February 1, 2023
2 mins read

አባታችን አቡን ማትያስና የጭራቅ አሕመድ ሲሳይ አጌና ዘዴ

matias

ጭራቅ አሕመድ ኢሳትን ለመበታተን ሲነሳ፣ በኢሳት ውስጥ በቀላሉ ሊደለል የሚችል ቁልፍ ሰው ነው ብሎ ያሰበውን ሲሳይ አጌናን በስም ጠርቶ አመሰገነው፡፡  ሲሳይ አጌናም ልክ ጭራቅ አሕመድ እንዳሰበው ሆነና፣ ከሁሉም ባልደረቦቸ እኔ ብቻ ተለይቸ፣ በስም ተጠርቸ በጠቅላይ ሚኒስትር ተሞገስኩ ብሎ በትዕቢት ተወጣጥሮ ዝሆን አከለ፡፡  ጭራቅ አሕመድም ተወጣጥሮ በተነፋው በሲሳይ አጌና ሆድ ውስጥ ገብቶ ሲሳይን በማፈንዳት ኢሳትን በታተነው፡፡

አባታችን አቡነ ማትያስ ሆይ፣ ትናንት በነ ዳንኤል ክብረት አማካኝነት ከፍ ዝቅ እያደረገ ሲሰድብወና ሲያሰድብወ የነበረው ባለጌው ጭራቅ አሕመድ፣ ዛሬ እርስወን ለይቶ ያመሰገነወ፣ በርስወ ውስጥ ገብቶ ተዋሕዶን ለመበታትን ሲል ብቻ መሆኑን ይጠፋወታል ብየ ስለማላስብና፣ እንደ ሲሳይ አጌና በቀላሉ ተደላይ ነወት ብየ ስለማልገምት፣ እኛም አውቀናል ጉድጓድ ምሰናል ይበሉትና ቁርጡን ያሳውቁት፡፡  የጭራቅ አሕመድ መውደቂያው ስለቀረበ የሚያልፍ ዝናብ አይምታወ፡፡

 

ጭራቅ አሕመድ ዐሊ የኦነጉ ኦቦ

አፉና ምግባሩ ሐራምባና ቆቦ፡፡

ባንደበቱ መስሎ የኢትዮጵያ ሙሴ

በምግባሩ ሆነ የኦነግ ራምሴ፡፡

በመውረስ ያገኘው ከወያኔ አባቱ

መዋሸት ማጭበርበር ነውና ፍጥረቱ፣

አንዴ ቢያታልለን የሱ ነው ኀፍረቱ

ሁለቴ ቢደግም የኛ ነው ጥፋቱ፡፡

 

መስፍን አረጋ

[email protected]

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop