April 7, 2013
1 min read

ደደቢት ከአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውጭ ሆነ

(ዘ-ሐበሻ) በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ከሱዳኑ አል ሃሊ ሽንዲ ጋር የተጫወተው ደደቢት በድምር ውጤት ከውድድር ውጭ ሆነ። ደደቢት ሱዳን ላይ ባደረገው የመጀመሪያው ጨዋታ 1 ለ 0 የተሸነፈ ሲሆን ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ባደረገው የመልስ ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ ውጤት በመለያየት በድምር ውጤት 1 ለ 0 ተሸንፎ ከውድድሩ ውጭ ሊሆን ችሏል።
ደደቢት ወደ ተከታዩ ዙር ለማለፍ በሁለት የጎል ልዩነት ማሸነፍ ይጠበቅበት የነበረ ቢሆንም ውጤት ሳይቀናው ቀርቷል።
የደደቢት ክለብ አሰልጣኝ አብርሃም ተ/ሃይማኖት ከጨዋታው በፊት በሰጠው አስተያየት « ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ሁለት ለባዶ ማሸነፍ ይበቃናል። ተጋጣሚያችንን እንደተመለከትነው ያን ያህል ጠንካራና የሚያስፈራ አይደለም። በመጀመሪያው ጨዋታም ባዶ ለባዶ የመለያየት እድል ነበረን።ይሁንና በጨዋታው መጠናቀቂያ አካባቢ አንድ ግብ ተቆጥሮብናል። በሱዳኑ ጨዋታ የሠራነውን ስህተት አንደግመውም፡፡ በሰፊ ውጤት እንደምናሸንፍ እገምታለሁ » ብሎ ነበር።

Go toTop