July 21, 2022
7 mins read

በጠላት ነፃ የሚወጣ ህዝብ የለም !  

ኢትዮጵያ ላለፉት ሶስት  አስርተ ዓመታት  የገባች የፅልመት እና ዉቀድቀት ጉዞ በግፈኞች እና ኢትዮጵያ ጠል ጥምር የጥፋት ሴራ ከጂምሩ ግንቦት ፳ ቀን አስራ ዘጠኝ መቶ ሠማንያ ሶስት የተዘራዉ የጥፋት እና ሞት ዕሳት ሁለንተናዊ መቀጣጠል እየሆነ ነዉ ፡፡

ፀረ ኢትዮጵያዉያን ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ፣ ከታሪክ ማማ ለማዉረድ እና ከሰማይ በታች ኢትዮጵያን ለማጥፋት ከጥፋት ስምምነት (ጥላቻ እና አግላይነት) ሠነዶች በሚቀዳ ክህደት የኢትዮጵያ ህዝብ እና አገር ተደፍሯል፡፡

ኢትዮጵያን ከዉስጥ በማናጋት ከዉጭ በማጋጫት  አገር ያለ በር (ወደብ)፣ ዳር ድንበር ሲደፈር ፣ ህዝብ በማንነቱ በአገሩ ሲሳደድ፣ ሲዋረድ ፣ ሲታረድ እና ሲሞት ዓሜን ብሎ የተቀበለዉ አጥፊዉ እና የአጥፊዉ ተባባሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ዛሬ ስለ ብሄራዊ አንድነት ፣ ደህንነት ፣ሠላም እና ዕርቅ ሲያስተጋባ ማየት ህመሙ ሠዉነት ላለዉ ከባድ ነዉ ፡፡

ትናንት በመላዉ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያን ጥንታዊ እና ታሪካዊ ታላቅነት ለማጥፋት በኢትዮጵያዊነት እና ዓማራነት ላይ ለደረሰዉ ክህደት እና ጥፋት ለምን ማለት ሆዱ እና ጥቅሙ ከአገር እና ህዝብ በላይ የሆነባቸዉ አድር ባዮች ዛሬ ስለ ህዝብ እና አገር የአዞ ዕንባ የሚያነቡ  አስመሳዮች ከናዚዎች በምን እንደሚለዩ ግልፅ አይደለም ፡፡

ናዚዎች በአገራቸዉ እና ከአገራቸዉ ጀርመን ዉጭ የሚኖሩትን የዘመኑን ፅዮናዉያን  አሳዶ ማጥፋት በወቅቱ ከነበሩት ዘረኞች በመሆን ዘረ-ፅዮናዉያንን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት  ክንዳቸዉ እስኪዝል የዘር ፍጂት እና ጥፋት አድርገዋል፡፡

እ.ኤ.አ. 1940 ለእስራኤላዉያን እንደ አገር መመስረት መሰረቱ የአስራኤላዉያን ( ፅዮናዉያን) ያላሳለሰ ብርቱ ክንድ እና ህብረት ተጋድሎ ተመሰረተች እንጂ ናዚዎች እና ተስፋፊ የጥፋት ግብረ አበሮች አልነበሩም ፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ የደበቡብ አፍሪካ የቅርብ ጊዜ ነፃነት ዕዉን የሆነዉ በቅኝ ገዥዎች  እና በአድር ባዮች ሳይሆን ዕንቁዉ የጥቁር ምድር የነፃነት ታጋይ  እና መሪ ኔልሰን ማንዲላ ቁርጠኛ መሪነት ብቻ እና የነፃነት ታጋዮች የደም እና ህይወት ዋጋ ክፍያ ነበር ፡፡

እኮ እንዴት ነዉ ዛሬ ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዉያን እና ዓማራ በዘመኑ  ኢትዮጵያ ጠሎች (Racist ) ሠላም ፣ አንድነት ፣ነፃነት እና ህልዉና ሊረጋገጥ የሚችለዉ ፡፡

ለምንድን ነዉ ዕዉነት ስለ ኢትዮጵያ እና የሰዉ ልጆች ደህንነት እና ክብር ያሳስበናል የሚሉት ስለተበዳይ ካሳ እና ስለበዳይ መካስ እና መከሰስ(መጠየቅ) አንድም ጊዜ መናገር የማይችሉት ፡፡

ኢትዮጵያ የሁላችን አገር ናት ብለን ዋጋ መክፈል እንዴት እንደ መናኛ ዕቃ እየተወረወረ ኢትዮጵያ ለሞቱላት ዕሬት ፤ለገደሏት ወተት እንድትሆን የሚሰራዉን ብሄራዊ ደባ ሳናስቆም እንዴት ጥልቅ እና ሩቅ የሚጓዝ ብሄራዊ ስምምነት እና አንድነት ይኖራል፡፡

ለማንኛዉም የየትኛዉም አገር ህዝብ ሉዓላዊነት በዜጎች ነፃነት እና ህልዉና መከበር ጋር የማይነጣጠል እንደመሆኑ ዕዉነተኛ እና ዘላቂ ብሄራዊ ጥቅም ለማንበር ምርት እና ግርድ መለየት ያስፈልጋል ፡፡

ጠላትንም ሆነ የተወሰነ መደብ ጥቅም እና ፍላጎት ለማስጠበቅ ሲባል የህዝብ እና አገር ጉዳይ ቸል ማለት ቆሞ ለአገር እና ህዝብ የሚሆን ስም እና ታሪክ ሰርቶ ማለፍ በሚያልፍ ዓለም የዘላለም ስም ለትዉልድ እናዓለም ማሳለፍ ይጠቅማል፡፡

ህዝብ በአገሩ እና በምድሩ እየሞተ የሚፈጠር አገር ስለማይኖር የግል እና የወል የመኖር ተፈጥሯዊ መብት ሳይከበር ብሄራዊ ጥቀም እና ሠላም ማስከበር የሠላሳ ዓመታት ንግግር እንጂ ገቢር ሆኖ ባለመታየቱ ተግባር እና ግንባር ፊት ለፊት መምጣት ይኖርባቸዋል ፡፡

ከዚህ ዉጭ ለዓመታት የደም እና ዕንባ ጎርፍ ለሚያጥባት አገር በንግግር እና ግንባር በማዞር  አይቶ እንዳላየ ፤ሰምቶ እንዳልሰማ የሆነ ስለምን ይነገራል በምን መመዘኛ ፡፡ አበዉ  “ ማን ይናገር የነበረ ፤ ማን ያርዳ የቀበረ ”   እንዲሉ ሲሆን ከዚህ ዉጭ  ጩኸቴን ቀሙኝ የብልጠት  ንግግር እና የክህደት ሩጫ መቋረጥ ይኖርበታል ፡፡

 “የየትኛዉም ህዝብ  ነፃነት እና ህልዉና የሚረጋገጠዉ  በተባበረ ክንድ  ብቻ ነዉ  ”

ኔሎስ

 

1 Comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

adanech Abebe
Previous Story

በህገ አምላክ!  ወይዘሮ አዳነች – ገለታው ዘለቀ

download 3
Next Story

ታዬ ድንድዓ በኦሮሞ ክልል ጨፌ (ምክር ቤት) እንዳይናገር መደረጉ የኦህዴድ ብልጽግና ምን ያህል ትልቅ ችግር ውስጥ እንደገባ አመላካች ነው – ግርማ ካሳ

Latest from Blog

blank

አርበኛ አስረስ ማረ እና ምርኮኞቹ | ስለ ፋኖ የብሔራዊ ባንክ ገዥው ያልተጠበቀ ንግግር |

#ሰበር_ዜና #AmharaFano ➢መሰከረም 29/01/2017 ዓ.ምብዙ ድሎችን አግኝተናል፣➢1️⃣115 ምርኮኛ ➢2️⃣70 እስረኞችን አስለቅቀናል➢3️⃣ 7 ብሬን➢4️⃣2 ድሽቃ➢5️⃣ 4 ስናይፐሮችን➢ለትግል የሚጠቅሙ የነፍስ ወከፍ ክላሾችንተተኳሾችን መኪኖችም ገቢ… pic.twitter.com/GbYaOAtFtr — ትዝብቱ🔔 (@Geteriew1) October 12, 2024 በፋኖ የተማረኩት ኮሎኔል
blank

ትግሉ ይጥራ – ከጥሩነህ ግርማ

የህልውና ትግሉን ወደሚቀጥለው ምዕራፍ ለማሸጋገር የኦይዶሎጂ ብዥታን ማጥራትና በመሬት ላይ ያለውን ተንኮል መጋፈጥና ማፅዳት ያስፈልጋል የህልውና ትግሉ በአማራ ብሄርተኝነት ላይ ያጠነጠነ እንደመሆኑ የመኖር አለዚያም እንደ ህዝብ  የመጥፋት ትግል ነው: ሌላው ኢትዮዽያዊ ወገን
blank

የፋሽስቱ አብይ አህመድ አሊ ኢትዮጵያ ውስጥ በአማራ ላይ እየተካሄደ ስለሚገኘው ጦርነት ከመስከረም 13 እስከ 27/2017 ዓ.ም በተለያዩ ቦታዎች ላይ የደረሰ የጉዳት !!!መረጃ:

ሸዋ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መርሀቤቴ አውራጃ በደራ ወረዳ ልዩ ስሙ ኮሉ በተባለ አካባቢ ላይ በሚገኙ የአማራ ተወላጆች ላይ አሸባሪው የሸኔ ቡድን ከኦሆዴዱ ጥምር ጦር ጋር ቅንጅት በመፈጠር መስከረም 22 ቀን 2017ዒ.ም ከለሊቱ
Go toTop