አራምባና ቆቦ…..ሰውየው ምን ያህል ጮርቃ እንደሆነ ያሳያል

ሰው በዘሩ በብሄሩ ተለይቶ ወለጋ ውስጥ ባደራጃቸው ነፍሰ በላዎች የሚፈጸመውን ዬአማራ ጭፍጨፋ አሜሪካ እድሜው ለአቅመ አዳም ባልደረሰ የ lአእምሮ ህሙማን ጎረምሶች ትምህርት ቤት ውስጥ ዘርና ብሄር ሳይለዩ ከሚከፍቱት የተኩስ እሩምታ ጋር ማነጻጸር ሰውየው ምን ያህል ጮርቃ እንደሆነ ያሳያል….።
በዚያ ላይ ተረት ተረቱ ……ቱ

የምክር ቤት አባላት ያነሷቸው ጥቄዎች ግን ቀጣዮቹ ናቸው ፦

 • ባለፉት አራት አመታት እየተፈጸመ ያለው የዘር ፍጅት የብሔራዊ ደኅንነት ስጋት ነው ብሎ መንግሥት ምን ያህል ያምናል?✍️የንጹሃን ሞት እና እልቂት መቋጫ እንዲኖረው መንግሥት ምን እየሠራ ነው፡፡
 • ዜጎች በነጻነት እንዳይኖሩ የኾኑበት መሠረታዊ ምክንያቱ ምንድን ነው?
 • ሽብርተኞቹ እየወሰዱ ላሉት የንጹሃን ግድያ መንግሥት እየወሰደ ያለው አጸፋዊ እርምጃ ምንድን ነው?
 • የመንግሥት ቀዳሚ ተግባር ዜጎችን ከጥቃት መጠበቅ ቢኾንም ይህ መሆን ያልቻለው ለምንድን ነው?
 • መንግሥት ለምን ሕግ ማስከበር አቃተው?
 • በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያሉ የሽብር ቡድኑን የሚደግፉ ሰችዎችን መለየት ለምን አልተቻለም?
 • ሰዎች ለሰላማዊ ተቃውሞ በወጡ ሰዎች የአካል መጉደል እና ግድያ መፈጸሙ ያለውን የሀገሪቱን ሕግ የሚጥስ አይደለም ወይ?
 • የዘር ፍጅቱን መንግሥት እንዴት እና መቼ ለማስቆም እያሰበ ነው?
 • የፍትህ ተቋሙ የዘር ፍጅት በሚፈጽሙት ላይ ለምን ክስ መመስረት አልተቻለውም?
 • መንግሥት የዘር ፍጅቱ ላይ ፍትህ መስጠት ካልቻለ ሰለባዎቹ በዓለማቀፍ መድረክ ፍትህ እንዲያገኙ ምን ያህል ቁርጠኛ ነዎት?
 • መንግሥት ከሱዳን የሚሰነዘረውን ትንኮሳ እንዴት እያየው ነው?
 • የኢትዮጵያን መሬት ወርሮ የሚገኘው የሱዳን መንግሥት እና የጦር ጀኔራሎቹን እብሪት መንግስት በምን አይነት መንገድ ሊፈታ አስቧል?
 • ድርድርን በተመለከተ ገዥው ፓርቲ ለብቻው ለመደራደር የሚያደርገው እንቅስቃሴ ትክክል አይደለም፡፡
 • በአሸባሪነት የተፈረጀው ድርጅት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪነቱ ባልተነሳበት ሁኔታ ለመደራደር መሞከር ወንጀል አይደለም ወይ?
ተጨማሪ ያንብቡ:  አወጋን በወልቃይት ጎሮ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የአማራ ልጆች እንዳይማሩ መከልከላቸውን ገለጸ

 አፈትላኪ ዜናዎች

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share