የኮነሬል አብይ የነፍስ ገበያ በኢትዮጵያ!!! አንድ ሐሙስ የቀረው ጊዜ የሠጠው ነፍስ የሚሸጥ መንግሥት!!!

ክፍል  ሁለት

ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ)

የኮነሬል አብይ አህመድ ኦህዴድ ብልፅግና መንግሥት በሃገሪቱ ያሉ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ከተፎካካሪ ፓርቲዎችና ከህዝብ ጋር አብሮ ከመፍታት ይልቅ ለሌላ ጦርነትና የአማራን ህዝብ ለመጨፍጨፍ እቅድ ነድፈው አገር በማተራመስ ላይ ይገኛሉ፡፡ ኦህዴድ ብልፅግና መንግሥት በካፒታል ኩብለላ፣ በኮራፕሽን፣ በወታደራዊ ወጪ፣  የነዳጅ ወጪ፣ማዳበሪያ ወጪ፣ የወደብ አገልግሎት ክፍያ፣ የምግብ ዘይት ወጪ፣  ከፍተኛ የዋጋ ግሽበትና በአጠቃላይ  የኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ ዳሰሳ በማድረግ የመንግሥታዊ ወጪ የፓርኮች ግንባታ፣  የወንዝ ዳር ልማት ግንባታ፣ የቤተመንግሥት ግንባታ፣ የሸገር ከተማ ግንባታ፣ መንግሥታዊ ወጪ በመጨመር ሃገሪቱን ኢኮኖሚ ወደ አዘቅት ውስጥ በመክተት ላይ ይገኛሉ፡፡ መረጃውን እንሆ፡-

  • በ2023 እኤአ የኢትዮጵያ ስብአዊ ድጋፍ (Ethiopia Humanitarian Response Plan (HRP)) እቅድ መሠረት በመላ ሃገሪቱ ለሚገኙ ሃያ ሚሊዮን ህዝብ ስብዓዊ ረድኤት ድጋፍ ለማቅረብ US$3.99 (ሦስት ነጥብ ዘጠና ዘጠኝ ቢሊዮን) ዶላር እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡ ከዚህ አሃዝ ውስጥ 4.6 ( አራት ነጥብ ስድስት) ሚሊዮን ህዝብ በአረጋቸው ውስጥ ከቀያቸው የተፈናቀሉ እንደሆነ ተገልጾል፡፡ The 2023 Ethiopia Humanitarian Response Plan (HRP) requires US$3.99 billion to target more than 20 millionpeople across the country. This includes an estimated 4.6 million internally displaced people (IDPs).Feb 28, 2023
  • ግሎባልኢኖቨሽን መለኪያ (Global Innovation Index) ኢትዮጵያ በወርልድ ኢንቴሌክችዋል ፕሮፐርቲ ኦርጋናይዤሽን  አመታዊ ጥናት መሠረት በግሎባል ኢኖቬን መለኪያ ከ132 አገሮች3 ነጥብ በማግኘት   117ኛ ወጥታለች፡፡ ሲዊዘርላንድ አንደኛ በመውጣት 64.6 ነጥብ አግኝታለች፡፡  In the Global Innovation Index,  Ethiopia ranked 117th in 2022 with 16.3 points. The index is calculated annually by the World Intellectual Property Organization  (WIPO) and most recently included 132 countries. The top country was Switzerland with 64.6 points.

{1} ካፒታል ኩብለላ (Capital flight)፡- ከሃገሪቱ በህገወጥ መንገድ የሚወጣ የውጪ ምንዛሪ ካፒታል ኩብለላ Capital flight ከ2 እስከ 3 ቢሊዮን ዶላር በአመት እንደሚደርስ የአፍሪካው ልጅ  ታቡ ኢንቤኪ አጋልጠዋል፡፡ በኦህዴድ/ብልፅግና መንግሥት አምስት ዓመት አገዛዝ ዘመን የውጭ ምንዛሪ ኩብለላ ዋና ተዋናዬች ከፍተኛ የመንግስት ሹማምንቶች የሚከወን ሲሆን በሃገሪቱ በሚስተዋለው ህዝባዊ እንቢተኛነትና አመጽ ፍራቻ የተነሳ እንደሆነ ይታመናል፡፡ በሃገሪቱ የብር የመግዛት አቅመ ከጊዜ ወደ ጊዜ መውደቅ የተነሳና በብሔራዊ ባንክ የብር የማርከስ ሂደት፣ በእቃዎች ዋጋ እየጨመረ መሄድ የኑሮ ውድነት እየተባባሰ የሚሄደው በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ከሀገር ውስጥ መኮብለል የተነሳ ሁኔታውን አባብሶታል፡፡ An economist recently interviewed on ESAT (Ethiopian Satellite Television  and Radio)  indicated the illicit foreign currency leaving Ethiopia is now reaching over US $3 billion dollars. This, the economist added, is a worrisome trend and Ethiopia is now among the top countries in Africa where illicit trafficking of foreign currency is a big problem….(1)

በደርግ ወታደራዊ አገዛዝ ዘመን ከ 1970 እስከ 2012እኤአ አጠቃላይ ካፒታል ኩብለላ 31(ሠላሳ አንድ) ቢሊዮን ዶላር ሲገመት በየአመቱ ግማሽ ቢሊዮን ዶላር ከአገር ይወጣ እንደነበር ጥናቱ ያመላክታል፡፡ በህወኃት/ኢህአዲግ መንግስት ዘመን ከ1991 እስከ 2018እኤአ የካፒታል ኩብለላ በየአመቱ አንድ ቢሊዮን ዶላር ከአገር የወጣ ሃያ ሰባት ቢሊዮን ዶላር ይገመታል:: በህወሃግ/ኢህአዲግ በህገወጥ መንገድ ከሃገር ውስጥ የወጣ ካፒታልና የንዋይ ኩብለላ 27 (ሃያ ሰባት) ቢሊዩን ዩኤስ ዶለር ከኢትዬጵያ  ረሃብተኛ ህዝብ ተሰርቆ ወደ ተለያዩ ባህር ማዶ አገራት ተቀምጦል፡፡  We find that the total real capital flight during the 1970–2012 period is about US$31 billion. On average, the country has lost around half a billion dollars annually under the ‘Derg’ regime. This amount more than doubled to over 1 billion per annum during the EPRDF regime.

{2} የህዝብ ኃብት ዘረፋ Corruption in Ethiopiaበኢትዮጵያ ውስጥ ስር የሠደደ የሙስና ዝርፍያ ወንጀል የተነሳ የሃገሪቱ ልማት እድገት ተጨናግፎል፡፡በ2020 እኤአ ትራንስፓራንሲ ኢንተርናሽናል ባዘጋጀው 38 የሙስና  መለኪያ ከመቶ ሰማንያ አገሮች ዘጠና  አራተኛ ደረጃ ስታገኝ በዓለም ፕሬስ ፍሪደም መለኪያ ኢትዮጵያ መቶ አንደኛ ደረጃ ከመቶ ሰማንያ አገሮች ዉጤት አግኝታለች፡፡ Pervasive corruption remains to be one of the most serious challenges hampering the country’s development.4 The Transparency International 2020 Corruption Perception Index awarded 38 points to Ethiopia, ranking it 94th out of 180 countries and Ethiopia ranks 101 out of 180 in the World Press Freedom Index.5

የኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት የሃገሪቱን የመሬት ኃብት በመቆጣጠር በተለይ በአዲስ አበባ ውስጥ ያሉ ቦታዎችን ሁሉ በፓርኮች ስም፣ በመንግስታዊ ቢሮዎች መገንቢያ ስም፣ በቤተመንግስት መገንቢያ ስም፣ በወንዞች ዳር ልማት ስም፣ በእሬቻ ማክበሪያ ስም ወዘተ ሁሉንም ቦታዎች ኮነሬል አብይ አህመድ ተቆጣጥሮታል፡፡ በኢትዮጵያ ልዩ ልዩ  የኢኮኖሚ ዘርፎች ወስጥ  የንግዱ ህብረተሰብ ለሙስና የተጋለጠ ነው፡፡ የመሬት ኃብት ክፍፍልና አስተዳደር መንግስታዊ ቢሮ ተቌማዊ የሙስና መፈልፈያ ሲሆን ነጋዴዎችና አልሚዎች መሬት በጠየቁ ጊዜት ከፍተኛ ጉቦ ይጠየቃሉ፡፡ There are several sectors in Ethiopia where businesses are particularly vulnerable to  corruption.  Land distribution and administration is a sector where corruption is institutionalized, and facilitation payments as well as  bribes are often demanded from businesses when they deal with land-related issues.[1]……(2)

