መኢአድ፣ እናት ፓርቲና ኢሕአፓ “የክብር አፈር ስለተነፈጋቸው የዘር ፍጅት ሰለባዎች ጥቁር በመልበስ የህሊና ፀሎት በማድረግ እናስባቸው” በሚል በአዲስ አበባ የሻማ ማብራት መርሐ ግብር

አምስተርዳም :- ሐምሌ 04/2014 ዓ.ም
አሻራ ሚዲያ
መኢአድ፣ እናት ፓርቲና ኢሕአፓ “የክብር አፈር ስለተነፈጋቸው የዘር ፍጅት ሰለባዎች ጥቁር በመልበስ የህሊና ፀሎት በማድረግ እናስባቸው” በሚል በአዲስ አበባ የሻማ ማብራት መርሐ ግብር አከናውነዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ:  የታምራት ገለታ አዲስ ጨዋታ

1 Comment

  1. መቸም እንኳንስ በእኩያን ገዥ ቡድኖች በቀጥታና በተዘዋዋሪ በሚታገዙ የገንዛ ወገኖቻቸው በግፍ ለተጨፈጨፉ ንፁሃን ወገኖች በግፍ ለሚገደል ማነኛውም ሰብአዊ ፍጡር ሃዘንን መግለፅ አስፈላጊ አይደለም የሚል ባለ ጤናማ አእምሮ ሰው የሚኖር አይመስለኝም። እናም ከዚህ እይታ አንፃር እነዚህ የፖለቲካ ድርጅቶች አባላት ያደረጉት ትክክል ወይም ተገቢ የሚሆነው ማለት ይቻላል ።

    እጅግ ትልቁና ፈታኙ ጥያቄ ግን ለዘመናት የመጣንበትና ከአራት ዓመታት ወዲህ ደግሞ በተረኞች እጅግ አስከፊ በሆነ አኳኋን እየቀጠለ ያለው የመከራና የውርደት ዶፍ በእንዲህ አይነት ሲምቦሊክ በሆነ ክንውን ይቆማል ወይ ? እውን ይህንን አይነቱን ድርጊት አልባ የመግለጫ ጋጋታና የሃዘን እግዚኦታ በእውን ሰምቶ ምላሽ የሚሰጥ አምላክ አለ ወይ ? ከአራት ዓመታት ለማሰብ የሚከብድ ግፍና መከራን ለማስቆም ከዚህ እይነት ሲምቦሊክ ከሆነ የሃዘን እየየ ለምንና እንዴት ተሳነን ? እውን ይህንን ማድረጋችን እንደ ትልቅ የፖለቲካ ሥራ ቆጥረን እንቅልፍ እየተኛን ይሆን? ለምድነው እነዚህ ፓርቲዎች ተብየዎች በዚህ የሰቆቃ ወቅት ንድ መሆን ባይችሉ እንኳ በዋና ዋና የአገሪቱ ጉዳዮች ዙሪያ አንድ አይነት ግንባር ወይም የጋራ የፖለቲካ ዣንጥላ ሥር ተሰባስበው ትርጉም ያለው (ከመግለጫና ከሃዘን ስብሰባ ያለፈ ) ሥራ መሥራት ተሳናቸው ? ፣ ወዘተ የሚለው ። እናም እውነተኛና ውጤታማ ልብ ይስጠን !!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share