ላሟን ጠልተው ወተቷን ሥጡን የሚሉትን ፣ የትግራይ ህዝብ “ ይበቃል !

 “ ማለት እንዲችል ላሚቷን ለጊዜው ገለል ማድረግ ተገቢ ነው ።

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

10/10/2013 / ሊነጋጋ ሲል ይህንን ህልም አየሁ ህልሙንም ሰኔ 23 ፈታሁት መቼም ጊዮርጊሥ ተአምረኛ አይደል ? ህልሜን ፈታው በእለተ ቀኑ።

ህልሙ በጣም ሥለረበሸኝ ቀደም ሲል የተረጎምኩት ከቀድሞዎቹ መሪዎች በተለየ መንገድ አገርን ለመመራት እየሞከረ ያለው የአገራችን መሪ ለይ አደጋ ሊደርሥ ይችላል በሚል መንገድ ነበር ህልሜና ሥጋቴንም በወቅቱ እንደማሥጠንቀቂያ ለሚመለከተው በተገቢው ድረ ገፅ ይድረሥ ብዬ ልኬዋለሁ

ይድረሥ አይድረሥ ምን አውቃለሁ

መላኩን ልኬዋለሁ ማለቴ ግን አልቀረም

በወቅቱ ትክክለኛ የህልሜን ፍቺ ያገኘሁ መሥሎኝ ነበር አልነበረም ህልሜ በሐረግ በሐረግ የሚፈታ ነበር ምልክቱም በወጉ መጤን ነበረበት ወይ የኔ ነገር ከህልሜ በፊት በማታወቁት ህልም እንድትመራመሩ አደረኳችሁ አይደል ? ይቅርታ ህልሜን እንሆ

( እውነተኛ ህልም ነው ፈጠራ እንዳይመሥላችሁ )

/ ደብረ ፅዮን ሥዩም መሥፍን በነጭ ራቫ ፎር ወሥጥ ከፊትና ከሆላ ተቀምጠው መኪናቸውም ከነጭ ቪላ ፊት ለፊት ቆሞ አየሁ ገፃቸው ፈክቷል ።በጣም ያምራሉ ።አብሶ ስዩም መሥፍን በጣም ተውቧል ደብረፅዮን ደግሞ በጥቁር በተለመደው መነፅሩ አይኑ ተከልሏል። ሥዩም መሥፍን በታላቅ ዝምታ ውሥጥ ሲሆን ደብረፅዮን ባይናገርም ሰውነቱ ይንቀሳቀሳል

ደብረ ፅዮን ሽክ ብሎ እሥከ መነፅሩ ጋቢና በግርማ ሞገስ መቀመጡ ቢታየኝም ሹፊር ግን አይታየኝም በቁጥጥር ሥር ውለው ወደ ችሎት የሚወሰዱ ይመሥለኛል።ጠ/ አብይ አህመድ በሥፍራው ነበረ / አብይ እነሱ መኪና ውሥጥ እንዳሉ አረጋግጦ ወደ አጃቢና ጓዶቹ ዘንድ ይሄዳል እኔ ምን እግር እንደጣለኝ አላውቅም እነሱ ታሥረው ከወጡበት ነጭ ቪላ ውጪ ከመኪናቸው ፊት ለፊት አድፍጬ ህንፃውን ተደግፊ በፍርሃት በነደብረፅዮን አካባቢ ያለውን ወታደራዊ እንቅሥቃሴ እያየው ነው ወታደሮች ከቤቱ ወጪና ውሥጥ ይንቀሳቀሳሉ አንድ ወታደርን ደብረፅዮን በጥቅሻ ጠርቶት የኤትኤም ካርድ የመሰለ ቢጫ ነገር ደብቆ ይሰጠዋል የዚን ጊዜ እጅግ በመሥጋቴ እየጮኹ ወደነ / አብይ እሮጣለሁ ወዲያው ተኩሥ ይቀልጣል ብዙ ሰው ይሞታል ብዙ ወታደሮችም / አብይ ከአደጋው ለመከለል ዙርያውን ከበው አብዛኞቹ ተረባርበው ከጥፋቱ ይጋርዱታል ከአፍታ በኋላ በወታደሮች መሐል ሲንጓራደድ አየዋለሁ አብይ ይተርፋል በዛ ቀውጢ ሰዓት ቦንብ ቦንብ ብዬ እጮኸለሁ። እዛ የተገኘ የወታደሮቹ ሻንጣ ሳይቀር ይበረበራል በአንድ ሻንጣ ውሥጥም ድምፅ የሚያሰማ በሰዓት የሚፈነዳ ፈንጂ ይገኛል የፈንጂ ኤክሥፐርትም እንዲያወጣው ይታዛዛል

ተጨማሪ ያንብቡ:  በከንባታ ጠንባሮ ዞን ተቃውሞ ያነሱ ወገኖች ወደ አዲስ አበባ እና አርባ ምንጭ የሚወስደውን መንገድ ዘጉ

ለመሆኑ ነጭ ራቫ ፎር ነጭ ቪላ በምን ይመሰላል ? በጣም ማማር ፍቺው ምንድነው የሥዩም መሥፍን ዝምታ በሞት ይመሰል እንበል የደብረፅዮን እንቅሥቃሴ እና ቢጫ የኤቲ ኤም የምትመሥል ካርድ ምንድናት ? ( አለመሞቱን ያመለክታል ። ) ለምን በዛ ነጭ የተዋበ ህንፃ ግርግዳ ጥግ እኔ ተገኘው ? (ምናልባት ለዓመታትት በፃፍኳቸው የዛሬ ሰው የነገ ሬሣነታችንን በሚያሥገነዝቡ ፅሁፎቼ የወቅቱን የትግራይን ጉዳይ በማሥመልከት በፅሑፎቼ ውሥጥ በጠቆምኳቸው ማሥጠንቀቂያዎች ይሆንን ? ) እርግጥ ሞት ለሁሉም ሰው በተራ የሚደርስ ነው በምድር ላይ ለዘላለም የሚኖር ከቶም የለም ሁሉም ሰው ወደ አፈርነት መቀየሩ አይቀርም በማንኛውም የሞት መንገድ ህይወቱ ይለፍ ፤ ሰው አሥቀድሞ አፈር በመሆኑ ወደአፈር መመለሱ አይቀርም ( ልብ በሉ ከልጅነት እሥከ እውቀት የአፈርን ምርት በልተን ነው ዛሬ ጎልማሳና ሽማግሌ የሆን ነው ) ሰው ሁላ አላፊና ጠፊ ነው ማንም ዘላለማዊ አይደለም በዚህ እውነት ዙሪያም የሚያጠነጥኑ ፅሑፎች ደጋግሜ ፅፊያለሁ ለዚህ ይሆን ከነጩ ቪላ ጥግ የነጮቹን ሤራ ተገንዝቤ በፍርሐት አድፍጬ የተገኘሁት ?

በነገራችን ላይ ሲአይ ኢትዮጵያን ለመጋጥ እንዲህ ያሰፈሰፈ ጂብ ሆኖ በቅርብ በገሃድ ይታያል ብዬ ባላሥብም፣ የምእራቡን እና የተባበረችውን አሜሪካ የሚዘውሯት ቱጃሮች ለኸጫቸውን እያዝረበረቡ ለዘመናት ኢትዮጵያን በመጎምጀት እንደሚያዮት ኢትዮጵያም የምትጠፋው በራሷ ዜጎች እንደሆነ ገብቷቸው ያለመታከት ሤራቸውን ለመተግበር ሲሰሩ እንደነበር ግን ህሊና ያለን እና ከነጮቹ የተሻለ አእምሮ ያለን እኛ ኢትዮጵያዊያን እናውቅ ነበር

ወደህልሜ ልመልሳችሁ

ወታደሩ በምን ይመሰላል ? በሻንጣ ውሥጥ ያለው ፈንጂሥ ?

ህልሜን ዛሬ ላይ ሆኜ ለመፍታት እችላለሁ ፈንጂው ወይም ታይም ቦንቡ ፣ኢትዮጵያን ለማጥፋት በባንዳነት ከታሪካዊ ጠላቶቻችንን እና በሰው ደም ወይም በአፍሪካውያን ደም ከደለቡት ጅብ ምእራባውያን ቱጃሮች ጋር የወገነውን ህወሓትን የሚመለከት ነው

ተጨማሪ ያንብቡ:  በጎጃም ከሚያዝያ እስከ ነሐሴ ባሉት ወራት 8 አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል፤ ሰማያዊ ፓርቲ ማብራሪያ ጠየቀ

ዛሬ ለጊዜው ከፊሉ የትግራይ ከተሜ ከአሸባሪው ህውሃት ጋር ቢወግንም ነገ ከነገወዲያ የለ ኢትዮጵያ ህልውና እንደሌለው ሲረዳ ኢትዮጵያ ማሪኝ ማለቱ አይቀርም ወዳጄ ላሚቷን ጠልተህ ወተቶን መመኘት ጅልነት መሆኑንን እወቅ የኢትዮጵያ መንግሥት በህግ አግባብ በሚመረጥ የትግራይ ከፍለ ሀገር ( በኢፈዴሪ መንግሥት የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ) አሥተዳደር ጋር ይተባበራል እንጂ ከአሸባሪው ህወሓት ጋር ያደርገዋል ብሎ ማሰብ በራሱ ይከብዳል

አንድ አንድ ሊሂቃን የነበረው እንዳልነበረ ሆኗል አብቅቷል ይሉናል ሆኖም ግራ የተጋባው ፤ ከሁለቱም ጎን ያልቆመው የትግራይ ህዝብ የማሰቢያ ጊዜ ይሰጠው ለአምሥት ለስድስት ወር ከጦርነት እፎይ ይበል አለ እንጂ ማዓከላዊ መንግሥት በአሸባሪነት የተፈረጁት የጥፋት ኃይሎች ወደ ሥልጣን ይምጡ አላለም የትግራይ ህዝብ የራሴ ጅብ ይብላኝ የሚል የዋህ እንደማይሆን እና ለዘላቂ ጥቅሙ ብቻ ሳይሆን በደም ከተሳሰረው የኢትዮጵያ ህዝብ ላለመለየት ህውሃቶችን በቃችሁ ! ” እንደሚል አሥባለሁ

ህውሃት በባንዳነት አገር የምትጠፋበት ቦንብ ዛሬ አሁን በአገር ላይ ማንጠልጠሉን የትግራይ ህዝብ አሥተውሎ ይህ የቅጥረኝነት ጨዋታ ይበቃል ! ” በማለት ፣ ወደ ህሊናው ሲመለስ ነውና ፤ ላሚቱን ከፊት ለፊቱ ዞር ማድረግ ተገቢ ነው የትግራይ ህዝብ በንፁህ ህሊና የራሱን መሪ እሥከሚመርጥበት ጊዜ ድረሥም በጀት እና መሠረተ ልማት አይኖረም ምናልባት ቢኖር ለአሸባሪው የወንድ በር መሥጠት ነው በጀት መሥጠት ብሎ ነገር ግን አይኖርም

ህውሃት የሸሸጋትን በቀድሞ ቅኝ ገዢዎች የተሰራች በጊዜ የምትፈነዳ ቦንብ መቼ የት እንደምትፈነዳ አይታወቅም ከዚህ ፀረ _ ኢትዮጵያ ኃይል ጋር ድርድር አይሰፈልግም ትግራይ የኢትዮጵያ ታሪክ ናት ቅኝ ገዢዎች ካቋቋሙት የእብዶች ሥብሥብ ጋር ድርድር ከቶም አያሥፈልግም ህውሃት እኮ በቢላ ህዝብን እያሥፈራራ የሚገዛ ሂትለራዊ ሤጣናዊ ኃይል ነው ከአልቃይዳም ሆነ ከአቦኩሃራም በመቶ እጅ የሚበልጥ ጨካኝና ግፈኛ ነው ።

ከአሸባሪ ቡድን ጋራ ፣ ድርድር ይቅርና ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ያለ እውቅናውና ግልፅ ቁጥጥሩ ፤ በአየር የሚደረግ እርዳታን መፍቀድ አይኖርበትም ገለልተኛ የትግራይ ጊዜያዊ አሥተዳደር ሊቋቋም ግን ይቻላል

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከአምቦ ተፈናቅለው በአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት የተጠለሉ የአማራ ተወላጆችን አስመልክቶ በፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል የተቀነባበረ ዘጋቢ ፊልም

ማጠቃለያ

ህልሜ ዛሬ ተፈቷል የነጩ ቪላ ሚሥጥር የነጮች ረዢም እጅ ነው ነጮቹ ትላንትም በኢትዮጵያ ጉዳይ እጃቸው ነበረ ዛሬም አለ ለልማት ለብልፅግና በተነሳን ቁጥር ለጥቅማቸው ሲሉ እርሥ በእርሥ የሚያባሉን ዛሬም የአፍሪካ ቅኝ ገዢነበሩት ናቸው

የግንጠላ ጥያቄ ከትግራይ ህዝብ ከቶም አይነሳም የማንን ወተት ጠጥቶ ሊኖር ነው እገነጠላለሁ የሚለው ? ያሳደገችውን ኢትዮጵያ የምንጅላቶቹን ሀገር አልፈልግሺም ከአንቺ ተለይቼ እኖራለሁ ማለት ይቅርና በህልሙም ፣ የሚያስብው አይመሥለኝም

ህዝብ ሥንል 10 እና 11 ሚሊዮን የትግራይ ህዝብ መካከል ግማሽ ሚሊዮን የሚሆን የዘረፋው ጠበል የደረሰው ከህውሃት ጋር የቆመው ብቻ ነው ፤ ካልን ተሳስተናል የትግራይን ህዝብ በሙሉ በፀረ ኢትዮጵያዊነት መፈረጅ ትልቅ ሥህተት ነው ። ተመሳሳይ ችግር በአዳዋ ጦርነት ታይቷል ። በ1928 በማጨው ጦርነት ከዚህ የከፋ ባንዳነት ታይቷል ።ትግራይን ከኢትዮጵያ ህዝብ ለይቶ ማየት ለግንጠላ ድርድር ማቅረብ ለቅኝ ገዢዎቻችን ሃሳብ መንበርከክ ነው

እናም የትግራይ ህዝብ የተጎነጎነበትን ሤራ በቅጡ ለመረዳት እድሉ ይሰጠው መኩራት ያለበት በኢትዮጵያዊነቱ እንደሆነ ያምናል በተጣበቀ አንጀቱ በዶላር የጠገቡትን ባንዳዎቹን ምሥኪኑ የትግራይ ህዝብ የሚደግፋቸው አይመሥለኝም ።የሚቀምሰው የቸገረው ፣ብዙሃኑ ህዝብ በሃሺሽ በሠከሩ አራጆች ተከቦ በፍርሃት ቆፈን ውሥጥ ነው ፤ የሚኖረው የእናቱን የኢትዮጵያን ወተት እንዳይጠጣ የከለከሉትም በሥሙ የሚነግዱ ሃሺሽ ያሠከራቸው ባንዳዎች መሆኑንን አሣምሮ ያውቃል

የህልሜ ፍፃሜ ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዳው ቦንብ ይከሽፍ ዘንድ ፣ ለፈንጂ አክሻፊ ባለሙያ መሠጠቱን ያመለክታል ይህ ደግሞ የኢትዮጵያ ጦር ለጊዜው ከመቀሌ መውጣቱን አጥፊ የሆነውን ፈንጂ ማክሸፉን ግልፅ አድርጎልኛል የታቀደው የኢትዮጵያን ጦር የማጠልሸት ሤራ ከሽፏል ። ዕቀባውና ጦር ማሥገባቱም እንዲሁ ። በህዝቡ መሐል ህውሃቶች ተሸሽገው ከጀርባው ተኩሰው በዘግናኝ ሁኔታ ጦሩን የገደሉትና ከኃይሉ ቆርጠው ምርኮኛ ያደረጉት በወገኑ ላይ ጥይት ባለመተኮሱ ነው ሠራዊቱ ባልተገባ መሰዋትነት ህዝቤን አልገልም ብሎ ሞቷ

በመሰዋትነቱም ኢትዮጵያን አድኗል የትግራይ ኃይማኖተኛ ህዝብም ይህንን ይገነዘባል ።በቅርብ ቀንም አሸባሪውን ህውሃት ህዝቡ በእኛ መነገዱ ይበቃል ! “እንደሚለው ተስፋ አደርጋለሁ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share