል ሀገር እንዳትኖር አደርጋለሁ ብሎ ሲዝት መስማት የተቻለው።

እኛ አማራዊያን ግን ይህንን ፋሺስታዊን የእብደት ዛቻ – በወንድሞቻችን የኤርትራ ሕዝብና በኤርትራ መንግስት ላይ የተላለፈን ዛቻ በእኛ በአማራ ላይ የተላለፈ ዛቻና ጦርነት ብለን የምናየው በመሆኑ የኤርትራን ነጻነት ለመንጠቅ የሚደረግን ማንኛውንም ዓይነት ዘመቻና ፕሮፖጋንዳን በጥብቅ የምናወግዝና አጋርነታችንንም ለኤርትራዊያን በማድረግ ወራሪውን እንወጋለን እንጂ አንድም የአማራ ልጅ በጸረ ኤርትራ ዘመቻ ላይ የማይሳተፍ መሆኑን አስረግጠን በአቌም ደረጃ እንደ ሕዝብ የምንገልጸው አቌማችን ነው።

እንቁዎቻችሁን እሪያ ፊት አትጣሉ። ጭቃ ላይ ይረጋግጡታልና። የእግዚ አብሔር ቃል

የአቢይ ክህደት ሰንሰለት ማለቂያ የለውም። የአቢይ ተክለ ስብእና የተገነባው በክህደት፣በውሸት፣በጥላቻ ቅናት የተገነባ እሱ ራሱ ህይወት ያለው ክህደት ቅናት ጥላች ውሸት ሆኖ ስጋ ለብሶ የተከሰተ በመሆኑ ያከበሩትን የደገፉትን ከጎኑ ቆመው የረዱትንና ያገዙትን በሙሉ ከግለሰብ እስከ ማሕበረሰብ ከድርጅት እስከ የሀገር መንግስታት ያሉትን በሙሉ በሚቻለው መጠንና አቅም ሁሉ አንድ በአንድ ተመልሶ የሚበላ ሰው ነው።

ጠቢበኛው ሰለሞን እንቁዎቻችሁን እሪያ ፊት አትጣሉ ጭቃ ላይ ይረጋግጡታል ብሎ ሲናገር እንቁ ማለት – እውነት፣እምነት፣ፍቅር፣ክብር፣ታማኝነና ውለታ ሲሆን እሪያ ማለት ደግሞ እንሥሳው ሳይሆን እውነትን፣ፍቅርን፣እምነትን፣ክብርን፣ታማኝነትን እና ውለታን የማያውቅና የማያከብር ውለታ ቢስ የሆነ ሰው ነኝ ባይ ግን ስብእናዊው ግብሩ እንሥሳዊ የሆነ እንደ አቢይ አህመድ አይነቱን ነው እሪያ ብሎ የገለጸው።

እኛ አማራዊያን ግን በእጅጉ ተለይተን ከምንታወቅባቸው እንቁ እሴታዊ ስብእናዎቻችን ውስጥ ውለታን አክባሪነት፣ ለእውነትና ለእምነት ጹኑ አክባሪነትና ተገዢነት የምንታወቅበት የግብር መገለጫዎቻችን ሲሆን ይህን ድንቅ እንቁ ስብእናን ለማይገባው ሰው መሳይ ግን ግብሩ እሪያ ለሆነ ፈጽሞ መግለጽና መስጠት እንደሌለብን የፋሺስቱን ኡቢይ እኩይ ምግባር በጥሩ አስተማሪነት ተምሳሌት በመጥቀስ እደመድማለሁ።አበቃሁ።

 

7 Comments

  1. በእርግጥ የጸሃፊውን ማንነት ብንረዳ ከምን ማእዘን ሃሳቡን እንደሰጠ መረዳት ላይ እንደርስ ነበር፡፡ አብይ አህመድ ከዚህ በላይ ማለት ቢችልም ጸሃፊውን ቱግ ግንፍል አድርጎ ወደ ውጊያ ቀጠና ያስገባው አብይ ኤርትራን ጠቅልዬ አሰብን በቁጥጥሬ ስር አድርጌ ልዕለ ሃያል እሆናለሁ ያለው መሰለኝ፡፡ በበኩሌ አብይ ይህን መናገሩን አልሰማሁም ያየሁት ነገር ቢኖር ኢሳይያስ ቡና ሲያፈላ አብይ ቁርስ ማቅረቡን ነበር፡፡ ዛሬ አብይ ከትግሬዎች ታርቆ ኤርትራን እወራለሁ ቢል ተገማች ነበር፡፡ የፕሪቶሪያው ስምምነት አላማው ይህ ነበር የአማራ ክልል ወረራም ከዛው የቀጠለ ነው፡፡ በስምምነቱ መሰረት ጌታቸው ረዳም በተደጋጋሚ እንደገለጸው ወልቃይትና ጠገዴን አብይ ይሰጠናል ትንሽ ጠብቁኝ ነበር ያለው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ትግሬዎች ኤርትራን ይተናኮሳሉ ጦርነት ይነሳል የአብይ ሰራዊት ኤርትራ ጋር ሲዋጋ ትግሬ ሃይሉን አደርጅቶ ወደ ኋላ ይቆያል የደከመችውን ኤርትራ በጦር ወርሮ ታላቁን ትግሬ ትግርኛን አገር ይመሰርታል፡፡ ለህወአት አገርነት የኢትዮጵያ ልጆች በአብረሃ በላይ አማካይነት ያልቃሉ፡፡ ይህ ነው የደናቁርት ፖለቲካ፡፡ ፋኖ እንዲህ ሲዋደቅ የኤርትራ መንግስት አማራው ላይ ባለው ጥላቻ ሲያዛጋ አብይ በዛ በኩል ያለውን መተላለፊያ ከብቦታል፡፡ እንግዲህ ከወዲሁ ሁኔታውን ይህን ሲመስል ምንም እንኳን ኤርትራ አቅም ያለው ተዋጊ ሃይል ባይኖረውም ራሽያ የሰጠችው መሳሪያ ደቡብ አፍሪካን አልፎ ሊመታ ስለሚችል ካለበት ሳይንቀሳቀስ አብይ ቢሮው ውስጥ እንዳለ መጨረሻውን ያደርገዋል፡፡ አብይ የት እንዳለ ለማወቅ አዲስ አበባ እንደ አሸዋ የተበተነው ኤርትራዊ ስራው ስለላ ነውና፡፡ እስቲ ደግ ጊዜ ያምጣ፡፡
    እናስ ምን ይደረግ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ሁና እንድትቀጥል የሚፈልግ ሁሉ በአንድነት የትግሬዎችንና የአብይን ፕሮግራም ማክሸፍ ይጠበቅበታል፡፡ ይህ አካሄድ ለተራው ኦሮሞም ጥፋት ስለሆን የጁዋርን፤የመራራን፤የዳውድን፤የዲማንና ያበዱ ያረጁ መሪዎቹን ትቶ ከውንድሞቹ ጋር ሁኖ ይህንን ማእበል ካልቀለበሰ ከማንም በላይ ጥፋቱ ለእርሱ ይሆናል፡፡ እዚህ ላይ ቆም ብሎ ማሰብ ያለበት ኦሮምያ ብለው የሰሩት ክልል በስንት ክልሎች እንደ ተከበበ ማየት ነው፡፡

    • ልጅ ቢረጋ ጎሽ ነገሩ ሁሉ ግልጽ ሆኖ ታይቶሃል። ላንተ እንደተገለጠልህ እውነቱን እያዪ ፈቅደው ለታወሩ ሁሉ ይታያቸው እንላለን። ወያኔን አቅፎ አማራን የማሳደድ ተግባር ኤርትራን ከወያኔ ጋር በመሆን ለመውጋት ነው። ይህ ግን ሰው ያጫርሳል እንጂ ትርፍ አያመጣም። እዚያም እሳት እንዳለ መረዳት ግድ ይላል። በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ በአዲስ አበባና በሌሎችም የሃበሻ ምድር የሚርመሰመሱ ኤርትራዊያን ስራቸው ልክ እንዳለፈ ታሪካቸው ስለላና መዋጮ ማሰባሰብ ነው። አዲስ አበባ ላይ ተወልደው እግራቸው የኤርትራን መሬት ሳይረግጥ በናፍቆት እንባ ያፈሱ የነበሩ ዛሬ ዞረው ቅኝ አደረገችን ከሚሏት ሃገር በጥገኝነትና በሌላም ሰበብ ዞረው ሰፍረዋል። አብይ ጦርነት በኤርትራ ላይ ቢከፍት ከውስጥም ከውጭም የሚያመልጥበት ምንም መንገድ አይኖርም። ዝም ብሎ የሆነ ያልሆነ ቱልቱላ እየነፉ ሰውን ለሞት ከማዘጋጀት ለሰላም በሰላም ለመኖር ነገሮችን ማርገብና የዘርና የጎሳ ፓለቲካውን አክ እንትፍ ማለት መልካም ይመስለኛል።

  2. ፉከራና ሥራ ለየቅል ናቸው። ጊዜው ይራቅ እንጂ ያኔም የኤርትራን ሸማቂ ተዋጊዎች ቀይ ባህር ውስጥ እንከታቸዋለን በማለት ተደንፍቶ ነበር። ቆይቶ ላየው ቀይ ባህር የገባው ማን እንደሆነ ታሪክ ያሳየናል። ይህ የመገዳደል እልፈት የለሽ መከራ ግን አንድን ጀግና ሌላውን ሌላ የሚያደርግ አይደለም። ተያይዞ ማከክ እንጂ። ያኔ ሲያለቅሱ የነበሩ አይኖች ዛሬም በኤርትራም ሆነ ከቁራሽ በተረፈችው ኢትዮጵያ ያነባሉ። እነዚያ ሂደው እነዚህ መጡ ቢባልም የስም ለውጥ እንጂ ነጻነትና ብልጽግናን ለህዝባችን አላመጣም። የሃበሻው ወስላታ ፓለቲካ የመበላላት ፓለቲካ ነው የምንለውም ታሪክን ተንተርሰን እንጂ በስማ በለው ወሬ አይደለም።
    አሁን በአማራ ጥላቻ ሁለንተናው የጠቆረው ጠ/ሚ ያኔ ከአቶ ኢሳያስ ጋር ጫጉላ ቤት እንደ ወጡ ሙሹሮች ሲተቃቀፉና ሲሳሳሙ ላየ ሰው ነገርየው እንደማያዛልቅ ግልጽ ነበር። አቶ ኢሳያስ ባድሜን ከመቀበላቸው ባሻገር የወያኔ ከሥልጣን የመውረድም ደስታ አፍለቅልቋቸው በአስመራና በአዲስ አበባ ያሳዩት ፍቅር መሰል ነገር ጊዜአዊ እንጂ ዘላቂነት አልነበረውም። የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው ከሚል ስሌት የመነጨ ፍንደቃ ነበር። የወያኔና የሻቢያ ክፋት የጀመረው ገና ጫካ እያሉ እንጂ የከተማ አለቆች ከሆኑ በህዋላ አይደለም። ሁለቱ ድርጅቶች የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ነበሩ አሁንም በተንኮልና ክፋታቸው አንድ ናቸው። በዚህ መካከል ነው የኦሮሞ ጠባብ ብሄርተኞች የስልጣን ባለወረፋ የሆኑት። ልክ እንደ ወያኔ ከዓለም ዙሪያ ደጋፊዎቻቸውን ሁሉ እየጠሩ ስልጣን በመስጠትና በማስተናገድ ላይ እንደሚገኙ ጥብቅ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ጠ/ሚሩ የወታደራዊ መዋቅሩን ወያኔ ከላይ እስከ ታች ይዘውት እንደነበር በነገረን ማግስት አሁን ላይ ኦሮሞው ከላይ እስከ ታች ድረስ የወታደራዊውንና የሲቪሉን ሥራ ከመያዙም ሌላ የብልጽግናው ጠ/ሚ በይፋ በኮታ ኦሮሞ 45% በየሥራ መስኩ እንዲሰማራ መመሪያ ሰቷል። የፓለቲካ አፓርታይድ ይህ ነው። የሥራ ልምድ፤ እውቀትና ሌላውም መስፈርት ቀርቶ በዘርና በክልል ፓለቲካ ሰውን ያለስፍራው እየሸነቆሩ እንሆ ህዝባችን ዛሬም ኡኡታ ያሰማል። ሰሚ ግን የለም። ዝንተ ዓለም ለቅሶና ረሃብ። በነጻነት ስም ከበፊቱ የከፋ ባርነት። ይህ ነው የሃበሻ የፓለቲካ ለውጥ!
    ጠ/ሚ አብይ ወደብ አስመልሳለሁ፤ ኤርትራን ከኤትዮጵያ ጋር አንድ አረጋለሁ ማለቱ በህልም ዓለም ሆኖ እንጂ እውነት የሚሆን ቅዥት አይደለም። ላም ዓለኝ በሰማይ ወተቷን አላይ አይነት ነገር። ግን የፓለቲካ ታምቡር እየመቱ ለሃገርህ ለወገንህ ለድንበርህ የተወሰደብህን ለማስመለስ በሚል ሳቢያ ለማገዳደልና የራስን የፓለቲካ እድሜ ለማራዘም ለጊዜውም ቢሆን ይረዳ ይሆናል። ለዚህም ነው ሰራዊቱን በተኛበት ያረደውን ወያኔን አቅፎ ዛሬ አማራ ላይ ሰፊ ጥቃት የከፈተው። ይህን ያዝ ለቀቅ ሲጨንቅ ድረሱልኝ ፋታ ሲገኝ ከዓይኔ ጥፉ የተመለከተው ገጣሚ እንዲህ ብሎ የገጠመ።
    ማርከህ ታጠቅ ያለኝ የጨነቀው ለታ
    ሥልጣን አደላድሎ በደሜ ጠብታ
    ዛሬ ጠላት አርጎኝ ይላል ትጥቅ ፍታ።
    አማራን ትጥቅ የማስፈታት ዘመቻው ወያኔን ለማጎልበትና ኤርትራን ለመውጋት ካቀደው ሽፍድፍድ ዓላማ ጋር ግጥምጥም ነው። በዚህም በዚያም የሞት ጥሩንባ እየነፉ ብልጽግና የለም። እንካችሁ ብሎ ወያኔ በዓለም መድረክ ያስረከባትን ኤርትራ ዛሬ ወደብ፤ ሃገር ገለመሌ ማለቱም ጅላጅል መሆን ነው። ጠ/ሚሩ ያለ ልክ በገነባው ሰራዊት ይመካል። ግን የእንቧይ ካብ እንደሆነ አልገባውም። ዞር ብሎ በሰራዊት ብዛትና በትጥቅ ጥራት ብቻ ሃገርን ሃገር አድርጎ ማቆየት የቻለ የለም። ቁርጠኝነት፤ የሃገር ፍቅር፤ የሃገር አንድነትና ሌሎቹም የህብረተሰብ ቱሩፋቶች ሳይኖሩ ከላይ ቦንብ ከሥር እሳት ቢነድ የተፎከረለት ሰራዊት ግቡን አይመታም።
    ስለሆነም የቆየ ቁስል ውስጥ እንጨት እየሰደድ ሰውን ለውጊያ ከማነሳሳት ይልቅ የኤርትራም ሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ ተቻችሎና ተደጋግፎ የሚኖርበትን በህግ ላይ የተመሰረተ ግንኙነት መፍጠሩ ብልህነት ነው። የሰው ልጅ እስከ መቼ ጠበንጃ ተደግፎ እንዘጥ እንዘጥ እንዳለ ይኖራል? ገደብ አለው? ያበቃል? የሚመስል ጉዳይ አይደለም። ቆይተን እንይ! በቃኝ!

  3. The true reason for Abiy Ahmed’s war on Eritrea and Kenya is not his personal ambition but the Great Oromia project created by the west to destabilize the entire Horn of Africa. It is known that the original Oromia map of the OLF extends from Mombasa at the Southern tip of Kenya to Qarora on the northern most corner of Eritrea. OLF claims Bobbaasaa (Mombasa) and Qarora are Oromiffa words, indicating to whom these places belong. It is not just this one crazy guy, Abiy Ahmed, that lays a claim to places in Eritrea and Kenya. It is the the entire adherents of the Oromumma ideolgy (an East
    African version of Nazism and Lebensraum).

  4. የኤርትራው ጉዳይ ትንሽ ወደ እውነት ሊቀርብ ይችላል ስለኬንያ የተነሳው ግን አጠቃላይ ፀሃፊው ምን አይነት መልእክት ሊያስተላለፉ እንደፈለገ ጥያቄ ውስጥ ያስገባል

  5. ወንድ ወሰን ተክሉ አቶ ጌታቸው ረዳ (የአክሱሙ ኢትዮጵያዊ) ጥያቄ ጠይቆህ ነበር ስለተረትህ ይቅርታ ወይስ ማስተባበያ ሰጥተሃል?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share