የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፖርት

IDPs 2048x1152 1ኢሰመኮ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በላከው እና በዓይነቱ የመጀመሪያ በሆነው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፖርት መንግሥት በማናቸውም ጊዜ የሰዎችን መብት እንዲጠብቅ፣ እንዲያከብር እና እንዲያረጋግጥ አሳሰበ

ሪፖርቱ የሚሸፍነው ጊዜ በኢትዮጵያ የበጀት ዓመት አቆጣጠር መሰረት ከሰኔ ወር 2013 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2014 ዓ.ም. ያሉትን 12 ወራት ሲሆን፣ በዓመቱ ውስጥ የነበረውን አጠቃላይ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን፣ የተገኙ ቁልፍ እመርታዎችን፣ ዋና ዋና አሳሳቢ ጉዳዮችን፣ ተግዳሮቶችን እና ምክረ-ሃሳቦችን ያካትታል

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን  ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በላከው የሀገሪቱ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ኮሚሽኑ በተገባደደው በጀት ዓመት ባከናወናቸው የክትትል፣ የምርመራ፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ፣ የዳሰሳ ጥናቶች እና ልዩ ልዩ ተግባራት የተመለከታቸውን መልካም ጅማሮዎችን፣ እንዲሁም በአፋጣኝ መፍትሔ ሊያገኙ እና ሊሻሻሉ የሚገቡ አሳሳቢ ጉዳዮችን የሚያካትት መሆኑን ገልጿል።

ኢትዮጵያ በምትገኝበት ወቅታዊ ሁኔታ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ በፍጥነት ተለዋዋጭ መሆኑን የገለጸው ኢሰመኮ፣ ዓመታዊ ሪፖርቱ በሚሸፍነው ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ እና በርካታ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች መከሰታቸውን አብራርቷል፡፡

ኮሚሽኑ እጅግ አስከፊ የሆኑ በማለት ያመላከታቸውን የበርካታ ሰዎች ሞት፣ የአካልና ሥነልቡና ጉዳት፣ ጾታዊና ወሲባዊ ጥቃት፣ መፈናቀልና፣ ንብረት ውድመት ጥሰቶች በመንግሥት ኃይሎችና ከመንግሥት ውጭ በሆኑ የታጠቁ ኃይሎችና ቡድኖች በጦርነትና ግጭት አውድ ውስጥ የተፈጸሙ፣ በሲቪል ሰዎች ላይ ያነጣጠሩ፣ ሴቶች፣ ሕፃናት፣ አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞችንም ጨምሮ በከፍተኛ ግፍና ጭካኔ የተፈጸሙ ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በሪፖርቱ በዝርዝር አብራርቷል፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያ ከተካሄደው ጦርነት ጋር ተያይዞ በጦርነቱ ተሳታፊ የነበሩ ሁሉም ኃይሎች ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶችን እና የሰብአዊነት ሕጎችን ድንጋጌ በሚጥስ መልኩ በሲቪል ሰዎች ላይ ጥሰቶችን ፈጽመዋል፡፡ ጦርነቱ በተካሄደባቸው አካባቢዎች በሕይወት የመኖር መብት፣የአካል ደኅንነት መብት፣ፍትሕ የማግኘት መብት፣ ከጭካኔ፣ ኢሰብአዊና አዋራጅ አያያዝና ቅጣት ነፃ የመሆን መብቶች ጥሰቶች በመንግሥት ወታደሮች፣ በሕወሓት  ኃይሎችና በተለያዩ የታጠቁ ቡድኖች ተፈጽመዋል። ተጎጂዎች በአብዛኛው ሲቪል ሰዎች ሲሆኑ፣ በጦርነት ተሳታፊ የነበሩና የተማረኩ ተዋጊዎችም ለመብት ጥሰቶች ተጋልጠዋል። በሌሎችም ክልሎች በተወሰኑ ፖሊስ ጣቢያዎችና መደበኛ ባልሆኑ የእስር ቦታዎች ከጦርነቱ ጋር በተያየዘ በታሰሩ ሰዎች ላይ  ላይ ተገቢ ያልሆነ አያያዝ፣ የተራዘመ የቅድመ ክስ እስር እና ድብደባ  ተፈጽሟል፡፡

በሪፖርቱ በተሸፈነው ጊዜ በተለይ በሥራ ላይ ከነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር ተያይዞ በበርካታ የሀገሪቱ አካባቢዎች የዘፈቀደ እስራት፣ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሰር፣ መደበኛ ባልሆኑ ቦታዎች ማሰር፣ የቤተሰብ እና የሕግ አማካሪ ጉብኝትን መከልከል እንዲሁም ምርመራ ሳይጀመር የተራዘመ የቅድመ ክስ እስራት በሰፊው ተስተውሏል። በተጨማሪም በአንዳንድ ቦታዎች ፍርድ ቤት በዋስትና እንዲለቀቁ የፈቀደላቸው፣ የክስ መዝገቦቻቸው ተዘግተው በፍርድ ቤት ውሳኔ በነፃ የተሰናበቱ እና በዐቃቤ ሕግ መዝገባቸው የተዘጋ ሰዎች ከእስር ሳይፈቱ አንዲቆዩ በማድረግ የፍርድ ቤት ውሳኔዎችም ተጥሰዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም በሕወሓት እና በመንግሥት ኃይሎች መካከል ሲደረግ ከቆየው ጦርነት ጋር ተያይዞ፤ በተለያዩ አካባቢዎች በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ ሰዎች አብዛኞቹ የተለቀቁ ቢሆንም የአፋር ክልል ፀጥታ ኃይሎች ከኪልበቲ ረሱ ዞን እና አካባቢ ከመኖሪያ አካባቢያቸው “ደኅንነታቸው ለማስጠበቅ እና በወንጀል የሚጠረጠሩ ሰዎችን ለመለየት” በሚል ምክንያት የሰበሰቧቸውን ወደ ዘጠኝ ሺህ የሚጠጉ የትግራይ ተወላጆች ሰመራ ከተማ በሚገኙ ሰመራ እና አጋቲና ካምፖች ከታኅሣሥ ወር 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ይህ ሪፖርት ይፋ እስከተደረገበት ጊዜ ከፈቃዳቸው ውጭ ተይዘው የሚገኙ መሆናቸውን ኢሰመኮ በሪፖርቱ አስታውሷል፡፡ በካምፖቹ ከሰብአዊ እርዳታና የሕክምና አገልግሎት ውስንነት የተነሳም ለሕይወት መጥፋት ምክንያት መሆኑንም አክሎ ገልጿል፡፡

በትግራይ፣ በአፋር እና በአማራ ክልሎች የተካሄደው ጦርነት በአካባቢዎቹ በመሰረታዊ አገልግሎቶች መቋረጥ፣ በጤና እና በትምህርት ተቋማት፣ እንዲሁም በግል ንብረቶች ላይ ያደረሰው ውድመት፣ እንዲሁም ጦርነቱ ባስከተለው  መፈናቀል ሳብያ በተከሰተው የእርዳታ  ፈላጊዎች መጨመር፣  በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተከሰቱ ግጭቶች ሳቢያ ምርት መስተጓገሉ  በተለይም ምግብ የማግኘት መብት፣ በጤናና ትምህርት አገልግሎት የማግኘት መብቶችን ጨምሮ በሁሉም ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መብቶች ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳደረ መሆኑን በሪፖርቱ ተመልክቷል። ከዚህም በተጨማሪ በኦሮሚያ እና በሶማሌ ከልሎች የሚገኙ አንዳንድ አካባቢዎች በድርቅ በመጠቃታቸው ምክንያት በመንግሥት እና መንግሥታዊ ባልሆኑ የእርዳታ ድርጅቶች የሚያቀርቡ ድጋፍ የመስጠት አቅም ላይ ጫና ያሳደረ መሆኑን ገልጿል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከ4 ሚልየን በላይ የሚቆጠሩ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች አሁንም አሳታፊ የሆነ ዘላቂ መፍትሔ የሚጠብቁ መሆናቸውን እና የእርዳታ አቅርቦቱም ሆነ በአጠቃላይ ሀገራዊው የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች የተጠለሉ ስደተኞችን ሕይወት ላይም ተጽዕኖ ያሳደረ መሆኑም ተገልጿል። በተመሳሳይ መልኩ የሴቶች፣ የሕፃናት፣ የአረጋውያን እና የአካል ጉዳተኞች ሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ክትትል እና በተለይም የመንግሥት አካላትን ትኩረት የሚጠይቅ መሆኑንም ኢሰመኮ በሪፖርቱ አስረድቷል።

