ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፓሊስ ተደበደበ!! – ታሪኩ ደሳለኝ (የተመስገን ወንድም)

June 3, 2022
photo5821312649554672610.jpgዛሬ ግንቦት 25/2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ፖሊስ በተለምዶ 3ተኛ ተመስገንን ለመጠየቅ ፖሊስ ጣቢያ ተገኝቼ ነበር::
በዚህ እስር ቤት በታሳሪና በጠያቂ መካከል በሁለት ሾቦ የተጋረደ ከ10 ሜትር የሚበልጥ ርቀት አለ::
በታሳሪና በጣያቂ መካከል ባለው ርቀት የተነሳ፣ ንግግር ለማድረግ እጅግ አዳጋች ነው። አጠቃላይ ነገሩ መጯጯህ ነው:: ተመስገን ከዚህ በፊት በእስር ቤት እያለ ባጋጠመው በጆሮ ህምም ምክኒያት በዚህ ግር ግር ውስጥ ጆሮው ለመስማት ያዳግተዋል::
ይሄ በመሆኑ ተመስገን ለፖሊሶቹ “ትንሽ ቀረብ ብሎ ቢያወራኝ ” ሲለው ፖሊሱ በእጁ የማመናጨቅ ምልክት አሳየው፣ ተመስገንም ድጋሜ ለማስረዳት ሲሞክር አንዱ ፖሊስ ከነበረበት ከጠያቂ ቦታ ሌላው ፓሊስ ከስረኛቹ መቆሚያ ደረጃ ላይ በመውረድ ለሁለት ተመስገንን አብረውት ከቆሙት እስረኞች መካከል ጎትተው በማውጣት በቦክስ፣ በጫማ ጥፊ ለሁለት ደብድበውታል።
ይህ ሲሆን የሌሎች እስረኛ ጠያቂ ቤተሰቦችና እስረኞችም አይተዋል። ድብደባውን እየፈፀሙ ወደ እስረኛ ክፍል ሳይሆን ወደ ሌላ ቦታ ይዘውት ሄደዋል::
ከቆይታ በኃላ በቢሮ ውስጥ ተመስገንን ስናገኘው፣ የግራ ዓይኑ ስር አብጦ የለበሰው ቲ-ሸርት ተቀዶ አግኝተነዋል::
አሁን ከእስር ቤቱ አስወጥተውኝ በሩ ላይ እገኛለሁ::
የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና ሚዲያዎች ጉዳዮን እንድታውቁልን፣ ማጣራት አድርጋችሁ ለሕዝብና ለሚመለከተው አካል እንድታደርሱልን።
Tariku Desalegn Miki ( ታሪኩ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ካወጣው የተወሰደ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Redwan
Previous Story

አቶ ሬድዋን ሁሴን አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ተክተው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ

Abiy 90
Next Story

ምክር  –  ራሳችንን አናቁስል አንዱ ዓለም ተፈራ

Latest from Blog

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ | ስለአማራ ክልል ከነዋሪዎች የተሰማው | አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል” | “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል”| “እጅ ከመስጠት ውጭ አማራጭ አይኖረንም” ፊ/ማ “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

ከውጭ በተላከ ገንዘብ ሀብት አፍርቶ የተላከበትን ደረሰኝ ያላቀረበ ንብረቱ እንዲወረስ የሚደነግግ አዋጅ ቀረበ

ዮሐንስ አንበርብር በጥፋተኝነት ላይ ያልተመሠረተ ንብረት የመውረስ ድንጋጌም በአዋጁ ተካቷል አዋጁ የሚፀድቅ ከሆነ 10 ዓመት ወደኃላ ተመልሶ ተፈጻሚ ይሆናል ከውጭ በተላከ ገንዘብ ሀብት አፍርቶ የተላከበትን ደረሰኝ ያላቀረበ ሰው ወይም ሊታወቅ ከሚችል ገቢው በላይ ሀብት አፍርቶ ምንጩ ሕጋዊ መሆኑን ማረጋገጥ ያልቻለ ሰው፣ ንብረት በመንግሥት እንዲወረስ የሚፈቅድ ድንጋጌ የያዘ
Go toTop