{3} ኢትዮጵያ  ወታደራዊ ወጪ ( Ethiopia Military expenditure-)እንደ  ስቶክሆልም  ኢንተርናሽናል  ፒስ ሪሰርች   ኢንስቲቲውሽን ጥናት  መሠረት፣  ዓለም አቀፍና የሃገራት ወታደራዊ ወጪ አፕሪል 24 ቀን 2023 እኤአ  ባወጣው  መረጃ  መሠረት  ኢትዮጵያ   ወታደራዊ ወጪ አንድ ቢሊዮን  ዶላር  (ሃምሳአራት  ቢሊዮን ብር)    2022 እኤአ እንደደረሰና ከአለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር 88 (የሰማንያ ስምንት) በመቶ   እድገት  እንዳሳየ   ዘግበዋል፡፡ Addis Abeba – According to new data on global military spending published on Monday, 24 April, by the Stockholm International Peace Research Institute (SIPRI), Ethiopia spent 1 billion USD on military expenditures in 2022, showing an increase of 88 percent from the previous year.…………(3)

ተጨማሪ ያንብቡ:  በአፋር ክልል ወጣቶች ለውትድርና በግዴታ እየታፈሱ ነው

ኢትዮጵያ  ወታደራዊ ወጪ ከሃያ አምስት ቢሊዮን ብር ወደ መቶ ቢሊዮን ብር በኮነሬል አብይ ዘመን ተመንድጎል፡፡ የ2022/ 2023 እኤአ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ገንዘብና ፋይናንስ  ሚኒስቴር  የኢትዮጵያ አጠቃላይ በጀት 785 (ሰባት መቶ ሰማንያ አምስት) ቢሊዮን ብር አጽድቆል፡፡ ከባጀቱ ውስጥ የወታደራዊ ወጪ 100 (መቶ) ቢሊዮን ብር መሆኑ  ተገልፆል፡፡  የኢትዮጵያ  ወታደራዊ ወጪ የጠቅላላ የሃገሪቱ በጀት 13 በመቶ ድርሻ  አለው፡፡  የኢትዮጵያ ወታደራዊ ወጪ ከጠቅላላ የሃገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) ድርሻ ጋር ሲነፃፀር Military expenditure as percentage of gross domestic product (GDP) in 2020 እኤአ 0.5 (ዜሮ ነጥብ አምስት) በመቶ  ነበር፡፡ በዚህ መሠረት ከ2021 እስከ 2023 እኤአ  የኢትዮጵያ ወታደራዊ ወጪ ከጂዲፒ ድርሻ ጋር ሲነፃፀር ከ 0.5 እስከ 1.5 በመቶ   እንደሚሆን ይገመታል፡፡

{4}  የኢትዮጵያ የነዳጅ ወጪ (oil import)  አራት ቢሊዮን ዶላር ወይም (ሁለት መቶ አስራስድስት)ቢሊየን  ብር በአመት ወጪ ሲኖርባት፣ በሌላ በኩል ኢትዮጵያ 194 (አንድ መቶ ዘጠና አራት)  ቢሊዮን ብር የነዳጅ እዳ እንዳለባት ይታወቃል፡፡  Ethiopia will soon start importing cheaper refined oil from South Sudan to cover the more expensive product from the Middle East. Ethiopia’s State Minister for Mines and Petroleum, Koang Tutlam announced on Wednesday that the move will save Addis Ababa 15 per cent to 20 per cent on the $3.4 billion it spends importing an estimate of four million tonnes of refined products…… South Sudan has oil reserves estimated at 3.5 billion barrels which is the third-largest oil reserve in Sub-Saharan with most of its oil unexplored…….(4)

Sudan oil export to Ethiopia ሱዳን ለኢትዩጵያ መንግስት  አራት ሚሊዮን ቶን የተጣራ ነዳጅ በመሸጥ $3.4  (ሦስት ነጥብ አራት) ቢሊዮን ዶላር የነዳጅ ፍጆታ ሺያጭ ወጪ ታወጣለች፡፡ ሱዳን  ሦስት ነጥብ አምስት  ቢሊዮን በርሜል የነዳጅ ክምችት ያላት አገር ስትሆን አሁን በተነሳው የሁለቱ ጀነራሎች የሱዳን ጦርነት የነዳጅ ክምችቱ አደጋ ላይ ሲሆን ኢትዮጵያም ከሱዳን ነዳጅ ለማግኘት ያላት ተስፋ የተመናመነ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ በአዲስ አበባ ከተማና በክልሎች ከተሞች የነዳጅ እጥረት ተከስቶል፡፡

{5} የማዳበሪያ ወጪ (fertilizer):-  ኢትዮጵያ ለግብርናው ዘርፍ ኢኮኖሚ ለማዳበሪያ ግዢ 1.2 (አንድ ቢሊዮን ሁለት መቶ ሚሊዮን) ዶላር ወጪ ተዳርጋለች፡፡ ኢትዮጵያ  በአለፈው  አመት በዓለም አቀፍ ንግድ ገበያ የማዳበሪያ ዋጋ እጥፍ በመጨመሩ የተነሳ ከስድስት መቶ ሚሊዮን ዶላር ወደ አንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ወጪ ተዳርጋለች፡፡ Last year, the price of fertilizer more than doubled in the international market, a situation that have bulged Ethiopia’s annual budget for the commodity from USD 600 million to USD 1.2 billion.Sep 24, 2022 ኢትዮጵያ በጅቡቲ ወደብ በኩል አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ፈርቲላይዘር ለማስገባት አቅዳላች፡፡ Ethiopia plans to import more than 1.2 million metric tons of fertilizer through Djibouti ports for the current farming season.Dec 28, 2022…..(5)

የቢቢሲ አማርና ዜና መሠረት አንድ ኩንታል ማዳበሪያ ዋጋ አምና አንድ ሽህ ሰባት መቶ ብር የነበረ ሲሆን ከእጥፍ በላይ በመጨመር አራት ሽህ አምስት መቶ ብር በኩንታል በመሆኑ የተነሳ ገበሬዋች በማዳበሪያ ውድነት የተነሳ መሬት ጦሙን ያድራል ብለው ፈርተዋል፡፡BBC Amharic has recently reported that a quintal of fertilizer had a price tag of 1,700 ETB last year which now cost more than double, 4,500 ETB per quintal. Farmers fear their land could go without being ploughed this farming season due to the soaring price of fertilizers. Rising inflation is what the farmers said would have a major impact on their products……(6)

{6} የኢትዮጵያ የወደብ አገልግሎት ክፍያ (Port Services) ኢትዮጵያ ለወደብ አገልግሎት ክፍያ ወጪ በአመት ሦስት ቢሊዮን ዶላር ወጪ ታደርጋለች፡፡ ኢትዩጵያ 85 በመቶ የሚሆነውን የውጪና ገቢ ንግድ በጂቡቲ ወደብ በኩል በመጠቀም እስከ 3 ቢሊዩን ዶላር ወጪ ታደርጋለች፡፡ የጂቡቲ መንግስት  ወደ ኢትዩጵያ በሚገቡ ዕቃዎች  ላይ አዲስ  ክፍያ ማለትም ዕቃዎቹን በዘመናዊ መሣሪያ በመፈተሸ በአንድ ኮንቴይነር ዕቃ፣ ከአስር እስከ 35 ዶላር ለማስከፈል እዲስ ዕቅድ አውጥቶል፡፡ ሃገሪቱ ለጅቡቲ የወደብ አገልግሎት  የምትከፍለው በአመት ከ2.5 እስከ 3 ቢሊዩን ዶላር የወደብ አገልግሎት ወጪ መክፈል ይጠበቅባታል፡፡

{7} የምግብ ዘይት ወጪ (Ethiopia edible oil):- የኮነሬል አብይ መንግሥት ለምግብ ዘይት ወጪ 48 (አርባ ስምንት) ሚሊዮን ዶላር በወር ወጪ እንደሚወጣና 57.2 ሚሊዮን ሊትር ዘይት በየወሩ እንደሚያስፈልግ  ታውቆል፡፡  የኢትዮጵያ የምግብ ዘይት አመታዊ ወጪ 576 (አምስት መቶ ሰባ ስድስት) ሚሊዮን ዶላር እንደሆነ የሀገሪቱ ጠቅላላ የውጭ ንግድ (ኢንፖርት) 15 (አስራአምስት) ቢሊዮን ዶላር  እንደነበረ በመረጃው ተዘግቦል፡፡ The federal government spends USD48 million every month to import edible oil, underscoring the pressing need for import substitution, Ministry of Trade & Industry said. While import of edible oil is almost USD576 million annually, it accounts for almost five percent of the country’s imports, which stood at USD15 billion during the last fiscal year…. Minister of Trade & Industry, mentioning the country needs 57.2 million liters of oil every month. …….(7)

