March 14, 2023
2 mins read

የኦሮሚያ ክልል የአባይን ግድብ የመጠቅለል እቅድ ፡ በኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል እና በቤኒሻንጉል ክልል ልዩ ኃይል መካከል ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ነው

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ታላቁ የህዳሴ ግድብን ወደ ኦሮሚያ ለመጠቅለል ጫፍ ደርሷል። የግድቡ ውሃ የሚተኛበት መሬት የማስፋፊያ ስራ እየተሰራ ነው።
ለጉባ አዋሳኝ በሆነችው ሸርቆሌ ወረዳ ልዩ ስሙ አውል ቤጎ በተባለ አከባቢ በደን ምንጣሮ ከተሰማሩት 3000 በላይ ወጣቶች መካከል ሙሉ በሙሉ በሚያስብል ደረጃ የኦሮሞ ተወላጆች ናቸው።(የአማራ ተወላጆች ስራውን ለቀው እንዲወጡ ተደርገዋል)። በስራው የተሰማሩት የኦሮሞ ተወላጆቹ ወታደራዊ ስልጠና የተሰጣቸው ናቸው ተብሏል።
በአቅራቢያቸው ከሚገኙ የኦነግ ታጣቂዎች ጋር ሰፊ ግንኙነት እንዳላቸውም ተጠቁሟል። በተጨማሪም ለጉባ ወረዳ በቅርብ ርቀት በሚገኘው ልዩ ስሙ ሲርባባይ በተባለ አከባቢ በኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል እና በቤኒሻንጉል ክልል ልዩ ኃይል መካከል ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ነው። ከዚህ አልፎ ግድቡ በሚገኝበት ጉባ ወረዳ እና በምዕራብ ወለጋ ዞን መካከል የሚገኘው የካማሺ ዞኑ ኦዳ ቡልዱ ጉሉ ወረዳ ነዋሪዎች አከባቢያችሁ ወደ ኦሮሚያ ክልል ስለተካለለ በአስቸኳይ ለቃችሁ ውጡ የሚል ትዕዛዝ ከኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል እንደተሰጣቸውም ተሰምቷል። የአማራ ድምፅ ሚድያ አንድ የቤኒሻንጉል ክልል ከፍተኛ አመራርን ጨምሮ ነዋሪዎቹን እንዲሁም በደን ምንጣሮው የተሰማሩ ወጣቶችን አነጋግሯል። ዝርዝሩን ይከታተሉ።
ምንጭ የአማራ ድምፅ

https://youtu.be/R9xEyI8Kut4

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop