የአፍሪካ ቀንድ ጅኦ-ፖለቲካል ሽኩቻና ውልደተ ውክልና ጦርነት!!! የውኃውን ቁልፉ እንጫነው? የትኛውን ፈረስ እንጫነው? ፋኖ በአማራ ክልል በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ ይጥራ!!!

ኢት-ኢኮኖሚ/ET- ECONOMY
(ክፍል ሁለት)
/ ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ

በአፍሪካ ቀንድ አገሮች የኃይል ሚዛን አሰላለፍ  ዳሰሳ   

{5} የሦስትዬሽ ስምምነት

የዓለም ፖለቲካ ሁኔታ ተለዋውጦል፣ የሦስትዬሽ ስምምነት በኢትዮጵያ በኤርትራና ሱማሌያ አገሮች መኃል ጉታ-ገጠም የሥነ- ምድር አንድነት፣ የታሪክ ትርክት፣ ባህል፣ ሃይማኖት እንዲሁም የጋራ ጥቅምና በእኩልነት በመከባበር፣በነፃነት፣ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት  ያካተተ ስምምነት ነው፡፡ የሦስቱ አገሮች ስምምነት በፖለቲካ፣ በምጣኔ ኃብት፣ በማህበራዊ ጉዳይ፣ በባህልና የድህንነት ጥበቃ ህብረት ላይ ያተኮረ ነው፡፡ የቀጠናውን ሠላም፣ ደህንነትና የጋራ ከፍተኛ ኮሚቴ አቆቁመዋል፡፡ የሦስትዬሽ ስምምነት በአብይ አህመድ፣ መሃመድ አብዱላሂ መሃመድና ኢሳያስ አፈወርቂ በአስመራ ከተማ ተፈፅሞል፡፡  ……………………………………………………………………………………(6)

The Tripartite Agreement, formally titled the Joint Declaration on Comprehensive Cooperation Between Ethiopia, Somalia and Eritrea, states that given their “close ties of geography, history, culture and religion as well as vital common interests” and “respecting each other’s independence, sovereignty, and territorial integrity”, the three countries agree to cooperate and “build close political, economic, social, cultural and security ties”, coordinate to “promote regional peace and security” and establish a Joint High-Level Committee to coordinate the implementation. The agreement was signed in Asmara on 5 September 2018 by Abiy Ahmed, prime minister of Ethiopia, Mohamed Abdullahi Mohamed (Farmaajo), president of Somalia, and Isaias Afwerki, president of Eritrea.[1]

የሱማሌ አዲሱ ተመራጭ ፕሬዜዳንት ሃሰን ሼክ መሃመድ ገና ከመመረጣቸው የአሜሪካን ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንን  የአሜሪካን ወታደሮች በአፍሪካ ቀንድ አገሮች በሱማሌያ ጦራቸውን እንደሚያሰፍሩና የአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያለውን በሱማሌያ መሠረቱን የጣለው አል ሻባብ ሽብርተኛ ቡድን በጋራ ለመምታት እንደሚስማሙ ከወዲሁ አገራቸውን በርግደው የጦር ሠፈር ለመስጠት ተንበርክከው ለምነዋል፡፡ አሜሪካ በኢትዮጵያ ፣ በኤርትራና ሱማልያ የተመሰረተውን የሦስትዬሸ ስምምነት በማፍረስ ሱማልያን ዳግም ለመቆጣጠር ችላለች፡፡ አሜሪካ በሱማልያ የሚገኘውን የተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ኃይል በመጠቀም ሕወሓትን  ለመርዳት ዳግም እድል አግኝታለች፡፡ አሜሪካ ለአዲሱ ሱማልያ መንግሥት የውጭ ብድር እዳ የእፎይታ ጊዜ እንድታገኝ፣ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ እንዲጠነክር ለመርዳት፣ የስብዓዊ ረድዔት ድጋፍ በርሃብ ለተጠቁ ሚሊዮን ሱማሌያውያን ለማድረስ እንደሚረዱ ቃል ገብተዋል፡፡

 አንድ ለእናቱ ዳዊት ወልደጊዬርጊስ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ቃሉን ያሰማል ‹‹አንዳንድ አገሮች ኢትዮጵያን ምስቅልቅሎን ለማውጣት የኃይማኖት ግጭት በመጫር የተወሳሰበውን የሃገሪቱን ችግር የብሄር ብሄረሰብ ጉዳይ በማስነሳት ይበልጥ ማጦዝና የራሳቸውን ፍላጎት መጫን ይሻሉ፡፡ በዚህ የፖለቲካ አሻጥርና የደህንነትና የፀጥታ ስጋት ሠላማዊ ህይወታቸውን መኖር ያልቻሉ በኢትዮጵያ ድንበርና ወሰን አካባቢ ያሉ እልፍ ዜጎች ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉር ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር የሚሽከረከርባት ሃገር ስትሆን፣ ሽምቅ ተዋጊዎች የፈሉባት የጦር መሣሪያ የታጠቀች ሃገር ሆናለች፡፡ አነስተኛ ህገወጥ የጦር መሣሪያ አዘዋዋሪዎች እንደ አሸን ፈልተዋል፣ እልፍ አእላፍ መሳሪያዎች በየቀኑ በድንበር በኩል ይተላለፋል፡፡  የእስላሚክ ስቴት (ኣይኤስ) በሱማሌ ድንበር በኩል የሚፈፅመውን ተልዕኮ በግልፅ አሳውቆል፡፡ በውጭ ኃይሎች የሚራገበውና የሚቆሰቆሰው የብሔርና የኃይማኖት አክራሪነት የብዙ ሰዎች ህይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት አስከትሎል፡፡ የኢትዮጵያን የዘመናት የተቆጠረ ሥልጣኔና አብሮ የመኖር የዳበረ ህብረ ብሄራዊ ባህል፣ እምነት፣ ቌንቌና ባህላዊ ትወፊት ያላት ሃገር ናት፣ በብዙ አፍሪካ አገሮችና መካከለኛው ምስራቅና ሰሜን አፍሪካ (ሊቢያ፣ ሲሪያ፣ ኢራቅ፣ የመን፣ ሱዳን፣ ሱማሌ፣ ሊባኖስ፣ ማሊ፣ ናይጀሪያ፣ ናይጀር፣ መካከለኛው አፍሪካ ሪፓብሊክ፣ወዘተ፣) ›› “Some countries are intent to destabilize Ethiopia along religious lines and complicate the already complex ethnic fractures to promote their own interests. Because of this wanton conspiracy and the security challenge it is posing to the survival of every Ethiopian living within its borders, Ethiopia has now become the most armed country in Africa. The small arms traffickers have never been as busy as tons of armaments cross over the borders on a daily basis. The Islamic State (IS) has already declared its intentions publicly from the borders of Somalia.  Such externally instigated ethnic and religious radicalization have left death and destructions to age old civilizations of tolerance amongst people belonging to diverse practices of religion, language and culture in many parts of Africa and the Middle East and North Africa (Libya, Syria, Iraq, Yemen, Sudan, Somalia, Lebanon, Mali, Nigeria, Niger, Central African Republic, etc.)” DWG

ተጨማሪ ያንብቡ:  መተቻቸታችን ለመማማር ቢሆን ኖሮ የት በደረስን ነበር!

{6} የልዕለ ኃያ የራሽያ መንግሥትና ሻብያ፡- የራሽያ መንግሥትና የኤርትራ መንግሥት ጋር የደረሱበት ሥምምነት መሠረት የቀይ ባህር ጂኦ-ፖለቲካ ቅኝት በራሽያ ቁጥጥር ስር የመውደቁ የራሽያ የጦር ሠፈር ምስረታ አሜሪካንና የአውሮፓ ህብረት ሃገሮች የኔቶ ጦርን አስቆጥቶል፡፡ ኢሳያስ አፈወርቂ ይህን ያልተጠበቀ ውሳኔ መወሰን ልዕለ ኃያሎቹን በእራሳቸው ዛቢያ ላይ መዞራቸውን አቆርጠው በኤርትራ ዛቢያ ላይ  እንዲዞሩ ተዳርገዋል፡፡   የቀይ ባህሩ ቆጥኝ ኢሳያስ አፈወርቂ ከስታሊን፣ ክሩቼቭ እስከ ብላድሜር ፑቲን ዘመን ድረስ የሳብየት ህብረትን ፖለቲካ አላምጠው የዋጡ በልጅነታቸው አፍቃሪ ኮምኒስት እንደነበሩና የግራ ፖለቲካን የኃይል አሳለፍ በእድሜቸው አቀላጥፈው ማወቃቸውን ልእለ ኃያሎቹ ሃገራት የዘነጉት ይመስላል፡፡ እድሜ ጠገቡ ኢሳያስ አፈወርቂ ከአሜሪካ ፕሬዜዳንቶች ከአይዘናህውር ኒክሰን እስከ ትራምፕና ባይደን የምዕራቡን ፖለቲካ እንደመተሬ ጠትተው ያሻራቸው ጥንት በፀረ ቅኝ ግዛት ዘመንና በፀረ- ኢምፔሪያሊስት ትግል የእድሜቸውን ሠላሳና አርባ አመታት የጉርምስና ጊዜቸውን በጫካ ማሳለፋቸው የምዕራቡን ፖለቲካና የኃይል ሚዛን ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ እናታቸውን እስከሚሸጡ ድረስ እንደሚዘቅጡ አሳምረው ያውቃሉ፡፡  ለዚህ ነው ኢሳያስ ስልጣን እንደያዙ መንግስታዊ ያልሆኑ የረድኤትድርጅቶች  (ኤንጂኦ) በሙሉ ከኤርትራ ምድር  የእህል አቆማዳቸውን እያራገፉ ያስወጡት፣ ከአፍሪካ አህጉር እህል የማይሠፈርላት ሃገር ብትኖር ኤርትራ ናት፡፡ የአህጉረ አፍሪካ እህል የሚሠፈርላቸው መንግስታት ህዝባቸውን ከርሃብ ቸነፈር፣ ከበሽታና ከስደት ማውጣት አልቻሉም፡፡ ምዕራባዊያን ሀገሮች የአፍሪካን አሀጉር በጥገኝነት ሱስ አደንዝዘው እየገዙ የህዝቡን በራስ የመተማመን ችሎታ በመስለብ እርዳታ ጠባቂ እንዲሆን ፈርደውበታል፡፡  የባህረ ነጋሹ ኢሳያስ አፈወርቂ በተደጋጋሚ በአሜሪካ መንግስት የኢኮኖሚ መአቀብ ላለፉት ሦስት አስርት ቢጣልባቸውም ያልተንበረከኩና ያለ ህገመንግሥትና ያለ ዴሞክራሲ፣ ያለ ምርጫ ሃገር የሚመሩ በእነዚህ እሴቶች ላይ የሚቀልዱ ምዕራባዊ አገሮች በአገራቸው ውስጥ የሌለ ዴሞክራሲን በሦስተኛ ዓለም ላይ የተተረጎመ ዴሞክራሲ፣ ምርጫና ህገመንግስት ሊጭኑበት ይሻሉ፣ ካራ በአንገቴ ይሄ ባልት በኤርትራ ምድር አይደረግም በማለት ተፋካካሪዎቻቸውን እየጨፈላለቁ ይገዛሉ፡፡ የመለስና የአብይ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ፣ ምርጫና ህገመንግሥት ከህዝብ እልቂት፣ ከብሄር ጦርነትና የኃይማኖት ግጭት ሌላ፣ የደም ዝናብ ከማዝነብ ሌላ ምን አተረፈ ብለው በየቃለ-መጠይቃቸው ይገልፃሉ፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአኖሌ ሃውልት ፖለቲከኞችንና ምሁራንን እያወዛገበ ነው

{7} ልዕለ ኃያ የአሜሪካ መንግሥትና ህወሓት  የአሜሪካ መንግሥት፣ የኤርትራ መንግሥት ከራሽያ ጋር ማበር በመቃብሬ ላይ ይሆናል፣ በቀይ ባህር ቀልድ የለም በማለት ልዩ ልዩ የፖለቲካ ሴራ በመንደፍ ላይ ይገኛሉ፡፡የአሜሪካ አንዱና ዋንኛው ሴራ የኢሳያስ አፈወርቂን አንባገነን መንግስት ከውስጥ ለማስገልበጥ የኤርትራ ተቃዋሚዎች በመርዳት የስርአት ለውጥ ለማምጣት ወይም ኢሳያስን ማስገልበጥ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ የአሜሪካ ሁለተኛው ሴራ በኢትዮጵያና ትግራይ ህወሓት በሚካሄደው ሁለተኛ አመቱን ለመያዝ አምስት ወራት የመቀረውን ህዝባዊ ጦርነት አቅጣጫ  ወደ ባህረ-ነጋሽ በማድረግ የኢሳያስን መንግስት መገልበጥና አዲስ ቅምጥ መንግሥት መመሥረት  ላይ ያተኮረ የጦርነት ስልት ነው፡፡ የአሜሪካ ስስተኛው የኢሳያስ አፈወርቂን መንግስት ለመደምሰስ የዶክተር አብይ አህመድ መንግሥት ጦሩን ኤርትራ ላይ ከወያኔ ጋር በማቀናጀት ጦሩን እንዲሰብቅ፣ ድሮዎኑን እንዲያዘንብ፣ መድፉን እዲያስጎራ፣ ታንኮቹን ላንቃ ወደ ባህረ ነጋሽ እዲያዞር በመድረግ ከአሜሪካ ለብልፅግና መንግሥት የሚደረገውን የኢኮኖሚ ድጋፍ፣ የአስራ ሦስት ቢሊዮን ዶላር ብድርና እርዳታ ብሎም የብድር እፎይታ እንድታገኝ ማድረግ ይገኝበታል፡፡ ከዚህም በላይ በአሜሪካ መንግሥት ባወጣው H-R-6600 እና S-3199 ረቂቅ ህግጎች በሰሜኑ ጦርነት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የተፈፀሙ የስብዓዊ መብት ጥስት፣ የጦር ወንጀልና የዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠያቂዎቹን የኢትዮጵያ  ባለሥልጣኖችን በነፃና ገለልተኛ አካላት በሄግ ለፍርድ መቅረባቸው ለመሠረዝ የአሜሪካ ምንግስት ማማለያ አቅርበዋል፡፡ ዶክተር አብይ አህመድ ‹‹ከዚህ በኃላ መሞት የሚፈልግ ኢትዮጵያዊ ለቀይ ባህር ይሙት›› በማለት ፍንጭ የሰጡበት ቀጣይ የህዝብ እልቂት በኢትዮጵያና በኤርትራ ሊሆን እንደሚችል አዲሱ የፖለቲካ ሴራ ይጠቁማል፡፡ አብይ አህመድ የቀይ ባህር፣ አስመራ፣ ምፅዋና አሰብ ግዛታችሁ በአንተ ጊዜ ሊመለስ ይገባል፡፡ ራሽያ የቀድሞ ግዛቶን ዩክሬንን ስትወር፣ ስለምን አንተ የቀድሞ ግዛትህን አታስመልስም የሚል ምክር ባይደን በቀጭኑ ሽቦ ሹክ ብለውታል፡፡ ህወሓትም የአማራ ክልልን መሬት (ወልቃይት፣ ሁመራ፣ ራያ፣ ወዘተ) የሱዳን ኮሪደር እና የአሰብ ወደብ ለባህር መውጫ ከኤርትራ ቅርጫ የድርሻውን እንደሚያገኝ ተስማምቶል፡፡ ለዚህም የትግራይ መከላከያ ሠራዊት ግማሽ ሚሊዮን የትግራይ ወጣቶችን ለመገበርና የሻብያ ለመውረር  የክተት አዋጅ በመላ ትግራይ አውጀዋል፡፡ በሌላ በኩል የአሜሪካ የባህር ኃይል የጦር መርከብ ኢትዮጵያንና ኤርትራን እንዲደበድብና የስብዓዊ ረድኤት እህል ወደ ትግራይ እንዲገባ ማድረግ ይቻላል በማለት አንድ የአሜሪካ የፓርላማ አባል ወደፊት ሊተገበር የሚችል ወረራ ለመፈፀም ዝግጅት እንዳለ ያስጠረጥራል፡፡

{8} ፋኖ፣ የአማራ ልዩ ኃይልና ሻብያ፡

አዲሱ የኦህዴድ ብልፅግና መንግሥት ከህወሓት ጋር በማበር በአማራ ላይ ጥቃት ማድረስ የፖለቲካ ሴራ በመፈፀም ላይ ይገኛሉ፡፡ ‹‹ህወሓት በአማራ ና አፋር ክልሎች ላይ የፈጸመውን ወንጀልና የስብዓዊና ቁሳዊ  ውድመት በተመለከተ የተባበሩት መንግሥታት፣ ሂውማን ራይት ዋችና፣ አምኒስቲ ኢንተርናሽናል በአማራ ህዝብ ላይ የደረሰውን የዘር ፍጅትና የጦር ወንጀል ከጉዳያቸውም አልጣፉትም፡፡ ለዓለም አቀፍ ህብረተሰብ የአማራ ህዝብን ፍጅት የክልሉን ሁኔታ በገለልተኛ ተቆም እውነቱ እንዲጣራ መጠየቅና ማስረዳት የጊዜው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡››

“The death and destruction of the Amhara people continue unabated, as these two organizations refuse to dedicate a fraction of their vast resources to look into the requests sent on behalf of the victims of geocode and crimes against humanity. Our requests to get the opportunity to share critical evidence and testimonies with the United Nations, Human Rights Watch and Amnesty International, have not even been acknowledged.  It is time to begin a vigorous campaign to spread the truth and demand actions from the international community and make it aware of the regional and global consequences of not doing so.” DWG

ፋኖ ሦስተኛ ተገዳዳረ ኃይል ሆኖ፣ በህቡዕ እየተደራጀ ፣ በአንድ መዐከል እዝ ስር ተሰባስቦ ለመስራት ቃል ገብቶ በመታገል ላይ ይገኛል፡፡ በፋኖ የአማራ ልዩ ኃይል ላይ የብልፅግና መንግሥት የሚፈፅመው ግድያ፣ አፈና፣ እስራት  ታሪክ ይቅር የማይለው ወራዳ ድርጊትን ተቆቁሞ መውጣቱ አይቀሬ ነው፡፡ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ብልፅግና  ከሃገር መከላከያ ሠራዊት የተሠናበቱ አባላቶችና የአማራ ልዩ ኃይል፣ መደበኛ ልዩ ፖሊስ ፋኖን ይቀላቀላሉ በሚል ፍራቻ  እየታሠሩ ይገኛሉ፡፡ የአማራ ክልል ስውር አዋጅ ፋኖን  ትጥቅ ማስፈታት ተጠናክሮ ቀጥሎል፡፡ የፋኖ የአማራ ልዩ ኃይል፣ አዴፓ ብልፅግና የአማራ ክልል መንግሥት በማስወገድ ‹‹ጊዜያዊ ህዝባዊ የሽግግር መንግሥት›› በመመሥረት እራሱን በእራሱ ማስተዳደር ይኖርበታል፡፡ የትግራይም ህዝብ ወያኔን አስወግዶ፣ ሁሉም ክልሎች ጊዜያዊ ህዝባዊ ህዝባዊ የሽግግር መንግስት እስኪያቆቁሙና በህብረት የጋራ መንግሥት የሚመሠርቱትን ፍኖተ ካርታ ነድፎ ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የትዉልዱ ችግር ለቃሉ የሚታመን ማጣት /መጥፋት ብቻ ነዉ 

ፋኖ  ለህግ የበላይነት፣ ፍትህና ርትህ በሃገሪቱ እንዲሠፍን ማድረግ ዋነኛ ስራው በማድረግ ለአንድ ሰው ህይወት የመኖር መብት ለማረጋገጥና የሰው ህይወት  ያለፍርድ እንዳይጠፋ በማድረግና ተጠያቂነት ማስፈፀም ዋነኛ ሥራው ይሆናል፡፡ ፋኖ የትም መቼም ሰው የገደለ ሰውም ቢሆን፣ የሰው ልጅ ያለፍርድ አይገደልም መርሁ አድርጎ መስራት አለበት፡፡

ፋኖ ህወሓት ከአማራ ክልል ተጠራርጎ በሰላም እንዲወጣ  የአማራ ህዝብ ከወሎ ምድር የፈለቀውን የተከዜን ወንዝ በመገደብ ህወሓትን ለሠላም ለማንበርከክ ይችላል፣ ወንዙ ከተገደበ የተከዜ ሃይድሮ ፓወር ይቆረጣል፣ የውኃ እጥረት ምክንያት የትግራይ ህዝብ ህወሓትን ከሥልጣኑ እንዲያባርር ተፅዕኖ ያደርጋል፡፡

 

{9} ኦሮሙማ አህዴድ ብልፅግና የኢትዮጵያ መንግሥት የልዕለ ኃያሎች ምርጫ አማራጮች መምታታት

የኮነሬል አብይ መንግሥት አንዴ ከራሽያ አንዴ ከአሜሪካ እንደ ፔንዱለም መወዛወዝ አቆም የሌለው በመርህ ላይ የተመሠረተ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ፖሊሲ የሌለው መደዴ አድርጎታል፡፡ ኦህዴደ ብልፅግና  መርህ አልባነቱ አንዴ ከአሜሪካ አንዴ ከራሽያ እንዲወግን አድርጎታል፡፡ ከኤርትራም መንግሥት ጋር አንዴ ወዳጅ አንዴ ጠላት ሲሆን ተስተውሎል፡፡ በሃገር ውስጥ ያለውም ተለዋዋጭ አቆም አንዴ ህወሓት ጠላት አንዴ ወዳጅ በማድረግ፣ ፋኖን አንዴ ወዳጅና አንዴ ጠላት ሲያደርግ የሚታይ መርህ አልባ ሥርዓት ውላጅ መሆን ችሎል፡፡

ለውጡን በደማቸው ያመጡት የኦሮሞ ቄሮዎች እንደ አማራ ፋኖዎች ሰልጥነውና ታጥቀው የኦሮሞ ህዝብን መጠበቅ ሲገባቸው ቄሮዎች እንዳይደራጁና እንዳይታጠቁ በማድረግ የኦህዴድ ብልፅግናና የኦሮሞ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ  አሻጥር ፈፅሞል፡፡ የኦሮሞ ህዝብ በስብዓዊ ጋሻነት በኦነግ ሸኔ ተይዞ ለሞት፣ እስራትና ስደት ሲዳረግ ለውጡን ያመጣው ቆሮ የኦሮሞ ወጣት ህዝባዊ እንቢተኛነቱን ተደራጅቶ መቀጠል አለበት እንላለን፡፡

የኦፌኮ ለፋኖ የአማራ ልዩ ኃይል ተገዳደሪ የፖለቲካ ማርሽ ቀያሪ ሆኖ መውጣቱ መራራ ጉዲናና ጁሀር አህመድ፣ በቀለ ገርባን የፍርሃት ብርክ አሲዛቸዋል፡፡ ፋኖ ከኢሳያስ አፈወርቂ መንግስት  ድጋፍ እየተደረገለት  በማለት ይወነጅላሉ፡፡ ኦነግ ሸኔን ከኦህዴድ ብልጽግና ጋር ለማስታረቅና ተገዳሪ ኃይል ሆኖ እንዲወጣ ውስጥ ውስጡን ሊያስማሙ ይጥራሉ፡፡ ኦፌኮ በኦሮሚያ ክልል በኦሮሞ ህዝብ ላይ የመደርሰውን የህዝብ ጭፍጨፋ ትንፍሽ ብለው ግን አያውቁም፡፡  (የኦፌኮ በፋኖ ላይ ያወጡትን መግለጫን ልብ ይበሉ፡፡)

የቀድሞው  ግንቦት ሰባት የዛሬው ኢዜማ በሃገሪቱ የፖለቲካ አሰላለፍ የአደረ አፋሽ በመሆን፣ የፖለቲካ ተመልካች በመሆን በተግባር የፋኖ የአማራ ልዩ ኃይል ትጥቅ እንዲፈታ በኦህዴድ ብልጽግና በመደገፍ የአማራ ክልል ህዝብ ስቃይን በኢዜማ የውስጥ የስልጣን ሽኩቻ ላይ ተቸክለው ይገኛሉ፡፡ ኢዜማ ህዝብ የሠጠውን አደራ በልቶ ሃገሪቱ በሴራ ፖለቲካ ስትታነስ፣ ሰዎች ሲታፈኑ፣ ሲገደሉ፣ ሲሰደዱ እያዩ እንዳላየ በመሆን ታሪካዊ ቀይ ስህተት ለሥልጣናቸው ሲሉ ክህደት ፈፅመዋል፡፡ የጀነራል ተፈራ ማሞ፣ የመስከረም አበራ፣ የሰለሞን ሹምዬ በግፍ መተፈን የደርግን ቀይ ሽብርና ነጭ ሽብር እራሱን እየደገመ መሆኑን ከዘነጉት፣ ለእራሳቸው ነግ በኔ በሉ እንላለን፡፡ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ አብሪ ጥይት በአብይ አህመድ የግፍ አገዛዝ እንዳከተመ ካልተገነዘቡ ህዝባዊ እንቢተኛነቱና ህዝባዊ አመፁ በማድረግ የኦህዴድን አፈና ግድያ ማስቆም ይኖርባቸዋል፡፡ ፋኖ በቅርብ ጊዜ በአማራ ክልል ለሦስት ቀናት በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ  እንዲጠራ እናሳስባለን፡፡

 

በአማራ ክልል በቤት ውስጥ የመቀመጥ አመፅ በፋኖ ይጠራ!!!

ምንጭ

(6) Tripartite Agreement (Horn of Africa) – Wikipedia

(7) Seized ammunition (EBC)/borkena

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share