February 28, 2023
6 mins read

የዓድዋ  ድል ክብረ በዓል የነፃነት እና የአንድነት ዓርማ ነዉ

default 1በኢጣሊያ የወራሪዎች ቅዠት በዕብሪት እና በከንቱ ምኞት በምስራቅ አፍሪካ የታሪክ ፣ የስነ ፅሁፍ፣ የባህል ፣ የማንነት ባህል ፣ዕምነት እና ወግ ያላት የሰዉ ልጆች ምንጭ የሆነች ታላቅ እና የአምስት ሽ ዘመናት  ስር መንግስት ያላት አገር መኖር ዕንቅልፍ የነሳዉ ለወረራ በሰሜን ሲገባ አደዋ (አምባላጌ) ላይ የሚጠብቀዉ የዉስጥ እና የዉጭ ቅጥረኛ እና ምንደኛ ባንዳ እንደነበር ማሳቡ ለሽንፈት ዳርጎታል፡፡

ይህም ጠላት ከነበረዉ ዝቅተኛ ግምት  በላይ ዕምየ ሚኒሊክ እና የጊዜዉ ቅድመ አያቶቻችን በአገር እና በርስት የማይደራደሩ መሆናቸዉን ካለመረዳት ምሱን ሰጥተዉ ወራሪዉ ጠላት የሰበሰበዉን በትኖ በበቃኝ  የተረፈዉ በዕግሬ አዉጭኝ በመጣበት ተመልሷል፡፡

ዕምየ ሚኒሊሊክ የጥበብ ፀጋ የተላበሱ ፣ ለሠዉ ልጆች ነፃነት በጨለማ ዘመን የደረሱ ፣ አርቆ አስተዋይ ለህዝባቸዉ ቀርቶ ለመላዉ የሰዉ ልጂ የነፃነት እና የመንፈስ አባት መሆናቸዉን ከዚያ አስከዛሬ አሳይተዉናል፡፡

ደግነት ፈጥኖ ይረሳል እንዲሉ የጀግንነት እና የደግነት ማማ ዕምየ ሚኒሊክ ታላቅ አገር አስረክበዉን ዛሬ ስራቸዉን አይደለም ስማቸዉን መስማት ይጓጉጠናል ፡፡

ዕዉነት ነዉ ክፉ ቀን ያወጣ ክፉ ቀን ይመስላል ነዉ ፡፡  ስለ ዕምየም ሆነ ስላለፉት የኢትዮጵያ ታላላቆች ለማለት ችሎታዉም ዕዉቀቱም የለኝም ግን አንድ ማለት ዕወዳለሁ ፡፡

ይኸዉም መቸ ነዉ የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያዉያን  ብሎም ለአፍሪካ እና ለመላዉ ጥቁር ሠዉ ልጆች የነፃነት ቀንዲሎች በዕዉነት የሚዘከሩት ፡፡

የፖለቲካ ስርዓት የቡድን ዓመለካከት እንጂ የኢትዮጵያን ህዝብ እና ታሪክ አይለዉጥም ፤ አይተካም ነግር ግን በዓደዋ በዓል ማስታወቂያዎች ላይ የዕምየ ሚኒሊክ ምስል በኢህአዴግ ዓርማ መወከሉ ጥያቄ ሆኖብኛል ፡፡

ዕዉን ኢህአዴግ በ1888 ነበር ወይስ ኢህአዴግ በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ላይ ያለዉን አቋም ኢትዮጵያዉያን አያዉቁም ፡፡

ዕዉነት ኢህአዴግ ስለ አገር እና ህዝብ ቢገደዉ የኢትዮጵያን የቆየ ታላቅነት እና የረጂም ዘመናት ታሪክ በአንድ ሠዉ ዕድሜ  ይቀነብብ ነበር ፡፡

ኢትዮጵያ ባንዲራዋ አረንጓዴ ፣ ቢጫ ፤ቀይ ሆኖ ሳለ በዕምነት ተቋማት ሳይቀር የድርጂት ዓርማ ካላየ የሚጨንቀዉ በአዳዋ የድል ክብረ በዓል የድርጂቱን አርማ እዩልኝ ማለት ዕዉነትም በ18ኛዉ ክ/ዘመን መጨረሻ ከዉጭ አፍራሽ ጠላቶች ጋር መፈጠሩን ለማሳየት ይሆን ፡፡

መፈጠሩን ካመነ በጊዜዉ በዓደዋ ጦርነት ጀግኖች ይዘዉት የነበረዉን የኢትዮጵያ ባንዲራ ዛሬ ላይ በማስታወቂያ ላይ ለማሳየት መስጋት አሁንም ትልቅ ታሪካዊ ስህተት ነዉ እና የኢትዮጵያ ባንዲራ ትዉልድ የሞተለት፤ ትዉልድ የሚኖርበት አረንጓዴ ፣ቢጫ ፣ቀይ ነዉ እና ዕምየም ኢትዮጵያዊ ፤አፍሪካዊ የነፃነት አባት ፤ የጀግንነት እና የአንድነት ምሳሌ ናቸዉ እና ቢቻልስ በአፍሪካ ህብረት እና በሌሎች አለም አቀፍ ተቋማት አደባባይ ስማቸዉ ፣መስላቸዉ እና የኢትዮጵያ ባንዲራ  ከፍ ሊል ይገባል ፡፡

የትናነቷ አገር አሜሪካ የነፃነት አባት የምትለዉን ጆርጂ ዋሽንግተን  የብሄራዊ ገንዘቧ  መመሰል ፤ መዲናዋ መሰየም ለአፍሪካ እና ለኢትዮጵያ ሚኒሊክ  ቢመለክ ምኑ ነዉ ስህተቱ የት ላይ ነዉ ፡፡

በመጨረሻም ዕምየ ሚኒሊክ የጥቁር ሠዉ ልጆች የነፃነት እና የሉዓላዊነት መንፈስ እንጂ እርሳቸዉም ሆኑ ኢትዮጵያ ከየትኛዉም ተቋም ወይም የፖለቲካ ድርጂት በፊት እና በላይ የነበሩ መሆናቸዉ ታዉቆ ኢትዮጵያ እና ንጉስ ሚኒሊክ  ምልክታቸዉ  የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪካዊ ባንዲራ ሆኖ ዕድሜአቸዉ ፭ ሽ ዘመናት የተሸገረ መሆኑን መርሳት ክህደት እንዳይሆንብን ሊታሰብ ይገባል ፡፡

 

አንድነት ኃይል ነዉ

 

Allen Amber

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop