ለብልፅግና አባላትና ለፓርላማ አባላት በሙሉ አድርሱልኝ

ይህ ቀጥሎ የምታዳምጡትን ንግግር ያደረጉት የብልፅግና ፓርቲ ሊቀመንበር የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ናቸው። በዚህ ንግግራቸው ላይ ጊዜው የአንድ ብሄር እንደሆነ በግልፅ ተናግረዋል። በመጀመሪያ ፓርላማው እንደ ፓርላማ ይህንን ንግግር ሰምቶ እንዴት በቁሙ ዝም ይላል? እንዴት ብዙህ የሆነችን ሀገርን የሚያስተዳድር ሰው ይህንን ይላል ብሎ ፓርላማው እንዴት አይቆጣም እንዴት እርምጃ አይወስድም?
ሁለተኛ የብልፅግና አባላት እኛ የታገልነው ለኢትዮጵያ አንድነት ነው። ጠቅላይ ሚንስትር ሆነህ እንዴት እንደዚህ ትላለህ? ይህ አባባል ለሶማሌ ክልል ለአማራ ክልል፣ ለትግራይ ክልል፣ ለደቡብ……. ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚያስተላልፈው መልእክት ምንድን ነው? ብሎ እንዴት አይጠየቅም። እንዴት የአመራር ለውጥ እንዲመጣ አይደረግም? ይህ ንግግር እኮ የፅንፈኝነት ቁንጮ ነው። ይህ ሰው ይህንን ሲናገር የዚህ ተቃራኒ የሆነ ፅንፈኝነት (counter extremism)   የሚያራባ ነገር ነው።
በሌላ በኩል ፊልድ ማርሻሉ ከወታደርነት ስነ ምግባር ወጥተው ስለተረኝነት ሲናገሩ እንዴት ነው የማይጠየቁት? እንዴት ነው ማእረጋቸው የማይነሳው? ከፍተኛ ፅንፈኝነት የሚባለው ይሄ እኮ ነው። በአጠቃላይ እናንተ የፓርላማ አባላትና የብልፅግና አባላት ሆይ በዚህ ወቅት በየክልሉ ያሉ አመፆች ከዚህ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ፍላጎት ጋር ተያይዞ የመጣ ነው። ስለዚህ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጠይቁ። ከስልጣን አንሱ።
ሃቀኛ የፓለቲካ ፓርቲዎችም ደግሞ ይህንን ንግግር ይዛችሁ ወደ ፍርድ ቤት ሂዱ። ክሰሱ። አለበለዚያ ህዝብን ማታገል ካልቻልን በተቃዋሚ ስም አንነግድ።

ከአክብሮቴ ጋር
ገለታው
ተጨማሪ ያንብቡ:  የአማራ ፋኖ በድል የታጀበው ጉዞ | አዲስ አበባ ላይ ያንጃበበው እልቂት | የኦሮሙማው ቡድን የድንጋጤ ምንጭ

1 Comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share