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሚሊዮኖች ድምጽ - የእሪታ ቀን ሰልፍ በሚያዚያ 26 ቀን እንደሚደረግ የአዲስ አበባ አስተዳደሩ እውቅና ሰጠ !

{8} የዋጋ ግሽበት (Inflation) በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት 34.2 በመቶ በማርች 2023 እኤአ የነበረ ሲሆን 2022 እኤአ በተመሳሳይ ወር ጋር አንድ ዓይነት ነበር፡፡ Inflation Rate in Ethiopia increased by 34.2 % in March 2023 over the same month in the previous year.(Central Statistical Agency.) የዋጋ ግሽበት፤ የእቃዎችና ምርቶች የዋጋ መናር ዋና ምክንያቶ ውስጥ የመንግሥታ ወጪ መጨመር፣ ከባንክ ውጪ  የሚቀመጥ ገንዘብ፣ የገንዘብ ዝውውር መጨመር፣ የውጪ ንግድ፣ የታክስ መቀነስ፣የሠራተኛ ማህበራት፣ ቀጥተኛ ያልሆነ ታክስ መጫን የመሳሰሉት የዋጋ ግሽበት ያስከትላሉ፡፡ የግብርና ምርቶቸደና የፋብሪካ ሸቀጣ ሸቀጦች ዋጋ መጨመር፣ የሸማቾች ፍላጎት መጨመር፣ ዕለት በዕለት የእቃዎች ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ   እያስከተለ የዎጋ ንረት ያስከትላል፡፡ በዚህም የተነሳ በኢትዮጵያ የዋጋ ንረት (Ethiopia: Inflation rate)  ስንመለከት፤ በ2020 እኤአ 20.35በመቶ፣ በ2021እኤአ 26.79 በመቶ፣ በ2022እኤአ 33.94 በመቶ እንዲሁም በ2023 እኤአ 31.43 በመቶ የዋጋ ግሽበት ተስተውሎል፡፡

የኦህዴድ ብልጽግና የኦሮሙማ መስፋፋት በሁሉም ክልሎች ድንበር በኩል የድንበር ግጪት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ የኦሮሞ ምሁራን ይሄንን የግዛት የመስፋፋት ጥያቄ የአስራስድስተኛውና የአስራሰበተኛው ዘመን ጥያቄ መሆኑን በማጤን ለኦሮሞ ህዝብ ጠላት አታብዙበት እንላለን፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወገኖቹ ጋር በሠላምና በህብረት እንዲኖር ማድረግ ይጠበቅባችሆል፡፡  {1} በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ የተመሠረተው ሸገር ከተማ ኖሪ የነበሩ መቶ ሽህ ዜጎች ቤታቸው ፈርሶ የከተማ ተፈናቃዬች ሆነዋል፡፡{2} በአብይ ዘመን የሚገነባው የጫካው ከተማ ፕሮጀክት አንድ ትሪለየን ብር ወጪ የገንዘቡ ምንጭ ምስጢር  ከኢትዮጵያ የብድር ግምጃ ቤት በብድር ስም የተመዘበረና ከአረብ አገር ንጉሶች በልመና የተገኘ ሊሆን እንደሚችል ይጠረጠራል፡፡   {3} የአማራ ክልልና የደቡብ ክልል የመንግሥት ሠራተኞች መንግሥት ለሠራተኛው የሚከፈለው ደሞዝ በማጣቱ አቤቱታ አሰምተዋል፡፡ የደቡብ ክልል ሃዲያ ዞን የመንግሥት ሠራተኞችከጥር ወር ጀምሮ ደሞዝ ስላልተከፈላቸው ህዝባዊ አመጸ በማድረግ ከአዲስ አበባ ወደ አርባምንጭ ሚወስደውን መንገድ ዘግተዋል፡፡ መንግሥት የህዝብ የጡረተኛ ገንዘብን እየበላ ከመጣ፣ ህዝብ መንግሥትን መብላቱ አይቀሬ ነው!!!

