የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የፓርላማውን ሥልጣን በመጣስ ዳኞችን ሰይሟል – የአማራ ክልል ፍርድ ቤት ዳኞች ማኅበር

በሲሳይ ሳህሉ|ሪፖርተር

የአማራ ክልል ዳኞች ማኅበር የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች  አስተዳደር ጉባዔ፣ ሕገ መንግሥቱንና የፓርላማውን ሥልጣን በመጣስ ዳኞችን ሰይሟል የሚል ቅሬታ አቀረበ፡፡ ለዳኞቹ የተሰጠ ሹመት እንደሌለ፣ ነገር ግን ውዝፍ መዛግብትን ከሰኔ 2014 ዓ.ም. እስከ ታኅሳስ 2015 ዓ.ም. ድረስ ለማጠናቀቅ የሚያግዙ አራት ዳኞች ከከፍተኛ ፍርድ ቤት መመደባቸውን ሪፖርተር ከምንጮች ሰምቷል፡፡

ጉባዔው ሥራዎችን ለማከናወን በፌዴራል ከፍተኛና በመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች የሚገኙ ዳኞችን ጨምሮ በክልል ደረጃ በዳኝነት ከሚያገለግሉ ዳኞች በፈተና አወዳድሮ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እየሾመ የቆየ ቢሆንም፣ አሁን ላይ አሠራሩን ከሕግ ውጪ እንደቀየረ ማኅበሩ አስታውቋል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞችን ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚሾምበትን ሥርዓት ሳይከተልና በክልል የሚገኙ ዳኞችን መብት ሳይጠብቅ፣ ለፌዴራል ፍርድ ቤት የሚሠሩ ዳኞች በሕዝብ ተወካዮች  ምክር ቤት ሳይሾሙ፣ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ውሳኔ ብቻ ዳኛ በማድረግ ተሰይመው እንዲሠሩ እየተደረገ መሆኑን ማኅበሩ አስታውቋል፡፡

በመሆኑም አሠራሩ በክልል ደረጃ የሚሠሩ ዳኞች በፌዴራል መንግሥቱ ዳኝነት ሒደት ላይ የመሳተፍን መብት የነፈገ እንደሆነ በመግለጽ፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ በዚህ ረገድ የሰጠውን ውሳኔ እንዲከልስና የተለመደውን ሕጋዊ አሠራር በመከተል የክልል ዳኞችን መብት፣ እንዲሁም የሕዝብ ተወካዮችን ሥልጣን እንዲያከብር ‹‹አጥብቀን እንጠይቃለን‹‹ ሲል ሰኔ 17 ቀን 2014 ዓ.ም. በጻፈው ደብዳቤ አስታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከአሁን ቀደም በፈተና አወዳድሮ ያለፉትን የክልሉን ዳኞች በማግለል፣ ያለ ውድድር የሚፈልጋቸውን ሰዎች ወደ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኝነት እንዲመደቡ በማድረግ፣ በሕገወጥ መንገድ  መሥራቱንም በመግለጫው አስታውቋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ‹‹አገራዊ ምክክሩ ታሪክ ላይ ብቻ መንጠልጠል የለበትም›› ባህሩ ዘውዴ (ኤመሬተስ ፕሮፌሰር)፣ የታሪክ ተመራማሪ

ውሳኔው የሕገ መንግሥቱን ዓላማ ያላገናዘበ በአገሪቱ የሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦች በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኝነት ሥርዓት የመሳተፍ መብትን የነፈገ መሆኑን ማኅበሩ ገልጿል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአዲስ አበባና ድሬዳዋ ብቻ የታጠረ አድርጎ በመገንዘብ የክልሎችን ተሳትፎ መንፈጉ፣ በክልል ደረጃ ሲያገለግሉ የቆዩትን ከፍተኛ የሥራ ልምድና የትምህርት ዝግጅት ያላቸውን ዳኞች የሚያገል፣ ለሚፈለገውም ‹‹አንድ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ መገንባት›› የሚለው የሕገ መንግሥቱን መርህ የጣሰ እንደሆነ አስረድቷል፡፡

በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 78(2) መሠረት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌዴራሉ መንግሥት ከፍተኛ የዳኝነት አካል እንደሆነ መደንገጉን፣ እንዲሁም በአንቀጽ 80(3)(ሀ) እንደተመላከተው፣ በክልል ፍርድ ቤቶች የሚታዩትን የፌዴራል ጉዳዮችና የክልል ፍርድ ቤቶች ሥልጣን የተሰጡትን ማናቸውንም የመጨረሻ ውሳኔዎች በሰበር የማየት ሥልጣኑን በመጠቀም፣ ጉዳዮችን እየተቀበሉና እያስተናገዱ እንደሚገኙ ማኅበሩ አስታውቋል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከአሁን ቀደም ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሲሾም በአገሪቱ ከሚገኙ ዳኞች መካከል በማስታወቂያ ጥሪ ተደርጎ በፈተናና በትምህርት ዝግጅት መሠረት በማወዳደርና አሸናፊዎችን በመለየት፣ በመጨረሻም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲሾም እንደነበር ማኅበሩ አውስቷል፡፡

ማኅበሩ ሰኔ 21 ቀን 2014 ዓ.ም.  ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትና ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች አስተዳድር ጉባዔ ጽሕፈት ቤት በላከው ደብዳቤ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ውሳኔ እንዲነሳና እንዲታረም ሲል ጠይቋል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ሕገ መንግሥታዊ አሠራርን በመጣስ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ አመራርና በጉባዔው ውሳኔ ብቻ በከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚሠሩ ዳኞችን ያለ ምንም ውድድርና ምልመላ ሥርዓት መርጦ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኝነት ተሰይመው እንዲሠሩ መሾሙ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን የሕዝብ ሉዓላዊነት ሥልጣን የሚጥስ፣ በመንግሥት አካላት መካከል ያለውን የእርስ በርስ ቁጥጥርና ክትትል ሥርዓት የሚፃረርና በፌዴራል ሥርዓቱ መርህ የሆነውን የዜጎች በፌዴራል መንግሥቱ የመሳተፍና የመወከል መብታቸውን የሚጥስ ኢሕገ መንግሥታዊ አሠራር ስለሆነ ሊታረም እንደሚገባው አስረድቷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  መኢአድ “ሕዝባዊ አንድነት ለነፃነት” የሚል የሕዝብ ንቅናቄ ጀመረ

በሌላ በኩል የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አሠራር፣ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ዳኞች በሕግ ያላቸውን የመወዳደርና የመሳተፍ መብት ላይ መዋቅራዊ በሆነ መንገድ አድልኦ እንዲፈጠር ማድረጉን በመግለጫው አመላክቷል፡፡

ዳኞች በሕገ መንግሥቱ ያላቸውን የእኩልነት መብት የሚጥስና የሚያገል፣ ዜጎች በሕግ አግባብ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባልተሾመ ዳኛ የሕይወት፣ የነፃነትና የንብረት ክርክሮችን እንዲያዩ ማድረግ ዜጎች ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን ያለ ሕጋዊ ሥርዓት እንዲያጡ የሚያደርግ መሆኑን፣ እንዲሁም ዳኞች በአስተዳደሩ ይሁንታ እንዲመረጡ ማድረጉ አስተዳደሩ የፈለገውን ሰው/ዳኛ የሚያደርግበትና በደረጃ የሚያሳድግበት ሥርዓት የመፍጠርና ይህም ሥልጣንን ባልተገባ መንገድ ለመገልገል በር እንዲከፈት የሚያደርግ መሆኑን፣ ማንኛውም መሥፈርቱን የሚያሟላ ዳኛ በውድድር እንዲሳተፍ በማድረግ የተሻለ ዕውቀትና ልምድ ያላቸው ዳኞች እንዲሾሙ የፈጠረውን ዕድል የሚጥስ ሰለሆነ እንዲታረም ሲል አሳስቧል፡፡

ጉባዔው ዳኞችን ለመሾም ሥልጣን የሌለው ስለመሆኑ ጠቁሞ፣ በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55(13) እና 81(2) መሠረት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች ለመሾም ሥልጣን የተሰጠው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሆኑን፣ ጉባዔው በምልመላ መሥፈርቱ መሠረት መልምሎ ዕጩዎችን ለምክር ቤቱ ከማቅረብ ያለፈ የመሾም ሥልጣን እንዳልተሰጠውም አብራርቷል፡፡

በዚህም ሒደት ዳኞች ያለ ውድድርና ያለ መሥፈርት በጉባዔው መመረጣቸው አንድ አስተዳደራዊ ውሳኔ ሲወሰን ሊከተል የሚገባውን ሒደት፣ የምክንያታዊነት መርህንና የግልጽነትን አሠራር የሚጥስ ከመሆኑም በላይ በአመራሩ (አስተዳደሩ) የማይታወቁ በክልሎች ያሉ ጠንካራ ዳኞችን ያለ ምክንያት ያገለለ አሠራር መሆኑንም ማኅበሩ አስታውቋል፡፡

የአማራ ክልል ዳኞች ማኅበር ያቀረበውን ቅሬታ በሚመለከት ሪፖርተር ማብራሪያ ለማግኘት የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጽሕፈት ቤት ኃላፊን በስልክ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የጉባዔ ሰብሳቢንና ምክትል ሰብሳቢን ለማግኘት የተደረገው ሙከራ ባለመሳካቱ፣ አጭር የጽሑፍ መልዕክት የተሳካ ቢሆንም ምላሽ ለማግኘት አልተቻለም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ገጣሚ በላይ በቀለ ወያ ታፍኖ ከተወሰደ በኋላ የት እንደቆየ እንደማያውቅ ተናገረ!!

2 Comments

  1. ጎበዝ ይሄ ሪፖርተር ማለት ባለፈው የትግሬዎችን ግፍ የትግሬዎች ችሮታ እያደረገ ነገር እያዛባ አገር ሲያምስ የነበረ ጋዜጣ አልነበረም እንዴ ስለ ኢትዮጵያ ትቶ ስለ ትግሬዎች ቢነግረን ምናለበት? አሁንም ትግሬያዊ ስራውን ቀጥሎበታል ማለት ነው? እኛን ትቶ ፈንግል ነው ፈንቅል የሚሉትን የትግሬ ድርጅት መሪ የፊት ገጹ ላይ ቢያወጣው፡፡ ሚኪ ነው መሰል ስሙ የጥልያን የሆነ ነገር ሁሉ ህልማቸው ነው፤ ለነገሩ ልጁ ጥልያንነት አያጣዉም፡፡ መጥኔ

  2. Great! Great! Great!

    At least የአማራ ክልል ዳኞች ማኅበር is standing against የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ (herein after simply ጉባዔ) on this issue. If the people assigned by the ጉባዔ hear and pass binding decisions, they are sitting as judges without being appointed by the House of People’s Represenatives following the relevant articles of the constitution. What’s strange is, the ጉባዔ is supposed to be an example of rule of law in the country, but it obviously is behaving as an outlaw institution.

    Keep the good job የአማራ ክልል ዳኞች ማኅበር ! Recently, we’ve read that you sent a letter to the prime minister (PM) demanding that he withdraw his outlandish claim that judges in the country are thieves. He has not withdrawn his claim or substantiated it with proof. As people learned in the law, you can charge him for that claim unless he withdraws it in good time. Summon him to Baher Dar to defend himself and if he does not appear slam him with fine and /or jail term for contempt of court and sentence him in his absence.. If there is a sentence hanging over his head, he won’t come to Amhara region. And that’s fine.

    By the way, is የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ out for revenge against የአማራ ክልል ዳኞች ማኅበር because it demanded that the PM withdraw his statement in which he presented judges as thives? Is the ጉባዔ of opinion that the PM has not undermined the judiciary in the country by blaming judges for thievery without showing any proof? Obviously the ጉባዔ is defending its boss by punishing Amhara judges by assining judges without constitutional process. By doing this the ጉባዔ has tried to weaken the judiciary more that its boss did.

    Judicial independence is a serious problem in the country. The executive has controlled and still is controlling the judiciary.የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ is simply reinforcing this reality. Assigning unappointed loyal judges who are most likely ffriendly with the ጉባዔ and the executive to the bench contrary to constitutional process means judicial independence is pushed down the tubes. At least የአማራ ክልል ዳኞች ማኅበር is showing signs to stand for the independence of the judiciary.

    Indpendence of the judiciary does not emerge because the constitution and other laws say so. It’s judges themselves who put into practice what is provided in the law.Brief! Independence of judiary essentially means independence of judes. If judges do not stand for their indepndence as provided in the law, who will do it for them? NOBODY. It is the same in every country. Independence of the judiciary is realized where judges stand for their rights and the law. Judicial independence does not exist where judges are bed fellows with the executive and the bureaucrcy. Try it and you will see the result. You will as well be remembered as pioneer in the struggle for judicial independence.

    So, stand against የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ which is part of the executive.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share