March 14, 2023
1 min read

“ከአንዳንድ ክልሎች ወደ አዲስ አበባ የሚደረገው ከፍተኛ ፍልሰት መንግስትን በመጣል በኃይል ስልጣን ለመቆጣጠር ያለመ ነው”- ከንቲባ አዳነች አበቤ

Adanch ababe 1 1

Adanch ababe 1 1

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “መንግስትን ለመጣል ከአንዳንድ ክልሎች ከፍተኛ ፍልሰት” እየተደረገ መሆኑን አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይህንን ያስታወቀው፤ ዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 5፤ 2015 በተጀመረው የከተማዋ ምክር ቤት ጉባኤ ላይ በቀረበ ሪፖርት ነው።

ወጣቶችን በማነሳሳት “ወደ ጥፋት ለመግባት” እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን በመጠቆም

አዲስ አበባን “የሁከት አውድማ” ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው ሲሉ አዳነች አበቤ ገልፀዋል።

ከንቲባዋ “ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ህዝብ የመረጠውን ህጋዊ መንግስት በመጣል በኃይል ስልጣን ለመቆጣጠር በማለም፤ ከአንዳንድ ክልሎች ወደ አዲስ አበባ የሚደረገው ከፍተኛ ፍልሰት” የጸጥታ ስጋት መሆኑን ለምክር ቤት አባላቱ አስታውቀዋል።

በከተማዋ ውስጥ የሚታየው “ጽንፈኝነት፣ ጥላቻ እና ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት” የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች፤ የከተማ አስተዳደሩን አገልግሎት አሰጣጥ ተደራሽ እንዳይሆን ማድረጋቸውንም አዳነች በሪፖርታቸው ላይ ገልጸዋል።

ምንጭ ፦ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

Leave a Reply

Your email address will not be published.

180766
Previous Story

የኦሮሚያ ክልል የአባይን ግድብ የመጠቅለል እቅድ ፡ በኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል እና በቤኒሻንጉል ክልል ልዩ ኃይል መካከል ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ነው

abn
Next Story

ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop