ዋናው ሊቀ ሠይጣን፣ ምነው ባላመጣኝ (ለጊምቢ ቶሌ ተጨፍጫፊዎች አንደኛ ወር መታሰቢያ)

ዋናው ሊቀ ሠይጣን
ጊምቢ ኦሮሚያ ጊምቢ አኬልዳማ
ጋፈ ወሎ ፊጠን
አከ ኢልማ ዲና አከ ኢልማ ኦርማ*
ሰኔ አሥራ አንድ ቀን የአሥራ ሁለት ዋዜማ
ንጹሕ የአራሽ ልጅ ታጭዶ እንደ ቄጤማ
ይቅርና ካሣ፣ እንባ ሚያብስ ጉማ
ለኅሊና ጸሎት እምቢ ሲል ፓርላማ
ሃያ / ሁለት ሰዎች ካንድ ቤት ያረዱ
የንጹሐንን ደም በጎርፍ ያወረዱ
ደሃን አስዘርፈው
ልጅ፣ ሴት አስጨፍጭፈው
ከብቶች አስነድተው
ሺዎች አስፈጅተው
ምንም ሳይነኩ ከቀሩ በሥልጣን
አቢይ አይደለም ወይ ዋናው ሊቀ ሠይጣን?
(አንተ አይደለህም ወይ ዋናው ሊቀ ሠይጣን?)

*ወሎን እንደ ጠላት ልጅ እንደ ባእድ ልጅ የፈጁት ቀን

ምነው ባላመጣኝ
ከሰማይ ለአመታት ቢጠፋ ደመና
ሰው ቅጠልም ቢረግፍ በርትቶ ቀጠና
እድሜዬን ለማርዘም
ምነው ባላመጣኝ
ያ የደርግ መኪና፤
እንዲህ ዘር ማንዘሬን
ጅብ አሞራ እስኪጠግብ
ከሚያጭድ ብልጽግና።
ኦነግ ኦሪት ሳይሆን
ኦነግን ተዋርሶ
ኦሪትን ሲያጸና፤
መድሓኒት ነው ያልነው
መራራ መርዝ ሆኖ
አገር ሲሆን ዲና፤
ከብቶቼ ሊነዱ
ቤቴ ሊሆን ከሰል
ቀዬው ሊሆን ኦና፤
ወልዲያ መርሳ ቆቦ
ላስታ ላሊበላ
ዋድላ ወይም ቡግና፤
መንደሬ ላይ ብቀር
ምነው እንደናፈቅሁ
ጉም፣ ጭጋግ፣ ደመና፡፡
ስድስት ወልዶ መካን ባምስት ጠምዶ ባዶ በአንዲቷ ጀምበር
ከምሆንስ ምነው ያ የደርግ መኪና ባላመጣኝ ነበር።
በኢትዮጵያ ምድር በገዛ ሀገሬ
አርሼ በበላሁ አርሼ ባበላሁ በኖርኩ ጥሬ ግሬ
ጎረቤት ያልኳቸው ወገን የመሰሉኝ
በእሳት ከሚያከስሉኝ
እንዲህ ከሚፈጁኝ ያላንዳች በደሌ ስለሆንኩ አማራ
ሕይወቴን አትርፎ ምነው ባላመጣኝ የደርጉ ሠፈራ።

*ቀጠና = ድርቅ፣ ረሃብ

ለጊምቢ ቶሌ (ወለጋ፣ ኦሮሚያ) የሰኔ አሥራ አንድ ጭፍጨፋ ሰለባዎች መታሰቢያ ይሁን።
አሁንገና ዓለማየሁ

ተጨማሪ ያንብቡ:  "እረኛ የሌለው ከብት ሆነናል" የአጣዬ ከተማ ነዋሪዎች ሰቆቃ ግድያና እንግልት

In this massacre of mostly women and children, entire families perished. The Tole, Wellega massacre of June 18 was followed by another massacre on 4th of July, 2022 in Qellem, Wellega. In the Sene Oromia massacre of Amharas, although more than two thousand people were killed, the bodies of less than 1000 people were found and buried. The majority of the victims were Moslem Amhara farmers. The sustained campaign of ethnic cleansing and genocide against the Amhara has been raging for the last four years and the so-called international community has chosen silence.

By contrast, the Ethiopian government has not been silent. It has been busy minimizing the scale of the massacre, blocking efforts to observe a national day of mourning and attempting to obfuscate its active involvement in the genocide.

https://zehabesha.com/ethiopia-wollega-massacre-death-count-surpasses-1500/

———————-

 

https://youtu.be/ra0e4Ex9K1U

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share