{4} መንግሥት መር የቤት ሠራተኛ ምልመላ መርሃግብር (A state-sponsored recruitment programme-) የብልፅግና መንግሥት 500,000 (አምስት መቶ ሽህ) ሴቶችን እድሜቸው ከ18 እስከ 40 የሚደርሱትን የቤት ሠራተኞችን መልምሎና አሠልጥኖ ወደ ሳውዲ አረቢያ ለመላክ ማቀዱን አስታውቆል፡  በቤት ሠራተኛነት ከሚመለመሉት አምስት መቶ ሽህ ሴቶች ውስጥ መቶ ሃምስ ሽህ ሴቶች ከአማራ ክልል ውስጥ እንደሚገኙ ታውቆል፡፡ መንግሥት ከምልመላ፣ከሥልጠናና የአይሮፐላን መጎጎዣ ክፍያን በመፈፀም ወደ ሳውዲ አረቢያ የመላክ መርሃግብር ፈጻሚ ነወ፡፡ የቤት ሠራተኞቹ አንድ ሽህ የሪያድ በወር ወይም ሁለት መቶ ስልሳ ስድስት ዶላር ክፍያ በወር ያገኛሉ፡፡ በዚህ መሠረት መንግሥት     (አምስት መቶ ሽህ ሲባዛ  ሁለት መቶ ስልሳ ስድስት ዶላር ይሆናል 133,000,000 (መቶ ሠላሳ ሦስት ሚሊዮን) ዶላር በወር እንዲሁም 1,596,000,000 (አንድ ቢሊዮን አምስት መቶ ዘጠና ስድስት) ሚሊዮን ዶላር በአመት) ለማግኘት መንግሥት መር የቤት ሠራተኛ ምልመላ መርሃ-ግብር ዘርግቷል፡፡ የሳውዲ አረቢያ መንግሥት የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት በማድረግ በዓለም አቀፍ የስብዓዊ መብቶች ተሞጋቾች ብዙ ሪፖርቶች የቀረበበት መንግሥት ነው፡፡ በ2020 እኤአ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ የአንዲት ኢትዮጵያዊት ሠራተኛ አሰቃቂ ድብደባና ግድያን በተመለከተ  የሳውዲ መንግሥትን ዘመናዊ ባርነት የሚያወግዝ ውሳኔ አስተላልፎ ነበር፡፡ የኮነሬል አብይ የብልፅግና መንግሥት ትላንት ከሳውዲ አረቢያ በመቶ ሽዎች ኢትዮጵያዊ ሠራተኞች አስወጣሁ ባለበት አፉ ዛሬ ግማሽ ሚሊዮን ሠራተኞች በነፍስ ገበያ በማቅረብ ዶላር ማጨድ ጎመዥቶል፡፡ ኦነግ/ኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት የነፍስ ገበያ፣ ዶላር ፍለጋ በጨረቃ ማለት ነው፡፡  A state-sponsored recruitment programme “Due to our country’s strong diplomatic ties with Saudi Arabia, job opportunities for 500,000 Ethiopians, including 150,000 from [the Amhara] region have been made available,” Tsehaye Bogale, a communications official in Ethiopia’s Amhara regional administration said in an official communique. Under the programme, women will board flights paid for by the government. In Saudi Arabia, migrant workers may earn 1,000 riyals monthly (about $266), more than most jobs on offer in Ethiopia where the per capita annual gross domestic product (GDP) was $925 in 2021………………(8)

{5} መንግሥት መር የውትድርና አገልግሎት ምልመላ መርሃግብር (A state-sponsored Military Service recruitment programme-) የኦነግ/ኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት መር የውትድርና አገልግሎት ምልመላ መርሃ-ግብር  በቅርቡ መጀመር ይፈልጋል፡፡ በትግራይና በኤርትራ የበድሜ ጦርነት መቶ ሽህ ወጣቶች ገብረናል፣ በትግራይና አማራ/አፋር የሁለት አመታት ጦርነት አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ሽህ ወጠቶች ገብረናል፣ በመቶ ሽህዎች አካላቸው ጎሎል፣ ሚሊዮኖች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ ዛሬ ደግሞ የአማራና ኦሮሞ ወጣቶች እንደቅጠል እንዲረግፉ የጦርነት አዋጅ ታውጆል፡፡  ይህን የአሜሪካና አውሮፓ የፖለቲካ ሴራ አስፈፀሚ ኮነሬል አብይ አህመድ፣ ወልቃይትና ራያን ለወያኔ በመስጠት፣ እንደ እጅ መንሻ የአማራን ሚሊዮን ወጣቶችን ለመገበርና የደም ገንዘብ ዶላር ለማግኘት አልመዋል፡፡ በኢትዮጵያ ዳግም የውትድርና አገልግሎት ለመጀመር ፊሽካ እየነፉ ነው፡፡ ኦነግ/ኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት የነፍስ ገበያ፣ ዶላር ፍለጋ በጨረቃ ማለት ነው፡፡

{6}  3.5 ሚሊዮን ህፃናቶች ትምህርት ቤት አይሄዱም፡- እንደ ሴቭ ዘ ችልድረን ኢንተርናሽናል መረጃ መሠረት ከአስራስድስት ህፃናት አንዱ ትምህርት ቤት እንደማይሄድ ጥናቱ ያስረዳል፡፡ ከኢትዮጵያ  ከመቶ ሃያ ሚሊዩን ህዝብ ውስጥም ሲሰላ 46.4 በመቶ ማለትም ሃምሳ አምስት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ህጻናቶች ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥ ሦስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ህፃናቶች ትምህርት ቤት እንደማይከታተሉ መረጃው ይጠቁማል፡፡ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት ሁለት ነጥብ ሦስት ሚሊዮን ህፃናቶች ትምህርት ቤት እንደማይሄዱና ትምህርት እንዳቆረጡ መረጃው ይጠቁማል፡፡ *1 in every 16 children being out of school is based on the population of Ethiopia 120,000,000 divided by the share of population that are children 46.4%, which makes the estimated number of children in Ethiopia 55.6 million and 3.5 million of them are out of school.Apr 12, 2023 ……….(9)

ተጨማሪ ያንብቡ:  በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የተገደለችው የወጣት ሃይማኖት በዳዳ ተጠርጣሪ ገዳይ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ፡


{7} ወላጅ የሌላቸው ልጆች (orphans)፡-በኢትዮጵያ ወላጅ የሌላቸው ህፃናቶች አስራ ሦስት በመቶ ከህዝብ ብዛት ውስጥ እናት ወይም አባት ወይም ሁለቱንም ወላጆች ያጡ እንደሆነ ይገመታል፡፡ በኢትዮጵያ ወላጅ የሌላቸው ህጻናት አራት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ሲሆኑ ከዚህ ውስጥ ስምንት መቶ ሽህ በኤችአይቪ/ኤድስ ወላጆቻቸውን ያጡ ናቸው፡፡  ( ኦነግ/ኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት የነፍስ ገበያ፣ ወላጅ የሌላቸው ህፃናት ህይወት ያሳዝናል፡፡   Ethiopia also has one of the largest populations of orphans in the world: 13 per cent of children throughout the country are missing one or both parents. This represents an estimated 4.6 million children – more than 800,000 of whom were orphaned by HIV/AIDS.

{8} አካላቸው የጎደለ ወገኞች (persons with disabilities) በዓለም ጤና ጥበቃ አካላቸው የጎደለ ሰዎች  ሪፖርት መሠረት በኢትዮጵያ አስራአምስት ሚሊዮን ሰዎች ህጻናት፣ ጎልማሶችና አረጋዊን ሲኖሩ ከህዝቡ ብዛት አስራአሳት ነጥብ ስድስት በመቶ እንደሚሆኑ ይገመታል፡፡ Dec 5, 2001 — According to this report from the total population of 53 million it was revealed that 991,916 i.e, 1.85 % were persons with disabilities . On …How many people are disabled in Ethiopia?  Based on the World Report on Disability jointly issued by the World Bank and World Health Organisation1, there are an estimated 15 million children, adults and elderly persons with disabilities in Ethiopia, representing 17.6 per cent of the population. ( ኦነግ/ኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት የነፍስ ገበያ፣ አካላቸው የጎደለ ወገኞች ህይወት ያሳዝናል፡፡

