August 15, 2022
17 mins read

አማራ፦ ህልውናህ ያለው በአንተው መዳፍ ውስጥ ነው (እውነቱ ቢሆን)

minsterአማራ አሁን እየደረሰበት ያለውን መከራ፣ ጭፍጨፋ ፣መንገላታታና ስደት እርሱ ራሱ “”እምቢ”‘ ብሎ “”በቃኝ”” ብሎ ማስቆም ካልቻለ ህገ መንግስቱ፣ አብይ አህመድ ፣ደመቀ መኮንን ወይንም የፌደራል ፖሊስና፣የደህንነቱ ተመስገን ጥሩነህ ወይንም ይልቃል ከፋለ ወዘተ አያድኑትም፡፡ ሲጀመር እነዚህ ሀይሎች ይህ ሁሉ መከራ በአማራ ላይ እንዲፈጸም የየራሳቸውን ከፍተኛ ሚና የተጫወቱ ናቸው፡፡ አማራው ራሱ ቆርጦ ችግሩን ካልተጋፈጠውና ራሱ ካላስወገደው ሌላ ማንም አይደርስለትም፡፡ አያስወግድለትም፡፡

እንዴት ነው አማራ እምቢኝ ብሎ ፣በቃኝ ብሎ መከራውን ሊያስቆም የሚችለው የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ መልሱ ቀላል ነው፡፤ መከራውና ጭፍጨፋው መንገላታቱና ያለልክ መገፋቱ እንዴትና በማን እንደተፈጸመበት አማራው ጠንቅቆ ያውቀዋል፡; ይህንን ሀቅ ጠንቅቆ ማወቁ ደግሞ የትግሉ ጉዞ ግማሽ መንገድ ተሄደ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ አማራን ማን እያስወጋውና እያስገደለው እንደሆነ መልሱ ግልጽ ነው፡፡ እርሱም ዱሮ የወያኔ አሽከር የነበረው ብአደን ስሙን ወደ አዴፓነት የቀየረው( አዴፓ) እንደገናም አሁን በጭራቁ በአብይ አህመድ የኦሮሙማ ጊዜ ደግሞ የአማራ ብልጽግና ተብሎ የሚጠራው የከርሳሞችና ወራዶች የአማራ ሹመኞች ስብስብ ነው፡፡

ችግሩ የሚፈታበት መንገድ አንድና አንድ ብቻ ነው፡፡ ይህም እነዚህን የአማራ ሹመኛ ተብየወቹን (ትርፍ አንጀቶች) በክልሉ ውስጥ ከታችኛው አርከን ጀምሮ እስከ ክልል ሹመኞችና ሀላፊወች/ተመራጮች ተብየወች ድረስ ያሉትን በሙሉ እንደዚሁም በፌደራልና፣ በክልሉ ምክር ቤትና በብሄራዊ ሸንጎ ደረጃ ጭምር በተመራጭነት በየደደረጃው ያሉትን በሙሉ በየተግባራቸው፣ በየስራቸውና በፈጸሙት አማራን የማሳደድና የማስገደል ሚና ልክ መዝኖ መክሮና ዘክሮ መለየት ከሁሉም ቅድሚያ የሚሰጠው አጣዳፊ ጉዳይ ነው፡፡ በእያንዳንዱ መንደር፣ ቀበሌ ወረዳና የአማራ ዞኖች ያለው ህዝብ የትኛው ተመራጭና ተሿሚ ተቡዬ መቼና እንዴት በህዝቡ፣ በፋኖና በአማራ የልማት ህልሞች ላይ ምን እንደደረገ ህዝቡ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የማይስተካከሉትንና ወደ ህዝቡ የነጻነት እንቅስቃሴ የማይቀላቀሉትን እየለዩና እያበጠሩ ተገቢውንና የማያድግም ትምህርት እየሰጡ መሸኘት ብቸኛው መፍትሄ ነው፡፡

በጣት ከሚቆጠሩት ከእነዚህ ተመራጮች በስተቀር 95% በላይ የሆኑት ተመራጮችና ተሿሚወች የአማራ ህዝብ በነጻ አንደበቱ የመረጣቸውና የህዝቡ የራሱ የሆኑ፣ ለራሱ ለህዝቡ የሚሰሩ ተመራጮች ሳይሆኑ ጭራቁ አብይ አህመድ ያስመለመላቸውና ያስመረጣቸው ሆዳሞች፣ በቁማቸው የበከቱና የበሰበሱ አጋሰሶች ናቸው፡፤ እነዚህ አጋሰሶች ለህዝብም ለራሳቸውም ለቤተሰቦቻቸውም አይጠቅሙም፡፡ ህሊና ቢስ ስለሆኑ የአብይ አህመድ መጋዣወች ናቸው፡፡ እነዚህ መጋዣወች ናቸው አማራን አንገቱን እንዲደፋ፣ እ””ንዲጨፈጨፍና እንዲሰደድ ያስደረጉትና አሁንም እያስደረጉት ያሉት፡፤ መጋዣወቹን ጭራቁ አብይ አህመድ “”ፋኖን ትጥቁን አስፈቱ”” ብሎ ሲያዛቸው የአማራና የኢትዮጵያ አለኝታ የሆነውንና በቅርቡ ከወያኔ ወራሪ ጦር ጋር ፊት ለፊት ሲዋጋ ደሙን ለአማራ ህዝብ ያፈሰሰውን ፋኖን ትጥቁን ለማስፈታትና ሰብስቦ ለማሰር ለምን ብለው አልጠየቁም፡፡ ብርቅየውቻችንንና አለንታወቻችንን ፋኖወችን አሳድዶ በጅምላ ለማሰርና ህዝቡን አንገቱን ለማስደፋት ወደሃኋላም አላሉም፡፤ ሌላው ሁሉ ይቅርና ብዙ አማራወች በየቀኑ በወለጋ ሲታረዱ ቢያንስ በክልሉ የሀዘን ቀን አውጆ የታረዱትን አማራወች አላሰቧቸውም፡፤ ሁለት ሶስት የሚሆኑ ሀቀኛወች ከመካከላቸው ቢገኙ የእነዚሁኑ ድምጽ ለማፈን ወደኋላ አላሉም፡፡ አፈኗቸው፡፡ ስርጭቱንም ከህዝብ ደበቁት፡፡

በፌደራል ምክር ቤቱ ውስጥም ቢሆን ሁለት ተወካዮች ያነሱትን በአማራነታቸው እየተመረጡ የተጨፈጨፉትን ዜጎች እናስባቸው የሚለውን ጥያቄ ፓርላማው በጉዳዩ ላይ ለመወሰን ምን ያህል እንደተጨቃጨቀበትና መጨረሻም በፓርላማው አፈ ጉባኤ ተብየው ታፍኖ እንዴት ውድቅ እንደተደረገ ለታዘበ ሁሉ ድርጊቱ ያማል፡፡ እጅግ በጣም ያማል፡፡ ይህንን ያህል ነው አማራው እንዲዋረድ አብይ አህመድ አባክሮ እየሰራ ያለው፡፡

ክሌላ አንጻር ደግሞ አሁን ያለውን የኦሮሙማ ፖለቲካ በትንሹ ጨለፍ አድርገን እንመልከተው፡፡ ጀብደኛውና ወንጀለኛው ጃዋር መሀመድ በውጭ አገራት እየዞረ ለማስመሰል ያህል “ወደመሀል ፖለቲክ መምጣት አለብን” እያለ የቻለውን ያህል ሊያወናብድ ሞክሯል፡፡ በውስጥም ፖለቲካም እንዲሁ አብይ አህመድ አንዴ የምክክር መድረክ ሌላ ጊዜ ደግሞ የድርድር መድረክ እያለ ሰፊውን የኢትዮጵያ ህዝብ እያዘናጋ ኦሮሙማን በየዘርፉና በየአቅጣጫው እያሰፋና እያስፋፋ ይገኛል፡፡ ሰውየው በሁሉም መስክ ኢትዮጵያዊነትን ነቅሎ ኦሮማዊነትን እየተከለ ይውላል፣ ያድራል፡፤ ዘረፋውና ገፈፋው ጭፈጨፋውና እልቂቱ በብልጽግና ቋትና ብርድ ልብስ ውስጥ ተደምሮ ! ተደምሮ ! ተደምሮ ! አብይ አህመድን የልብ ልብ ሰጥቶታል፡፡ ከወያኔ ጋርም በድብቅ በመመሳጠር የ46 ሚሊዮኑን የአማራ ህዝብ የደም መሬት የሆኑትን ታሪካዊ ርስቶቹን ወልቃይትንና ራያን ለወያኔ አሳልፎ ለመስጠት በድብቅ እየተደራደረ ይገኛል ፡፡

ወደተነሳሁበት የአማራ አንድ ሆኖና ጠንክሮ ለጭራቁ አብይ አህመድ አልገዛም ብሎ ራሱን ነጻ ወደማውጣቱ አሥፈላጊነት ርእሴ ልመለስ፡፡ ሌላ፣ ሌላውን ሁሉ ተወት፡፡ በወለጋ በቅርቡ አማራ በግፍ በታረደበት እለት የክልሉ ፕሬዝዳንት ተብየው ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ራሱ በቴሌቪዥን ቀርቦ የተናገረው እንደ አማራም እንደ ሰውም እጅግ ይሰቀጥጣል፡፡ያኔ ዶ/ር ይልቃል የተናገረው እንደዚህ ብሎ ነበር፡፡ “”በወለጋ የተጨፈጨፉት ሰወች ኢትዮጵያዊያን ናቸው”’ ነው ያለው፡ የተጨፈጨፉት አማራወች ናቸው የተጨፈጨፉበትም ምክንያት በአማራነታቸው ተለይተው አማራ ስለሆኑ ነው አላለም፡፡ ቪዲዮው አለ፡፡ ታዲያ ይህ ሰው ለአማራ ምኑ ነው???

መፍትሄው በቅድሚያ ህዝቡ ተነጋግሮና ተመካክሮ በመላው አማራ ክልል ውስጥ በየነጥብ ጣቢያው ያሉትን ሆዳሞች እንደየበደላቸው መጠን በሙሉ እየመነጠረ አስፈላጊውን እርምጃ ካልወሰደና በክልል ደረጃም ጠራርጎ ካላስወገዳቸው ክልሉም ስላም አይሆንም፡፡ ህዝቡም ሰላሙን አያገኝም፡፡ ይህ የተጋነነ ወይንም በምኞት የተሰላ ሀሳብ ሳይሆን አማራ እንደ ህዝብ መዳን ካለበት ምንም ነገር ከማድረጉ በፊት እነዚህን አረሞች ነቃቅሎ መጣል እንዳለበት ወቅቱ ግድ ማለቱን ለማስገንዘብ ነው፡፡

አማራው አንድ ነገርን አምኖ መቀበል አለበት፡፡ ታላቁን የአማራ ህዝብ ይህንን ያህል አዋርደው መሬት ላይ ዘጭ ያደረጉትና ለዚህ አሳፋሪ የበታችነት ያበቁት የራሱ ሆዳሞች እንጅ የወያኔም ህነ የኦነግ ጥንካሬ እንዳልሆነ ፍጹም መዘንጋት ይችላል፡፡ ህዝቡ ከፋኖ ጎን በመሰለፍ የራሱን አደረጃጀት ፈጥሮ ክልሉን ከኦሮሙማ ጅቦች መከላከል አለበት፡፡ አለበለዚያ አማራው በኦነግም ሆነ በወያኔ መጠቃቱ አይቆምለትም፡፤ በራሱ ሀቀኛ ልጆች መመራት ከጀመረ ግን የጭራቁ አብይ አህመድ ታዛዥ መሆኑ ይቀራል፡፤ ከዚያ በኋላ ወያኔም ሆነ ኦነግ አማራውን ሊደፍሩት ፈጽሞ አይችሉም፡፡

አማራው ቀድሞ ይህንን ካደረገ የኦሮሙማ ኬላ ጠባቂወች የአማራውን ተጓዥ እያስቆሙ የአማራ መታወቂያ ስለያዝክ ወይንም አማራ ስለሆንክና የአማራ ታርጋ ስላለህ ወደ አዲስ አበባ መግባት አትችልም ሊሉትና በጉቦ ለማሳለፍም እየተደራደሩ ገንዘቡን ሊዘርፉት አይደፍሩም፡፡ አዲስ አበባን እንደፈለጉ ገነጣጥለው በአዲስ ካርታ ወደ ኦሮሚያ ሊያጠቃልሏት ቀርቶ አሁን በማድረግ ላይ እንዳሉት ጥቅሟንና የኗሪወቿን መብት መጋፋትን ሊያስቡት አይችሉም፡፡

ህዝቤ ቆጥቦ ያሰራውን ኮንዶሚኒየም ነጥቀው ለመውሰድ አይከጅሉም፡፡ ምክንያቱም ያኔ አማራው የራሱን ሆዳሞች ቀድሞ ያስወገደና በአንዲነት የቆመ ስለሆነ አማራው ታሪካዊ ርስቱን አዲስ አበባን ጨምሮ በመላዋ እትዮጵያ ውስጥ ማንነቱንም ጥቅሙንም የማስከበር አቅምና ጉልበት አንዲነትና ሀይል ይኖረዋልና፡፤ ይህም የሚሆንበት ዋና ምስጢር ያኔ እንደ አሁኑ አብይ አህመድ በምርኩዝነትና በምስለኔነት የሚጠቀምባቸው የአማራ ሆዳሞች በክልሉ ውስጥ አይኖሩምና ነው፡፡ተጠራርገው ተወግደዋልና ነው፡፡ህዝቡ በአንድ መንፈስ ከፋኖ ጎን በአማራነቱ ኮርቶና አንድ ሆኖ ቆሟልና ነው፡፡ ያኔ አብይና 31 ዙር የሰለጠነው የኦሮሞ ሰራዊት አማራ ክልል ውስጥ ገብቶ እንደፈለገ የሚፏልልበት ሁኔታ ፈጽሞ አይኖርምና ነው፡፡ ለዚህ ሁሉ ስኬት አሁኑኑ ዛሬዉኑ አማራው ሆዳሞቹን ከውስጡ አጥርቶ ማስወገድ መቻል አለበት፡፡

ያኔ አማራው ጠንክሮ በራሱ ተማምኖ ይቆማል፡፡ ማንነቱን ያስከብራል፡፡ አሁን ባለው የአብይ አህመድ አገዛዝ በጋራ በእኩልነት ተሣስቦ መኖር የማይቻል ስለሆነ የአማራው ህዝብ በያለበት ሆድሞቹን አማራወች አራግፎ በማስወገድ አንዲነቱን አጠናክሮ ማንነቱን በቆፍጣና ተጋድሎው ያስከብራል፡፡ ያኔ የአብይ አህመድም ተረኝነትና ዘረኝነት ያልቅለታል፡፡ ያከትማል፡፡ ያኔ አማራው ነጻነቱን አውጆ ከሌላው ወንድም የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ለአገሩ ለኢትዮጵያ በጋራና በእኩልነት ሊቆም ይችላል፡፡

ነገር ግን አማራው ከሁሉም ነገር በፊት ውስጡን አጽድቶ ራሱን በዚህ መልክ ነጻ ማውጣቱን ሳይገፋበት ቀርቶ የክልሉን ነጻነትና የአማራነቱን ታላቅነት በአስተማማኝ ደረጃ እውን ሳያደርግ በፊት ለኢትዮጵያ እቆማለሁ ካለ ተንሳፍፎ፣ ተንቀራፍፎ፣ ተገፍቶና ተጨፍጭፎ በህይወት የሚተርፈው አማራ አገር አልባ ሆኖ ይቀራል፡፡ አማራው ነቅቶ ቀድሞ ራሱን ካላዳነ ያኔ ከሁለት የወጣ ጎመን ይሆናል፡፡ በአማራነቱ እየተመረጠ ተጨፍጭፏል ፡፡በኢትዮጵያዊነት ምትክም ኦሮሙማን ተገድዶ እንዲቀበል ይደረጋል፡፡

ስለዚህ አማራ ሆይ፦ መጪው ጊዜህ ከአሁን የባሰ ድቅድቅ ጨለማ ከመሆኑ በፊት ነጻ የምትወጣበትን የብርሀን ችቦህን ዛሬዉኑ ለኩስ፡፡ ችቦህም የራስህን ሆዳምች ከላይህ ላይ አሽቀንጥሮ መጣል ነው በአጭሩ፡፤ ሌላው ሁሉ ገብስ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop