እሳተ ነበልባሉ የጫካው አንበሳ፣ ሀገር ብትጠራው ምቾት ይቅር ብሎ ፎክሮ ተነሳ

የእናት ሀገር ፍቅር፣ ክብርና ምስጢር ሲገባ ልሙትላት፣ ልሰዋላት ያስብላል። ከሠንደቋ በፊት ልውደቅ፣ ከመከራዋ በፊት ልቅደም፣ የግፏን ፅዋ ልጠጣ፣ ቀድሜሽ ልውጣ፣ ጠላትሽን ድል አድርጌልሽ ልምጣ ያሰኛል። እናት ሀገር ከምቾትም ከምኞትም በላይ ናት። እርሷን የሚተካ፣ በእርሷም ልክ የሚለካ የለም። ሲወዷት ሕይወት ይሰጧታል፤ አጥንት ይከሰክሱላታል፤ ደም ያፈሱላታል፤ መከራ ይቀበሉላታል፤ በተቀበሉት መከራ ተሻግራ አሸናፊ ስትሆን ደግሞ ይኮሩባታል። ኢትዮጵያ ዜማ ናት፤ በጋራ የምናዜማት፤ ቅኔ ናት፤ በጥልቀት የምንቀኛት፤ ሰምና ወርቋን የምንፈልግላት፤ ምስጢሯን የምናከብርላት፣ የምንከብርባት፣ ኢትዮጵያ ጋሻ ናት፤ በጋራ የምንመካባት፤ ጌጥ ናት የምንዋብባት፤ ዙፋን ናት በጋራ የምንነግሥባት፤ ቅጠሎቿ የማይደርቁ፣ የማይጠወልጉ ጥላ ናት፤ የምንጠለልባት፡፡

ኢትዮጵያ ተስፋ ናት፤ ሁሉን ነገር የምናይባት፡፡ ኢትዮጵያ ከፍታ ናት፤ ማንም የማይደርስባት፡፡ ኢትዮጵያ ብርሃን ናት፤ የጨለማ ዘመን የሚገፈፍባት፡፡ ኢትዮጵያ መድኃኒት ናት፤ የሞት ፅልመት የሚርቅባት፡፡ ኢትዮጵያ ነፃነት ናት፤ የአሸናፊነት ማኅተም ያረፈባት፡፡ ኢትዮጵያ ቀደምት ናት፤ ሁሉም የተከተላት፡፡ ኢትዮጵያ ባለ ግርማ ናት፤ ሁሉም የሚያከብራት፤ የሚፈራት።

ለኢትዮጵያ ሲሉ ልጆቿ ሞትን መርጠዋል፤ ጥይትን ንቀዋል። ዓለምን ትተዋል፤ የተመቸ ሕይወታቸውን ረስተዋል። ለክብሯ በከፈሉት ዋጋ ኢትዮጵያም ፈተናዎችን ኹሉ አልፋ እንደተከበረች፣ እንደታፈረች ኖራለች። ዛሬም ልጆች የአባቶቻቸውን ጀግንነት ወርሰው፣ አሸናፊነታቸውን ተቀብለው ሀገራቸውን ከጠላት ለመከላከል እየተዋደቁ ነው ለክብሯና ለሉዓላዊነቷ፡፡

1970 .ም መጀመሪያ አካባቢ ነበር የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን የተቀላቀሉት። በዚያ መዘን የአሁኑ አሸባሪና ወራሪው የትግራይ ኃይልን ጨምሮ በርካታ ጠላቶቿ ኢትዮጵያን ለመውጋት አሰፍስፈው ነበር። እኒህ በልጅነት አዕምሮአቸው ሲመኙት የነበረውን ሙያ የተቀላቀሉት ወታደር ለሀገራቸው አያሌ አውደ ውጊያዎች ላይ ተሳትፈዋል፤ መቶ አለቃ ብርሃኑ ተረፈ፡፡ በኤርትራ በረሃዎች ለሰባት ዓመታት ተዋጉ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  Hiber Radio: አ. ግንቦት 7 ወያኔ ተገዶ በድርድር ስልጣን እለቃለሁ ካለ ድርድሩን እቀበላለሁ አለ - የሃብታሙ አያሌውን ልዩ ቃለምልልስ ይዘናል

1978 .ም ባሳዩት ጀግንነት የመቶ አለቅነት ማዕረግ ተሰጣቸው። በአስመራ በነበረው አራተኛ መድፈኛ ብርጌድ ውስጥ ዘጠነኛ ቢኤም አዛዥ ኾኑ። የግዳጅ አፈፃፀማቸው ላቅ እያለ መጣ። በርካታ ውጊያዎችን በድል ተወጡ። ጀግንታቸውን አስመሰከሩ። መንግሥት የሥልጠና ዕድል ሰጥቷቸው ወደ ሀገረ ኮሪያ አቀኑ። ከዚያም ወታደራዊ ሥልጠናቸውን በብቃት አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ። በ1981 .ም ስፓርታ የተባለውን ልዩ ሥልጠና ከሰጡት የጦር መኮንኖች አንደኛው ኾኑ።

ሽብርተኛው ትህነግ መራሹ ኢህአዴግ መንበረ ሥልጣኑን ሲቆናጠጥ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን እንደገና እንዲያዋቅሩ ከተመረጡት ሰዎች መካከል አንደኛው ኾነው ተመረጡ። ከመጀመሪያው ጀምሮ ክፋት የማይታጣበት ሽብርተኛው ትህነግ ጠንካራ የነበረውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አፍርሶ ራሱ በሚመቸው መልክ በራሱ ሰዎች አዋቀረ፡፡ የሽብርተኛው ትህነግ መሰሪነት ለመቶ አለቃ ብርሃኑ ተረፈ አልተዋጠላቸውም ነበር።

የሚዋቀረው ሠራዊት ሸፍጥ ያለበት መሆኑን አወቁ። አይተው ዝም አላሉም፤ “አይሆንም፤ አይደረግም” አሉ፡፡ ሽብርተኛው ትህነግም ኢትዮጵያ ተስፋ የጣለችባቸውን የጦር መኮንን ለእስር ዳረጋቸው። ከሥራም አባረራቸው። የጦር መኮንኑ በሚወዱት ሙያ ከዚያ በላይ መቀጠል ባይችሉም ከእስር ከተፈቱ በኋላ የሕይወትን መንገድ ቀይረው መጓዝ ጀመሩ።

ትምህርት ቤት ገብተው የጤና መኮንንነት አጠኑ፤ በሥነ አመጋገብ (ኒውትሪሽን) ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ያዙ። በዚያም ለረጅም ጊዜ አገልግለው ዛሬ ላይ በመሪነት እና አስተዳደር የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪ ናቸው። ትምህርታቸውን እያገባደዱ ያሉ እጩ ዶክተርም ናቸው። ትዳር መሥርተው ሁለት ልጆችንም አፍርተዋል። በአንድ ኮሌጅ ፕሬዝዳንትም ናቸው።

ከእኔ ጋር የተገናኘነው ያኔ ከሚወዱት የወታደርነት ሙያ የነጠላቸው ዛሬ ሀገር ለማፍረስ እየተጣጣረ ያለውን ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይል ለመፋለም ዳግም ውትድርናን ተቀላቅለው በወሎ ግንባር ነው። ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይልን ሴራ እና ክፋት የሚያውቁት የጦር መኮንኑ በወሎ ግንባር ሕዝባዊ ሠራዊት እየመሩ ነው ለዳግም ትግል ከዓመታት በኋላ ወደ ጦር ግንባር የተመለሱት።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በኮለምበስ ኦሃዮ የአማራ ተወላጆች ማህበር ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የተሰጠ ባለ 11 ነጥብ የአቋም መግለጫ

ወደ ዘመቻው እንድቀላቀል ጠየኩኝ ተፈቀደልኝ፤ ለዘመቻ ብቁ ለሆኑ ሰልጣኞች ስልጠና ሰጠሁ፤ ያሰለጠንኩት ሠራዊት ሲመለከተኝ ደስ አለውና የዘመቻው አዛዥ እርሱ ይሁን ብሎ ሾመኝ” ነው ያሉት። “አማራ ለህልውናው መዝመት አለበት” ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ዛሬም ላይ የምትኮራባቸው ስመ ጥር ጄኔራሎች በእርሳቸው ተገርተዋል፤ የወታደራዊ ሳይንስ ተምረዋል፤ ለዛሬ ማንነታቸው መሠረት ጥለዋል። እኒህ የጦር መኮንን ከረጅም ዓመታት በኋላ ወደ ሚወዱት ሙያ ሲመጡ ወኔያቸው አልቀነሰም። የጦር ስልታቸው አልደበዘዘም። መቶ አለቃ ብርሃኑ በእናት ሀገር ፍቅር እንደሞቁ ናቸው።

ጀግናው የተደላደለ ሕይወታቸውን ጥለው ለእናት ሀገር ልሙትላት፣ ከእርሷ በፊት ልቅደምላት ብለው ግንባር ገብተዋል።

የቀድሞ የኢትዮጵያ የጦር መኮንኖች የደርግ ሠራዊት በሚል ስም ለሀገራቸው የከፈሉት ዋጋ ዝቅ መደረጉ እንደሚያበሳጫቸው ነግረውኛል። በዚያ ዘመን ለኢትዮጵያ ለዳር ድንበሯ የቆሰለ ጀግና ሠራዊት እንደነበር ነው ያስታወሱት። አሁንም ጀግኖቹ የኢትዮጵያን ጠላቶች እየተፋለሙ ነው፡፡

መቶ አለቃ ብርሃኑ አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ኃይል በአጭር ቀናት ድባቅ ለመምታት መዘጋጀታቸውንም ገልጸዋል። ወታደር በሥነ ምግባር፣ በዓላማ እና ግብ እንደሚደራጅ ነው የገለጹት የጦር መኮንኑ፡፡ አሁን ሀገር ለመታደግ እየተመመ ያለው ሠራዊት በከፍተኛ እልህ፣ በራሱ ተነሳሽነት፣ ግንባታው በጥበብ የተሠራ መሆኑን መቶ አለቃ ብርሃኑ ተናግረዋል። ሠራዊቱ ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይልን መቅበር ብቻ ሳይሆን ለሌላም ድል መሰለፍ የሚችል ስለመሆኑም አስረድተዋል።

እንደ መቶ አለቃ ብርሃኑ ገለጻ ጠላት ጀሌ ነው፤ እስካሁን የመጣው በፕሮፓጋንዳ ነው፤ እሱን ማጥቃት በሚያስችል መልኩ እና የሚገባውን ቅጣት ለመስጠት ዝግጅት ተደርጓል፡፡ በቅንጅት በመሥራት በእርግጠኝነት በአጭር ቀናት ከዓላማችን እንደርሳለን ነው ያሉኝ። መቶ አለቃ ብርሃኑ “አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል እና ደጋፊዎቹ እጃቸው ይቆረጣል” ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከመንግሥት የሚጠበቅ ግልጽነትን እና ተጠያቂነትን በተመለከተ ከዓለም-አቀፋዊ የኢትዮጵያውያን ማሕበረ ሰብዓዊ ድርጅቶች የተሰጠ መግለጫ

እሳተ ነበልባሉ የጫካው አንበሳ፣

ሀገር ብትጠራው ምቾት ይቅር ብሎ ፎክሮ ተነሳ❞

ስፓርታው ኮማንዶ፣ እሳተ ነበልባሉ፣ የጫካው አንበሳ ከሞቀ ቤታቸው፣ ከተመቻቸ ሕይወታቸው ወጥተው ለእናት ሀገር ጥሪ ጦር እየመሩ ምሽግ ገብተዋል። ምቾት ይቅር ብለዋል። ሀገርና ክብር አስቀድመዋል።

ጀግናው በእልህ ተነስተዋል። ሠራዊታቸውንም በሚገባ አዘጋጅተዋል። “ሽፍታውን እንቀጣዋለን፤ እንቀብረዋለን” ነው ያሉት። የወገን ሠራዊት ጠንካራ እንደሆነ የተናገሩት የጦር መኮንኑ ከሕዝቡ ስንቅ ብቻ ነው የሚፈልገው፤ በወሬ አትሸበሩ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

አማራ ጫፍ እስከ ጫፍ መነሳት አለበት። እኛ ድል እናደርጋለን፤ ኹሉም የድሉ ተቋዳሽ ይሁን” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በታርቆ ክንዴ

ሕዳር 01/2014 .(አሚኮ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share