{9} ሠላሳ ሚሊዮን ሥራ አጥ ወጣቶች (Unemployment) ፡-  የወያኔ ኢህአዴግ ዘመን በኢትዮጵያ ሠላሳ ሚሊዮን ሥራ አጥ ወጣቶች ይገኙ ነበር  በዛም የተነሳ መንግሥት ‹‹የመቆቆሚያ ፈንዱ ምንጭ የፌዴራል መንግሥት የሚመድበው አሥር ቢሊዩን ብር በጀት እንደሚሆን አዋጁ ተደንግጎ ነበር፡፡ ከኢትዩጵያ ህዝብ 70 በመቶ ወጣቶች ሲሆኑ፣ ‹‹ ከፈንዱ ተጠቃሚ መሆን የሚችሉት ከ18 እሰከ 34 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ማንኛውም  ኢትዩጵያዊያን መሆናቸውን አዋጁ ያመላክት ነበር፡፡ አዋጁ ለሰላሣ ሚሊዩን ወጣቶች አሥር ቢሊዩን ብር ብድር ማለት 334 ብር የነፍስ ወከፍ ብድር ድርሻ ነበር፡፡  ከሰላሣ ሚሊዩን ሥራ አጥ ወጣቶች ውስጥ  በኦሮሚያ ክልል 10,314,270 ሚሊዩን፣በአማራ ክልል 8,024,773 ሚሊዩን፣አፋር (618,827)፣ ትግራይ (1,578,463)፣ ሶማሌ (1,806,539)፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ (338,433)፣ ደቡብ (5,643,731)፣ ጋምቤላ (150,414)፣ ሐረሪ (80,259)፣ አዲስአበባ (1,255,486)፣ ድሬዳዋ (164,762) ጠቅላላ ድምር (29,975,958)  ምንጭ፡- የፌዴራል ከተሞች ሥራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ( ኦነግ/ኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት የነፍስ ገበያ፣ ሥራ አጥ ወጣቶች ህይወት ያሳዝናል፡፡

{10} በኢትዮጵያ የወጣት የስደተኞች ቁጥር () አዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ ታህሥስ 17 ቀን 2009/ ‹‹ምጣኔ ሃብት ሲያድግ ስደት ለምን?›› በሚል ርዕስ  በኢትዩጵያ  በዓመት  ከአንድ ሽህ ዜጎች መካከል ዘጠኙ ወደ ሌሎች አገራት ይሰደዳሉ፡፡ 2015እኤአ በኢትዩጵያ የሥነህዝብ  ቁጥር  99,465,819 ሚሊዩን ውስጥ 895,192 ሽህ  ህዝብ  በዓመት  እንደሚሰደዱ በአይኦኤም መረጃ ተገልፆል  በኢትጵያ ውስጥ በየዓመቱ ሁለት ሚሊዩን ታዳጊዎች ወደ ወጣት የዕድሜ ክልል ይገባሉ በዚህም የተነሳ 1.4 ሚሊዩን  ወጣቶች አዲስ የስራ እድል ሊከፈትላቸው ይገባል ማለት ነው፡፡ ባለሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ እድገት አሳየች የምትባለው ሃገር የስደት ችግርን ለመፍታት አቅቶታል፡፡  ኦነግ/ኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት የነፍስ ገበያ፣ ዶላር ፍለጋ በጨረቃ ማለት ነው፡፡

 

ምንጭ (Reference)

(1) Ethiopia: Capital Flight Reaching Alarming Level/November 3, 2017

(2) Corruption in Ethiopia – Wikipedia

(3) #ASDailyScoop: Ethiopia’s military spending in 2022 increased by 88% to $1 billion – research/April 24,2023

(4) Ethiopia Plans to Import Oil From South Sudan | Umaizi/The Exchange Copyright 2019.

(5)   Ethiopia Begins Importing Fertilizer for 2023 Farming Season/ December 28, 2022

(6) Analysis: Farmers brace for worse as fertilizer prices rise, planting season approaches/MAY 4, 2022/Addiss Standered

(7) Nation imports USD48 million worth of edible oil every month/January 2, 2021

(8)Ethiopia recruits 500,000 women for domestic work in Saudi Arabia | Migration | Al Jazeera

(9)More than 2.3 million children out of school in northern Ethiopia despite peace agreement | Save the Children International

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share