የአመለካከት፣ ሃሳብን በነጻ የመያዝና የመግለጽ እንዲሁም መረጃ የማግኘት መብቶችን በተመለከተ ኢሰመኮ ባደረገው ክትትል መሰረት፣ ከሐምሌ ወር 2013 ዓ.ም. እስከ ግንቦት ወር 2014 ዓ.ም. ድረስ በተለያዩ ወቅቶች፣ በትግራይ ክልል ተይዘው የሚገኙ መሆናቸውን የተገለጹ 15 የሚድያ ሠራተኞችን ጨምሮ 54 የሚዲያ ሠራተኞች ተይዘው ከቀናት እስከ በርካታ ወራት ለሚሆን ጊዜ በእስር መቆየታቸውን አመላክቷል፡፡

የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርቱ በ2014 በጀት ዓመት መጀመሪያ ላይ የተካሄደውን 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በተመለከተ፣ ለኢሰመኮ የቀረቡ አቤቱታዎች ላይ የተመረኮዙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን፣ እንዲሁም መደበኛ ባልሆኑ ማቆያ ስፍራዎች፣ በማረሚያ ቤቶች እና በፖሊስ ጣቢያዎች በጥበቃ ሥር ያሉ (የታሰሩ) ሰዎች መብቶች እና የተያዙ ሰዎች ሁኔታን በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎችን እንደሚያካትት ኮሚሽኑ ባዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ተብራርቷል።

በበጀት ዓመቱ በተለያዩ የመንግሥት መዋቅሮች ከተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች በተጨማሪ መንግሥታዊ ባልሆኑ አካላትም ዘርፈ ብዙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተፈጽመዋል። በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ከተከሰተው ጦርነት ጋር በተያያዘ እና በሌሎችም አካባቢዎች በታጠቁ ኃይሎች፣ በኢመደበኛ ቡድኖች እና በግለሰቦች በሲቪል ሰዎች ላይ ብሔርን ወይም ሃይማኖትን መሰረት ያደረጉ ጾታዊና ወሲባዊ ጥቃቶችን ጨምሮ፤ የግድያ፣ የአካል ጉዳት፣ ማፈናቀል እና የንብረት ማውደምና ዘረፋ ድርጊቶች መፈጸማቸውን ኮሚሽኑ በበጀት ዓመቱ ባከናወናቸው የሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ ሪፖርቶች ማረጋገጡን ሪፖርቱ ያስታውሳል፡፡

“በአጠቃላይ በሀገሪቷ የተከሰተው ጦርነት፣ ግጭት እና የተስፋፉ በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶች መንስዔያቸው የፖለቲካ አለመግባባት/አለመረጋጋት ውጤት ስለሆኑ ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት ሁሉን አቀፍ ፖለቲካዊ መፍትሔ አስፈላጊ መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው” በማለት የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በሪፖርቱ ባሰፈሩት መልዕክት ጥሪ አቅርበዋል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነሩ አክለውም “የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርቱ ኮሚሽኑ ለአንድ ዓመት ባከናወናቸው የሰብአዊ መብቶች ሥራ አማካኝነት በምርመራ፣በክትትል፣ በጥናት እንዲሁም በሰብአዊ መብቶች ትምህርት ተግባራት የሰነዳቸውን ጉዳዮች የሚዳስስ እንደመሆኑ የአካባቢያዊ፣ የጊዜና የሰብአዊ መብቶች ዘርፎች ሽፋን ውስንነቶች ቢኖሩበትም፣ እጅግ አሳሳቢና አፋጣኝ መፍትሔ ሊያገኙ የሚገባቸው የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን የሚያመላክት ነው። ስለሆነም በተለይም ለፌዴራል እና ለክልል መንግሥታዊ ባለድርሻ አካላት በየዘርፋቸው የሚመለከታቸውን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል ለማድረግ እና ለማሻሻል ተገቢውን ምክረ ሃሳብ የሚያቀርብ ነው” ብለዋል። ሪፖርቱ ለሌሎች መንግሥታዊ ላልሆኑ ሀገራዊና ዓለም አቀፍ ድርጅቶችም ለሥራቸው አስፈላጊ የሆነ ግብዓት የሚሰጥ መሆኑንም ጨምረው  ገልጸዋል፡፡


 

1 Comment

  1. ሰብአዊ መብት

    One Shegitu Dadi, a very forward looking Oromo woman has the following to say on confederation. I’m copying and pasting her write-up without her authorization hoping that she’ll not mind.

    “Here is how to save Amharas, Oromos and the country.

    Once again in our recent history, Amharas have emerged as the holders of the MASTER key to solve Ethiopia’s multifaceted problems . How? By opting for confederation.

    Amharas have no choice but to move for confederation simply because federation in the Ethiopian context does not work.

    As a polirized multi-ethnic country, Ethiopia will not have a fair and free election without the opression of one or another ethnic group. Hence, democracy is an illusion that cannot be realized. The way Oromo rose to power and now control the entire country through proxy regional governments is the proof. Tigreans did it for the last thirty years and Oromos have stepped in Tigreans shoes to impose similar one ethnic group rule. With their number and size of their region, Oromo opressive rule will be much worse than Tigrean`s. Give another ten years to Oromo rule, Ethiopia will be the tail of the world by all standards of measure.

    So, it is time for Amharas to exercise their constitutional right to self-determnation and vote on confederation. If they adopt conederation, it will give them the opportunity to attract direct foreign investment since confederation will enable them to have economic diplomats and even have embasies abroad cutting the Oromo controlled foreign ministry diverting foreign investment to Oromia and other favoured regions. Amharas can also have a defense force which will protect them from foreign invaders including ethnic Oromo organizations.

    The Belgian model of confederation which appears to hep advance Amhara interests is something to explore.

    In any event, Ethiopia needs vast decentralization resembling confederation since the federalism the country has adopted is notheing other than unitarism in disguise. Controlled from the centre, it has miserably failed to develop the country let alone prosper and ensure safety and security of its citizens. The chaos we see in the country right now has much to do with lack of development (in all sectors) and security. Both have proven beyond the capacity of the federal government to provide.Change of government at federal level is not the answer for these problems.

    Tigreans have floated the idea of confederation, Amharas must follow. Tigreans know that they will not be fairly treated under Oromo rule; as a result, their choice of confederation appears just. Amharas must seize the opportunity to decide their destiny via self-determination as well without wasting another decade under incompetent Oromo rule. Despite all the atrocities they have committed, Tigreans are being heard and embraced by the Oromo rule since Oromos now feel tobe the savours of Ethiopia.

    Folks! Don’`t be fooled!. Oromos pretend to be “savours” only if they rule the entire country as one piece. Like any other ethnic group that aspire to oppress and dominate , they are after resources. If Amharas want to be heard and embraced as Tigreans, they have to go for confederation. If confederation does not work, they have to say good bye to the Ethiopian state.

    It is outdated for Amharas to hang on “mama ethiopia” cry since nobody in the country is interested in it any more. What Amharas got from this cry is atrocotoes, redicule and shame. All these on Amhara because they gave Oromos and other ethnic groups a country which they are not ready and willing to let go. If Amhara Insist on confederation, Oromos might call the army on it to protect the unity of the country! That will make them a laghing stock since they were in the forefront to weaken the unity of the country. Now they cannot be alllowed to reverse gear.

    Amhara! Wake up and smell the coffee. Tell Oromos that you want confederation – if not confederation then separation. Oromo crack down will soften even disappear as it did for Tigreans if Amara opt for confederation. But the idea is not to see Oromo softening on Amhara, it is to seek real confederation as a wayout from decades long quagmire. Oromo softeneing does not take Amharas anywhere.

    Try it! It will work and catapult Amhara development and growth to the sky and ensure their security. It will eventually liberate Oromos too from their bloody distructive path poised to takie everybody else down with them.

    For us, Oromos, conederation is also the answer. ”

    GREAT!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

12334445rr
Previous Story

ጃዋር መሐመድ ተከበብኩ ካለ የሚገደለው አማራ ነው፣ ከአብይ ጋር በስልጣን ከተጣሉ የሚገደለው አማራ ነው

advocacy
Next Story

ዘረኝነትን መታገል የሁላችንም ግዴታና ሃላፊነት ነው

Go toTop