February 24, 2023
3 mins read

 ለቦረና ወገናችን መከታ እንሁን

ቀደም ባለው ጊዜ በስራ ምክንያት ቡርጂ አካባቢ አንድ አመት ቆይቻለሁ። ጉጂዎችንንና ቦረናዎችን በቅርብ አውቄ ጓደኝነት መሰርቼ ኖሪያለሁ። እኔም እንደነሱ ወተት ወዳድ ነበርኩና ቅዳሜ ቅዳሜ ይዘዋት የሚመጧትን የቅል ወተት ለእኔ ለማቀበል አይኖቻቸው ሲንከራተቱ  የማያቸው ጉጂዎችና ቦረናዎች ነገር ዘወትር ከህሊናዬ አይጠፋም። እኔ ኦሮምኛ አልችልም። እነሱ አማርኛ አይችሉም። ነገር ግን የሰው ልጅ ፍቅር ካለው የሚግባባበት ሌላ የሆነ ረቂቅ ነገር ያለው ፍጡር ነወ።
331397943 1442832959818414 3141262873400492363 n 1 1 1ቦረናና ጉጂ ህይወታቸው ከብቶች ናቸው። እነዚህ ህዝቦች ለዚህ ምድር ኑሯቸው የሚሿት ትንሽ በቆሎና ወተት ነው። ወተት ምግባቸው ብቻ ሳይሆን ጌጣቸውም ነው።  ስለዚህ ይህንን ህዝብ ረሀብ ላይ እንዳይወድቅ የድርቅ ምልክት ሲታይ የከብት መኖ እርዳታ ነው የሚያሰፈልገው። ቦረና ላሙ ከሞተች የሱም ህይወት አይቀጥልም። ለዚህ ነበር ቀደም ባሉት ወራት አደጋ መከላከል ላይ የምትሰሩ ወገኖች ለዚህ ወገን መኖ አግዙት እያልን ስንጮህ የነበረው። መኖ ከምድረ ኢትዮጵያ አልጠፋም ነበር። ሌላው ቀርቶ ብዙ ስንዴ አምርተናል የሚሉ ወገኖች ለዚህ ህዝብ ገለባውን ቢያቀብሉት ከየቤቱ ሁለት ላም ቢተርፍ ያ ህዝብ ይተርፋል። አሁን ነገሮች ከፍተው ወገናችን ተርቧል። አሁን አርብቶ አደሩ ረሀብ ላይ ነው። መወቃቀሱ ለታሪክ ይቀመጥና አሰቸኳይ እርዳታ እናድርግ።

    332459196 732870318391342 1532925833538991309 n 2 1 1  እርዳታውን እንዴት እንላክ?
በግለሰብና በቡድን መሞከሩ ውጤታማ አይሆንም። የሚሻለው ከዚህ በፊት በእርዳታ ስራ ልምድና ኔት ወርክ ያለውን ግሎባል አሊያንስን እንደግፍ። ዛሬ ይህንን ደብዳቤ ስጽፍ ወደ ግሎባል አሊያንስ መሪ ደውዬ ነበር። በዚህ ጉዳይ ላይ እንደመከሩበትና ጎፈንድ ሊከፍቱ እንደ ሆነ ገልጸውልኛል። ሰለዚህ ሁላችንም በዚያ በኩል እናግዝ። ሌሎች አካባቢዎችም በተለይ ደብረ ብርሀን ከፍተኛ ተፈናቃይ አለና በዚያም በኩል ለወገን እንድረስ። እግዚአብሔር ሀገራችንን ይባርክ ይጠብቅ። አሜን።
ገለታው ዘለቀ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

የኦህዴድ መራሹ ብልፅግና  መንግስት  በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል በንጹሀን  ዜጎች ላይ እየወሰዳቸው ያሉ የነፃ እርምጃ  ግድያዎች  መንግስት ያሰበውን የፖለቲካ ግብ ያሳካለታል  ወይ ? በኔ አመለካከት እነዚህ የንፁሃን ዜጎች  የጅምላ ግድያዎች  በሁለት በኩል እንደተሳለ ቢላዎ (double edge sword) ናቸው:: ፩- መንግስት እያሰላው

 የኦህዴድ መራሹ ጅምላ ግድያዎች ስሌት (ሸንቁጥ- ከምዕራብ ካናዳ)

January 24, 2025
እነዶ/ር ደብረፅዮን እና በጠ/ሚ ዐብይ አህመድ በተሾሙት የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት መሪዎች እነጌታቸው ረዳ መካከል የነበረው አለመግባባት ተካርሮ ሰራዊቱን ወደውግንና አስገብቷል። የትግራይ ሐይል አዛዦች ትላንት ባወጡት መግለጫ ውግንናቸው ከእነዶ/ር ደብረፅዮን ጋር መኾኑን አስታውቀዋል።

በትግራይ የተፈጠረው ምንድነው?

January 23, 2025
የድሮ መሪዎች ያላደረጉትን ምሁር ጳጳሳቱ ያላስተዋሉትን ከፈረሰች ጎጆ ከባልቴት ቤት ገብቶ ክብሩን ዝቅ አድርጎ ውሀዋን ጠጥቶ ምግቧንም ተጋርቶ ያላለቀሰ ሰው ያንን ትይንት አይቶ ማን ይኖራል ከቶ? በዉሸት ፈገግታ ፊቱን አስመስሎ ፀሀይ የበራበት

ሰው በሰውነቱ – ከ ይቆየኝ ስሜ

Go toTop