ታዋቂው የታሪክ መምህርና አክቲቪስት ታዬ ቦጋለ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ታፈኑ

March 17, 2023
1 min read
taye 1 1 1

https://youtu.be/j4VfBoYWmpY

የታሪክ መምህርሩ ታዬ ቦጋለ ታፈኑ
የታሪክ መምህርና አክቲቪስት ታዬ ቦጋለ ልጃቸን ከትምህርት ቤት አውጥተው በታክሲ ወደ ቤታቸው እየሄዱ ባለበት ቦሌ ብራስ ዮድ አቢሲኒያ አካባቢ ሲደርሱ ከነልጃቸው ቦርሳና ምሳ እቃ እንደያዙ አፍሰው እንደወሰዷቸው ተሰምቷል።
መምህር ታዬን የወሰዷቸው ሲቪል የለበሱ የታጠቁ ግለሰቦች ናቸው ተብሏል። የታክሲ ሾፌራቸው ምንድነው? ብሎ ለመጠየቅ ሲሞክር መሳሪያ አውጥተው እንዳስፈራርቱ እና ልጃቸውን ይዞ ወደ ቤት እንደወሰደ ገልጿል።

3 Comments

  1. ትናንት ዘመነ ካሴ፤እስክንድር ነጋ፤አቶ ታዲዮስ ታንቱ፤መስከረም አበራ፤መአዛ መሃመድ ዛሬ ደግሞ ታየ ቦጋለን የመሳሰሉ ለማተባቸው የኖሩ ዜጎች ታሰሩ ከነሱ ጋር ኢትዮጵያም ታሰረች፡፡በመሰረቱ ህዝብም ለእርሱ ሲሉ ፍዳቸውን የሚበሉትን ካልታደገ መታገሉስ ምን ፋይዳ ሊኖረው ነው፡፡ ወንጀለኛ ወንጀለኛው ለሹመት ይታጫል ለሃገርና አንድነት አሳቢ ወደ እስር ይጋዛል ይገርማል ጠቅላላ ከብበውት የተቀመጡትና የተመቹት ነብስ ገዳዮች ብቻ ናቸው፡፡ ለማጣቀሻ ፕሬዚዳንቷን ጣል አድርጎበታል፡፡ ሃሜት እንዳይመስልብኝ ከወንጀለኞች መሃል አረጋዊ በርሄ፤ሺፈራው ሺጉጤ፤አገኘሁ ተሻገር፤ሬድዋን ሁሴን;ኦነጎች ወንጀለኛ ሁነው ንግዱን እንዲያሳልጡ የተመደቡ ኦሮሞዎች ጁዋር መሃመድን ይጨምራል፡፡ ይህ ጠ/ሚኒስቴር ይህች አገር ካልጠፋች እረፍት የሚያገኝ አይመስልም፡፡

  2. ሌንጮዎች፤ቀጀላ መርዳሳ፤ዲማ ነገዎ ተረስተው አይደለም ስንቱ ወንጀለኛ ይዘርዘር

  3. አይ ሃገር። ኢትዮጵያ አትፈርም እያሉ ማፍረስ። እንደመር እያሉ መቀነስና መፈረጅ፡ የብልጽግናው መንግስት ከወያኔ የሚለየው የቱ ላይ ነው? ያስራል፤ ይገርፋል፤ ይገላል፤ ያስገድላል። ሆን ተብሎ ቀጣይ ትውልድን ሁሉ ለማሸማቀቅ እንደ መ/ር ታዪና መስከረም ያሉትን ሰዎች ሲያፍኑ ከልጆቻቸው ፊት ነው፡፡ ይህ በእቅድና በፕላን የሚሰራ እንጂ አመቺ ጊዜ ነው ተብሎ የተመረጠ አይደለም። ባጭሩ የኦሮሞ ፓለቲከኞች አብደዋል። ለእኔ በጣም ግራ የሚገባኝ በሃገር ካለው ግርግርና ሌላውም የፓለቲካ ጫና ወጥተው በውጭ ሃገር የሚኖሩና የኖሩ ዛሬም ከፋፋይና እሳት ለኳሾች መሆናቸው ነው። በቅርቡ ጃዋር ያሰራጨውን ለተመለከተ ሃገሪቱ መዳኛ የሌላት በብሄር ፓለቲካ በወረፋ የምትዘረፍና የምትመራ ለመሆኗ ቁልጭ አርጎ ያሳያል። የፓለቲካ ሳይንስ ተማረ የተባለው ጃዋር እንዲህ አይነት ከመስመር የዘለለ ህሳቤ ለኦሮሞ ፓለቲከኞች ማካፈሉ የቱን ያህል መማር ከዘር ፓለቲካ የማላቀቅ አቅም እንደሌለው ያሳየናል። አንድ የገጠር የኦሮሞ ገበሬ ከኦሮሞ ብሄርተኞችና የፓለቲካ አዋቂዎች ነን ከሚሉት የተሻለ ስብዕናና ሃገራዊ እይታ አለው። ግን እኛ የምንልህን ተቀበል በሚባልበት የአስረሽ ምቺው ፓለቲካ በሰውኛ የሚያስቡትን ሃሳብ መቀበል ቀርቶ መኖራቸው ደስ አይለውም። ለዚህም ነው ኦነግ ሸኔ ኦሮሞዎችንም ለአማራ አብራችሁሃል እያለ የሚረሽነው።
    ይኸው እንሆ የሶሻል ሚዲያን ጥርቅም አርጎ የዘጋው የብልጽግናው መንግስት ልክ እንደ ወያኔ እኛ ከሌለን ሃገር ይፈርሳል ይለናል። በተግባሩና በሥራው ግን ሃገር አፍራሹ ራሱ የብልጽግና መንግስት ነው። በአድዋው በዓል በፈረሱ ላይ የተቀመጠውን ሰው በመገፍተር መሬት ላይ የፈጠፈጠው ፓሊስ፤ ካህኑን በጥፊ በጎሃ ጽዪን የደበደበው የኦሮሞ ፓሊስ፤ የጳጳሱን መቁጠሪያና ቆብ ሽንት ቤት ውስጥ የጨመረው ጽንፈኛ አክራሪ ኦሮሞ ቀን የማይመጣ መስሏችው ግፍን ለሌላው እያስጎነጩ እነርሱ ሲጨፍሩ ማየት መታወር እንጂ ብልህነት አይደለም። ጋዜጠኞችን፤ ጦማሪዎችን፤ የሶሻል ሚዲያ አንቂዎችን፤ ባጭሩ የብልጽግናውን መንግስት የሚቃወሙትን ሁሉ መደብደብ፤ ማሰር፤ ማሰቃየት፤ አልፎ ተርፎም መግደል ይህ ብልጽግናና አንድነትን ያመጣል ብሎ የሚያስብ መንግስት ጠበልና መድሃኒት በማያድነው በሽታ የተለከፈ መንግስት ብቻ ነው። ይህ መንግስት ከወያኔ የክፋት ጆኒያ አፈትልኮ ከወጣ ወዲህ የተፈጸመው በደልና መፈናቀል፤ ግድያና ዝርፊያ ወያኔ በ27 ዓመት ግዛቱ ካደረሰው የመከራ ዶፍ ጋር ይወዳደራል። የሚገርመው የመጣ የሄደው ጠላቴ ነው በማለት እየፈረጀ የሚፋለመው አማራውን ብቻ መሆኑ ነው። ይህ በወያኔ፤ በሻቢያና በኦሮሞ የፈጠራ ትረካ እንደ ጠላትነት ተቆጥሮ የሄደ የመጣው የሚረጋግጠው ወገናችን በእርግጥ እነዚህ የሙት ፓለቲከኞች እንደሚሉት ክፋት ፈጽሟል? ያለፈው ታሪካችን ከቅርቡና ከአሁኑ ጋር ሲነጣጠር አሁን እነዚህ ሃይሎች በዚህ ህዝብ ላይ ከሰሩትና ከሚሰሩት ግፍ ይልቃል? ግን የፈጠራ ትረካን በመረጃ ማቅረብ ስለማይችሉ ህባቸውን ለዘመናት የጋቱት የችግርህ ሁሉ መንስኤ አማራ ነው በማለት ነው። በዚህ የውሸት ትረካ ሰዎች በገደል ተጥለዋል፤ ቤታቸው ተዘግቶ በእሳት ከእንስሳት ጋር ጋይተዋል። በቀስት፤ በድላና በገጀራ ተቀጥቅጠው ተገለዋል። እየተገደሉም ነው። ይህ በዘመናት የማያባራ መከራን ለመመከት ራስን ማደራጀት፤ መታጠቅ፤ በህግና በደንብ እየኖሩ፤ አጥቂዎችን መመከት እስካልተቻለ ድረስ የፌደራል መንግስ ይድረስልኝ፤ የዓለም ህብረተሰብ ችግሬን ይስማልኝ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረደኝ፤ ፈጣሪ እንዲህና እንዲያ ያርግልኝ እያሉ ራስን ማታለል ከሞት አያድንም። በዘመናት መሃከል ያየነው ይህን እውነታ ነው። “እዚህ እሳት አለ እነዚያም ጭረዋል መኖርን ከጠሉ በሰላም በደስታ ቦግ ብሎ በመንደድ ይባላኝ በደስታ፡፡ ሁሌ ከምሳደድ ሁሌ ከምመታ ማመንታቴ ቀርቶ ልታጠቅ ጠበንጃ” እንዳለው ነው የጠላ ቤቱ አዝማሪ።
    ምድራችን የግፈኞች መፈንጫ ሆናለች። ግን ለግፍም ማብቂያ አለው። የፈነጩ ጸጉራቸውን በሃዘን ሲነጩ አይተናል። ዓለም መሽከርከርዋ ያለምክንያት አይደልም። አንድ ጋ ሲጨልም ሌላው ጋ በወረፋ ብርሃን ለመስጠት እንጂ። የዛሬው ወጋገን ነገ ይጨልማል። ለሁሉም ጊዜ አለውና!
    ይህ የኦሮሞ የፓለቲካ ጽንፈኞች ግፍ በጊዜ ካልታረመ ነገሮች ወደ ከፋ ደረጃ እንደሚሸጋገሩ አሁን ላይ የምናያቸው ነገሮች ይነግሩናል። የዛሬው ቱጃር ነገ ድሃ ይሆናል። ሰው በቀን አንዴ በልቶ ለመዋል ባልቻለበት ምድር ላይ “Hummer Car” በመንዳቴ ፓሊስ ጣቢያ ተወስጃለሁ የሚሉ የናጠጡ ሃብታሞች የሚርመሰመሱባት የግፍ ምድር ናት። ቁሳዊው ፍቅር አይናቸውን ያወራቸው ብዙዎች ናቸው። አላዪትም መሰል በቱርክ የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ በቁፋሮ የተገኘውን በጆኒያ የታሰረውን የወርቅና የዶላር ክምችት። ግን ምን ይሰራል ባለቤቶቹ የሉ። በፍርስራሹ ተቀብረዋል። እንዲህ ነው የምድራችን ነገር። እኖራለሁ እንጂ እሞታለሁ የለም። ባጭሩ ማስር፤ መደብደብ፤ ማስፈራራት፤ አንድን ክልል ከሌላው ክልል ጋር በስሌት ማጋጨት፤ ረሃብና እልቂትን ከህዝብና ከዓለም ፊት መደበቅ ይቁም። ጠ/ሚሩና በዙሪያቸው ያሉ የኦሮሞና የአማራ አመራሮች በጊዜ ነገርን ሰከን ብለው ይመልከቱ። የ 70 ዓመት አዛውንት አቶ ታዲዎስን እስር ቤት ጨምሮ ስለ ፍትህ ማውራት መሳቂያ መሆን ነው። ሰውን በማሰር፤ በመግደል፤ በመሰወርና በማፈናቀል ማንም ሃይል በስልጣን አይቆይም። ያማ ቢሆን ደርግና ወያኔ ዛሬም በመንበራቸው ላይ በሆኑ ነበር። የግፍ መቆሚያ አለው። ያኔ ቀናችሁ ሲያበቃ ልክ እንደ ሊቢያው ጋዳፊ በመንገድ ላይ እየተወገራችሁ ወደ እማንቀርበት ዓለም እንደምትጓዙ ከአሁን መተንበይ ይቻላል። ስራችሁ የድርቡሽ ነው። እይታችሁ ዘረኛ ነው። እንጠቅመዋለን የምትሉትን የኦሮሞ ህዝብም ልክ እንደ ወያኔ ከወገኑ ጋር አላትማችሁ ሞትን ሞት እየወለደው ሰው ሰላሙ ጠፍቶ እንዲኖር መንገድ እየዘረጋችሁ ነው። እንዴት ባለ ሂሳብ ነው ሰው ኦሮሞ ሆኖ ኦሮምኛ ባለመናገሩ ከሥራ የሚከለከለውና የሚደበደበው? በግድ እኔን ምስለ የሚሉት የጽንፈኞች ፓለቲካ። ባይገባህ ነው እንጂ የሃገራችን ቋንቋ ወንዝ አያሻግሩም። በጥብጠህ ጠጣው ያንተን ቋንቋ። ግን የፓለቲካው መላሸቅ ከአፍንጫ የማይርቅ አስተሳሰብን በማፍለቁ በሰው ስቃይ የሚስቁ እብዶች በምድሪቱ ላይ ተበትነዋል። ከእነክፋታችሁ ፈጣሪ ሰሃራ በረሃ ወስዶ ይጣላችሁ። በሰው ሰቆቃ የምትስቁ የዘር ፓለቲከኞ ከምድሪቱ ክሰሙ! በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

413wH4OFd8L. SY498 BO1204203200 1 1
Previous Story

ዐማራ እንደ ማህበረሰብ እንዲጠፋ የተወሰነበትና በመንግስት መዋቅር የሚታገዝ የዘር ጭፍጨፋ እየተደረገበት ያለ ህዝብ ነው

59ba71f0 c575 11ed 95f8 0154daa64c44 1 1
Next Story

አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ በህወሓት ተመረጡ

Latest from Blog

አትዮጵያ ያን ዕለት

ግም ሞት 20’ 1983 .ዓ.ም. ለህወሀት /ኢህአዴግ ልደት ለኢትዮጵያ እና ለብዙዉ ኢትዮጵያዉያን የዉድቀት ፣ጥልመት እና ሞት ዕለት መሆኑን ያ ለሁለት አሰርተ ዓመታት ከፍተኛ ዕልቂት እና ደም መፋሰስ የነበረበት ጦርነት አዲስ አበባ በደም

አቢይ አህመድ ታላቁን አሜሪካንና የተቀሩትን የምዕራብ ካፒታሊስት አገሮችን ማታለል ይችላል ወይ? የአሜሪካ “ብሄራዊ ጥቅምስ ኢትዮጵያ ውስጥ“ እንዴት ይጠበቃል? የአሜሪካ እሴቶችስ(Values) ምንድን ናቸው?

ለመሳይ መኮንና ለተጋባዡ የቀድሞ “ከፍተኛ  ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት” በአሁኑ ወቅት በአሜሪካን የስቴት ዴፓርትሜንት ውስጥ ተቀጥሮ ለሚስራው ኢትዮጵያዊ ሰው የተሰጠ ምላሽ!   ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ግንቦት 19፣ 2016(ግንቦት 27፣ 2024) መሳይ መኮንን በአ.አ በ17.05.2024 ዓ.ም አንድ እሱ  የቀድሞው “ከፍተኛ የኢትዮጵያ

ጎንደር ሞርታሩን እስከ ጄነራሉ ተማረከ | ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | ብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን

ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | “ፋኖ ከተማውን ቢቆ-ጣ-ጠር ይሻላል” ከንቲባው |“አብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን” ኮ/ሉ |“በድ-ሮን እንመ-ታችኋለን እጅ እንዳትሰጡ” ጄ/ሉ
Go toTop