[የሳዑዲ ጉዳይ] ዲፕሎማቱ የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ት/ቤትን ተቆጣጠሩ፤ ለተመዘበረው 1.7 ሚሊዮን ሪያል «ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ» ወላጆችን ባለዕዳ አደረጉ

ከኢትዮጵያ ሃገሬ ከሳዑዲ አረቢያ ጂዳ

ከ1500 በላይ በሆኑ ወላጆች በባለቤትነት እንደሚተዳደር የሚታወቀው በሪያድ አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት በዲፕሎማቱ ቁጥጠር ስር መዋሉን የሚገልጹ ምንጮች ለዛሬ ማርች 28 2014 በኤምባሲው ደብዳቤ የስብሰባ ጥሪ ተላልፎላቸው የነበሩ ወላጆች ባለመገኝታቸው የስብሰባው አዳራሽ ባዶ ሁኖ መዋሉን አክለው ገልጸዋል፡:

ንበረትነቱ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር እንደነበር የሚነገርለትን ት/ቤት ኤምባሲው ለመቆጣጠር እያደረገ ያለው ጥረት ከግልጥቀም የመነጨ መሆኑንን የሚናገሩ ውስጥ አውቂ ምንጮች ት/ቤቱን ከኮሚኒቲው በመነጠል ከወላጆች በሚመረጥ የቦርድ አስተዳደር ይመራል በሚል ሽፋን ላለፉት 5 አመታት በት/ቤቱ ጥሬ ገዝንዘብ ላይ ግልጽ የሆነ ምዝበራ መፈጸሙን ይናገራሉ። ይህን አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት ዲፕሎማቱ ልግል ጥቅማቸው ለማዋል ያልፈነቀሉት ድንጋይ ያልበጠሱት ቀጠል እንደሌለ የሚናገሩ ወገኖች ከዛሬ 7 ወር በፊት ለይስሙላ ህብረተሰቡ በቦርድ አባልነት ለመሳተፍ የሚያስችለውን ማስታወቂያ አውጥተን የሚቀርብ ሰው አጣን ለማለት የመወዳደሪያውን ማመዘኛ ዲግሪ እና ከዛ በላይ ከፍ በማድረግ ማንኛውም ወላጅ በቀላሉ ማቀረብ የማይችላችውን ተጨማሪ ድብዳቤዎች እንዲያቀርብ የሚጠይቅ መስፈርቶችን በማስቀመጥ ወላጆች ት/ቤታቸውን ለማስተዳደር እንዳይችሉ መደረጋቸውን ይገልጻሉ።

ይህ በዚህ እንዳለ ወላጆች ባላቸው አቀም እና የትምህርት ደረጃ አቋቁመው ለዘመናት ያለማንም ድጋፍ እና ረዳት በማስተዳደር ለዚህ ያበቁትን የልጆቻቸውን ዕውቀት መገብያ ማዕከል ኤምባሲው ለመንጠቅ በሪያድ የዲያስፖራው ሃላፊ እንደሆኑ የሚነገርላቸው አቶ ተመስገን ኡመርን በጓሮ በር አሾልኮ በመስገባት ቀደም ብለው ያዘጋጇቸውን ታማኝ አገልጋይ የቦርድ አባላት ስልጣን ካፀደቁ በሃላ ዛሬ ወላጆችን ለማደናገር በኤምባሲው ማህተም በተደገፈ ደብዳቤ ስብሰባ መጥራታቸው የዲፕሎማቱን አላውቂ ሳሚነት በግልጽ ያሳይል ተብሏል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ህብረት ለአገራችን ኢትዮጵያ የህልውና ዘመቻ ህብረት - ዘመቻ ህልውና

ዲፕሎማቱ በኤንባሲ ሽፋን ህገወጥ ተግባር በመፈጸም ላይ እንደሚገኙ የሚናገሩ ወገኖች 1500 በላይ የሆኑ ወላጆች በባለቤትነት እንደሚቆረቆሩለት የሚነገርለትን ት/ቤት ቁጥራቸው ከ 50 የማይበልጥ የት/ቤቱ ጉዳይ የማይመለክታቸውን ደጋፊዎቻቸውን ሰብስበው አዳራሽ በማስገባት «አይጥ በበላው ዳዎ እንዲሉ » ምንም የማያውቁትን ወላጆች የ 1.7 ሚሊዮን ሪያል ባለእዳ የሚያደርግ ሪፖርት በዲይስፖራው ሃላፊ አማካኝነት በማቅረብ ዲፕሎማቱ የመረጣቸውን ህገ ወጥ የቦርድ አማራር አባላት ህጋዊ ለማድረግ ከወላጆች ጀርባ ዛሬ የፈጸሙት ደባ በህግ ሊያስጠይቃቸው የሚገባ ብሄራዊ ወንጀል መሆኑን ገልጸዋል። ስብሰባው ላይ በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያው አምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ህሰን መገኘታቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል። በዚህ ዙሪያ የዲያስፖራውን ሃላፊ አቶ ተመስገን ዑመርን ለማነጋገር ያደርኩት ሙከራ አልተሳካም::

2 Comments

  1. Enante ye mahbere kidusan abalatina akrari naftegnoch sira fet hula. Be Alcohol nigd yemitetedaderu ina ye habeshochin Sim yemitatefu. Ahun demo bilachihu bilachihu be timihirt betachin metachihu. Iyandandish be mutawa balaslekimish Awlachew aydelehum. Ende diyakonu nebiyu sirak wede isir bet tigebiyalesh hulishim ye kees lij hula.

  2. « Awlachew »በሚል ስም ሽፋን ከዚህ በላይ በተጠቀሰው እውነታ ላይ አስተያየት ለመስጠት የሞከርከው ሰው ማንነትህን እና ስምህን እዚህ ድህረገጽ ላይ መጥቀስ ተገቢ ባይሆንም አንተ የሰጠህው አስተያየት ግን አንተ እከተለዋለህ ብለህ በማጭበርበሪያነት የምትጠቀምበትን የተከበረ ሃይማኖት የሚከተሉትን ወገኖች የሚወከል አለመሆኑ ስገልጽ አስተያየትህ ፍጹም ያነትን ዋልጌነት ቁልጭ አድርጎ ስለሚያመለክት ከዚህ በላይ የተወቀሱትን ዲፕሎማቶች ወክለህ ልተከራከርላቸው የሚያስችል የሞራል ብቀታ እንደሌለህ እና እንሱም እንደአነት አይነቱን ዋልጌ እርዳታ እንዳማይሹ መግለጽ ወዳለሁ ። መሃበር ቅዱሳን ቄስ ነብዩ ሲራክ ምናምን ብለህ ለመሳደብ የግድ ከዚህ በላይ የተጠቀሰውን ዜና ሽፋን ማድረግ ምን አመጣው ። እንደለመድከው በክርስትና እምነት ላይ ያለህን ጥላቻ መግለጽ ዳድቶህ ከሆነ እዚህ ክበር ባለው የሁሉም እምነት ተከታይ ወገኖች የሚስተናገዱበት የድምጽ አልባዎች ድምጽ በሆነው ገጽ ላይ ይህን የወረድ አስተያየት በዚህ መኩ አውላቸው ብሚል ስም ከምትሰጥ በግልጽ የተለመደውን ጽኝፈተኝነትህን በተለመደው ፌስ ቡክህ ላይ ብታናፋ ይሻለሃል ! ብቻ ከዚህ በላይ ባስቀመጥከው አስተያየት ላይ ምላሽ መስጠት ተግቢ መስሎ ስላልታየኝ አፍንጫህ ስር ያሉትን የኮሚኒቲውን ማህበረሰብ ጠይቀህ ትረዳ ዘንድ መክሬን ቸርሃለው ። ከዚህ ባሻገር ሃይማኖትን መስረት አድርገህ ከእንግዲህ ለመናገር ከቃጣህ ማነትህን በግልጽ ገልጬ እዚህ ገጽ ላይ ስለናተ ማለት የሚገቡኝን እወናትዎች ለማስቀመጥ ግድ ይለኛል ! በለፈለፉ በአፍ ይጠፉ ! አይደል የሚባለው ከብዙሃኑ ወገኖቻችን ሃይማኖት ላይ እጅህን አንሳ !

Comments are closed.

Share